Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
ማሕደረ ዜና፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላዉ ዓለም የተደረጉ፣ ሊደረጉ የታቀዱና የተነገሩ ዓበይት ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዘወትር ሰኞ ይቃኙበታል። ዝግጅቱ የሐገራትን፣ የዓለም አቀፍ እና አካባቢያዊ ማሕበራትን፣ድርጅቶችንና የታዋቂ ግለሰቦችን ያለፈ፣ያሁንና የወደፊት ምግባሮችን እያነሳ በባለሙያዎች አስተያየት የተደገፈ ትንታኔ ይቀር... more
FAQs about ማሕደረ ዜና:How many episodes does ማሕደረ ዜና have?The podcast currently has 339 episodes available.
March 31, 2025ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮጵያ ፈርጀ ብዙ ቀዉስየብርቱካን ተመስገን ትረካ እዉነት-ሐሰትነት ለብዙዎች በጣሙን እሁለት ለተገመሱት ለማሕበራዊ መገናኛ ዘዴ አስተያየት ሰጪ-ተከታታዮች ማከራከሩን እንደቀጠለ ነበር።ግን እንዲያዉ ለመጠየቅ ያሕል 120 ሚሊዮን የሚሆነዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሐቁን የሚያወጣ አንድ መርማሪ ፖሊስ፣ አንድ መርማሪ የሕግ ባለሙያ፣ አንድ መርማሪ ጋዜጠኛ፣ አንድ የምክር ቤት አጣሪ ኮሚቴ እንዴት አጣ?...more15minPlay
March 24, 2025ማሕደረ ዜና፣ ሱዳኖች አንድም ሁለትም ሆነዉ ከግጭት-ጦርነት ያልተዩ ሐገራትየማቻር ደጋፊ የሚባሉት የኑዌር ጉሳ ሚሊሻዎች ኢትዮጵያን በሚያዋስነዉ ድንበር አካባቢ ከሠፈረዉ ከፕሬዝደንት ሳልቫኪር መንግስት ጦር ጋር መዋጋት ከጀመሩ ሳምንት አልፈዋል።የጁባዎች ጠብ የናረዉ ጁባዎች ከጋራንግ ሞት በኋላ እንዳደረጉት ሁሉ ከአል በሽር መወገድ በኋላ ዋና እና ምክትል ሆነዉ የካርቱም ሪፐብሊካን ቤተ መንግስትን የተቆጣጠሩት የሱዳን ጄኔራሎች የገጠሙት ጠብ በጦር ሜዳዉም በፖለቲካዉም መስክ ወደ አዲስ ምዕራፍ በተሸጋገረበት ወቅት መሆኑ ነዉ።የፈጥኖ ደራሹ ጦር ከደቡብ ሱዳን ቡድናት ካንደኛዉ ጋር ያለዉን ትብብር ከማጠናከርም አልፎ የትይይዩ መንግስት--- ዳርፉር ግዛት ሊመሰርት ይችላል የሚለዉ ግምትም እያየለ ነዉ...more13minPlay
March 17, 2025“መፈንቅለ-መንግሥት” ወይስ “ሕግ ማስከበር” የትግራይ ቅርቃርየህወሓት አመራሮች ልዩነት ሲበረታ በደም አፋሳሽ ጦርነት ውስጥ ያለፈው የትግራይ ክልል ነዋሪ “ነገስ ምን ይፈጠራል?” በሚል “እየተሳቀቀ እንዲኖር” ተገዷል። ነዋሪዎች እንደሚሉት ጦርነት ይቀሰቀሳል በሚል ሥጋት “ሰዉ በጣም ተረባብሿል”፤ በኅብረተሰቡ ዘንድ “መከፋፈል” ተፈጥሯል። ነጋዴዎች የዋጋ ጭማሪ በማድረጋቸው “የኑሮ ውድነቱ እያሻቀበ” ነው።...more12minPlay
March 10, 2025ደቡብ ሱዳን ወደ የርስ በርስ ጦርነት ዳግም እየተንሸራተተች ይሆን?ከኢትዮጵያ ድንበር 30 ኪሎ ሜትር በምትርቀው ናስር ከተማ በደቡብ ሱዳን ጦር ሠፈር ላይ የተፈጸመ ጥቃት ጁባን ፖለቲካዊ ውጥረት ውስጥ ከቷታል። በናስር በሚገኝ የደቡብ ሱዳን የጦር ሠፈር ላይ ባለፈው ሣምንት ጥቃት የፈጸመው ዋይት አርሚ ተብሎ የሚጠራ የኑዌር ጎሳ ታጣቂ ቡድን ነው። ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር ምክትላቸው ሪየክ ማቻርን ሳያማክሩ የወሰዷቸው ርምጃዎችም ቅሬታ ፈጥረዋል። ሁለቱ የተፈራረሙት የሰላም ሥምምነት ፈርሶ ደቡብ ሱዳን ወደ የርስ በርስ ጦርነት እንዳትገባ ሥጋት አለ።...more13minPlay
