Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
ማሕደረ ዜና፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላዉ ዓለም የተደረጉ፣ ሊደረጉ የታቀዱና የተነገሩ ዓበይት ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዘወትር ሰኞ ይቃኙበታል። ዝግጅቱ የሐገራትን፣ የዓለም አቀፍ እና አካባቢያዊ ማሕበራትን፣ድርጅቶችንና የታዋቂ ግለሰቦችን ያለፈ፣ያሁንና የወደፊት ምግባሮችን እያነሳ በባለሙያዎች አስተያየት የተደገፈ ትንታኔ ይቀር... more
FAQs about ማሕደረ ዜና:How many episodes does ማሕደረ ዜና have?The podcast currently has 324 episodes available.
February 24, 2025ማሕደረ ዜና፣ የሱዳን ትዩዩ መንግስት፣ ጦርነቱና የዉጪ ጣልቃ ገብነትጉባኤተኞቹ እንዳሉት ዓላማቸዉ የሱዳንን አንድነት፣ የሕዝቧን ሠላምና ደሕንነት በጋራ ማስከበር ነዉ።የጉባኤተኞቹን ዉሳኔ በንባብ ያሰሙት የፍትሕና የእኩልነት ንቅናቄ መሪ ሳንዳል ሐጋር እንዳሉት ደግሞ ጦርነቶችን በሙሉ ለማቆም ቆርጠዋልምተባባሪዎቹ በአማላይ ቃላት የከሸኑትን ሥምምነትና ትብብር ገቢር ማድረግ አለማድረጋቸዉ በርግጥ አጠያያቂ ነዉ።ፈጥኖ ደራሹ ጦር ከቀድሞ ቀንደኛ ጠላቶቹ በተለይም ከSPLM-N ጋር መወዳጀቱ ግን የወታደራዊ ጉዳይ ተንታኞች እንደሚሉት ከምዕራባዊ ሱዳን እስከ ደቡብ ሱዳን ድንበር ጥግ፣ ከሊቢያ ጠረፍ እስከ ኢትዮጵያ ድንበር በሚደርሱ አካባቢዎች ለመንቀሳቀስ ይጠቅመዋል።...more15minPlay
February 17, 2025ማሕደረ ዜና፣ የሁለት ጉባኤዎች አጭር ወግየሐገራት መሪዎች፣ ሚንስትሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ የማሕበራት ሊቃነ መናብርት፣ ባለሙያዎች፣ የሠላምን ጥቅም፣ የዴሞክራሲን ፋይዳ፣ ተባብሮ የመሥራትን አስፈላነትን፣ ግጭት፣ጦርነት፣ አለመግባባት ያደረሱና የሚያደርሱትን ጉዳት የሚገልፁ፣ዉብ፣አማላይ፣ ማራኪ ቃላትን በየአዳራሹ አዘነቡት።በነዚያዉ ቃላት ተጠዛጠዙባቸዉም።የአፍሪቃ መሪዎች ዉሳኔ፣ መግለጫ ከአዲስ አበባ ሲናኝ የሙኒክ ጉባኤተኞች የፕሬዝደንት ሼሴኬዲን ማብራሪያ ያዳምጡ ነበር።እዚያዉ ምሥራቃዊ ኮንጎ ግን በሩዋንዳ የሚደገፈዉ M23 አርብ የቡካቩ አዉሮፕላን ማረፊያን ቅዳሜ ከተማይቱን ተቆጣጠረ...more14minPlay
February 11, 2025ማሕደረ ዜና፣ የትራምፕ መርሕ፣ርምጃና ዉሳኔ ልማት ወይስ ጥፋትየትራምፕን እርምጃ ከማንም ቀድመዉ የአሜሪካ ታማኝ፣ የቅርብ ወዳጆች ብሪታንያ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይን ጨምሮ 79 መንግስታት አዉግዘዉታልፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈዉ 21 ቀናት ዉስጥ የወሰዷቸዉ እርምጃዎች፣ ያሰለፏቸዉ ዉሳኔዎችና ያፀደቋቸዉ ትዕዛዛት ነባሩን የዓለም ፖለቲካዊ ሥርዓት ግራ ቀኝ ያላጉ፣ የአሜሪካንን ተቀባይነት የሸረሸሩ፣ እርዳታ ተቀባዮችን፣ ሰጪዎችንም የሚጎዳ ነዉ።የተቀረዉ ዓለም በያለበት «አንድ እግር በርበሬ----»ን በተናጥል ከማላዘን ባለፍ እስካሁን ሰብሰብ ብሉ ጠንካራ አፀፋ ለመስጠት አልቃጣም ወይም አልቻለም።ትራምፕም ቀጥለዋል።መጨረሻቸዉ ነዉ-ናፋቂዉ።...more15minPlay
January 27, 2025ከጋዛ እስከ ዩክሬን ጦርነት ያልተለየዉ ዓለም ከአዉሽቪትስ ምን ተማረ?የፍልስጤም የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን እንደገመተዉ ትንሺቱ ሰርጥ 85 ሺሕ ቶን ፈንጂ እየዘነበባት አስከሬን ስታመርት፣ ቁስለኛ ስታሰላ፣ ፍርክስካሽ ስትከምር 15 ወራት አስቆጥራለች።መኖሪያ፣ ትምሕርት፣ መስሪያ ቤቶች፣ ዩኒቨርስቲዎች፣ የስደተኛ መጠለያዎች፣ መሳጂዶች፣ የንግድ፣ የዉሐ፣ የኤሌክትሪክ፣ የስልክ ተቋማት ወድመባታል።...more14minPlay
December 30, 2024ጀዋር መሐመድ እና ወቅታዊ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምልከታውከሰሞኑ በመገናኛ ብዙኃን የተከሰተው ጀዋር መሐመድ እንደገና አነጋጋሪ መሆን ችሏል። ከእስር ከተፈታ በኋላ ድምጹን አጥፍቶ የነበረው ፖለቲከኛው በራሱ ህይወት ዙሪያ የጻፈውን መጽሐፍ ለንባብ ከማብቃቱ ባሻገር በሚታወቅበት ድምጸት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ እና መንግስታቸው ላይ ብርቱ ትችት ማሰማት ጀምሯል።...more14minPlay
FAQs about ማሕደረ ዜና:How many episodes does ማሕደረ ዜና have?The podcast currently has 324 episodes available.