March 03, 2025ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮ-ሶማሊያ ወዳጅነት ካንጀት ወይስ ካንገት?የአዲስ አበባና የሞቃዲሾ መሪዎች የጠባቸዉን መሰረታዊ ምክንያት ሙሉ በሙሉ ማስወገዳቸዉን በይፋ ሳይናገሩ በወር ዕድሜ ለመወዳደስ፣ መተቃቀፍ መነፋፈቅ መድረሳቸዉ በርግጥ ጉድ አጃኢብ ማሰኘቱ አልቀረም።ማስታወቂያ ሚንስትር ዳዉድ አዌስ እንደሚሉት ግን ኢትዮጵያና ሶማሊላንድ የተፈራረሙት የመግባቢያ ሥምምነት ተሰርዟል።አዲሱ የትብብር ምዕራፍ ለኢትዮጵያ ወደብ ሥለ ማስገኘት አለማስገኘቱ በግልፅ የሚታወቅ ነገር የለም።የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል የምክር ቤት አባልናየፖለቲካ ተንታኝ ዶክተር አብዲ ቡባል እንደሚሉት ደግሞ መተማመንን ለመገንባት ከአዲስ አበባ-ሞቃዲሾ-አንካራ የሚባክኑት ባለሥልጣናት ወደብን በተመለከተ አሁንም አይተማመኑም...more14minPlay
February 24, 2025ማሕደረ ዜና፣ የሱዳን ትዩዩ መንግስት፣ ጦርነቱና የዉጪ ጣልቃ ገብነትጉባኤተኞቹ እንዳሉት ዓላማቸዉ የሱዳንን አንድነት፣ የሕዝቧን ሠላምና ደሕንነት በጋራ ማስከበር ነዉ።የጉባኤተኞቹን ዉሳኔ በንባብ ያሰሙት የፍትሕና የእኩልነት ንቅናቄ መሪ ሳንዳል ሐጋር እንዳሉት ደግሞ ጦርነቶችን በሙሉ ለማቆም ቆርጠዋልምተባባሪዎቹ በአማላይ ቃላት የከሸኑትን ሥምምነትና ትብብር ገቢር ማድረግ አለማድረጋቸዉ በርግጥ አጠያያቂ ነዉ።ፈጥኖ ደራሹ ጦር ከቀድሞ ቀንደኛ ጠላቶቹ በተለይም ከSPLM-N ጋር መወዳጀቱ ግን የወታደራዊ ጉዳይ ተንታኞች እንደሚሉት ከምዕራባዊ ሱዳን እስከ ደቡብ ሱዳን ድንበር ጥግ፣ ከሊቢያ ጠረፍ እስከ ኢትዮጵያ ድንበር በሚደርሱ አካባቢዎች ለመንቀሳቀስ ይጠቅመዋል።...more15minPlay
February 17, 2025ማሕደረ ዜና፣ የሁለት ጉባኤዎች አጭር ወግየሐገራት መሪዎች፣ ሚንስትሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ የማሕበራት ሊቃነ መናብርት፣ ባለሙያዎች፣ የሠላምን ጥቅም፣ የዴሞክራሲን ፋይዳ፣ ተባብሮ የመሥራትን አስፈላነትን፣ ግጭት፣ጦርነት፣ አለመግባባት ያደረሱና የሚያደርሱትን ጉዳት የሚገልፁ፣ዉብ፣አማላይ፣ ማራኪ ቃላትን በየአዳራሹ አዘነቡት።በነዚያዉ ቃላት ተጠዛጠዙባቸዉም።የአፍሪቃ መሪዎች ዉሳኔ፣ መግለጫ ከአዲስ አበባ ሲናኝ የሙኒክ ጉባኤተኞች የፕሬዝደንት ሼሴኬዲን ማብራሪያ ያዳምጡ ነበር።እዚያዉ ምሥራቃዊ ኮንጎ ግን በሩዋንዳ የሚደገፈዉ M23 አርብ የቡካቩ አዉሮፕላን ማረፊያን ቅዳሜ ከተማይቱን ተቆጣጠረ...more14minPlay
February 11, 2025ማሕደረ ዜና፣ የትራምፕ መርሕ፣ርምጃና ዉሳኔ ልማት ወይስ ጥፋትየትራምፕን እርምጃ ከማንም ቀድመዉ የአሜሪካ ታማኝ፣ የቅርብ ወዳጆች ብሪታንያ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይን ጨምሮ 79 መንግስታት አዉግዘዉታልፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈዉ 21 ቀናት ዉስጥ የወሰዷቸዉ እርምጃዎች፣ ያሰለፏቸዉ ዉሳኔዎችና ያፀደቋቸዉ ትዕዛዛት ነባሩን የዓለም ፖለቲካዊ ሥርዓት ግራ ቀኝ ያላጉ፣ የአሜሪካንን ተቀባይነት የሸረሸሩ፣ እርዳታ ተቀባዮችን፣ ሰጪዎችንም የሚጎዳ ነዉ።የተቀረዉ ዓለም በያለበት «አንድ እግር በርበሬ----»ን በተናጥል ከማላዘን ባለፍ እስካሁን ሰብሰብ ብሉ ጠንካራ አፀፋ ለመስጠት አልቃጣም ወይም አልቻለም።ትራምፕም ቀጥለዋል።መጨረሻቸዉ ነዉ-ናፋቂዉ።...more15minPlay
January 27, 2025ከጋዛ እስከ ዩክሬን ጦርነት ያልተለየዉ ዓለም ከአዉሽቪትስ ምን ተማረ?የፍልስጤም የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን እንደገመተዉ ትንሺቱ ሰርጥ 85 ሺሕ ቶን ፈንጂ እየዘነበባት አስከሬን ስታመርት፣ ቁስለኛ ስታሰላ፣ ፍርክስካሽ ስትከምር 15 ወራት አስቆጥራለች።መኖሪያ፣ ትምሕርት፣ መስሪያ ቤቶች፣ ዩኒቨርስቲዎች፣ የስደተኛ መጠለያዎች፣ መሳጂዶች፣ የንግድ፣ የዉሐ፣ የኤሌክትሪክ፣ የስልክ ተቋማት ወድመባታል።...more14minPlay
FAQs about ማሕደረ ዜና:How many episodes does ማሕደረ ዜና have?The podcast currently has 339 episodes available.