Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
ማሕደረ ዜና፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላዉ ዓለም የተደረጉ፣ ሊደረጉ የታቀዱና የተነገሩ ዓበይት ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዘወትር ሰኞ ይቃኙበታል። ዝግጅቱ የሐገራትን፣ የዓለም አቀፍ እና አካባቢያዊ ማሕበራትን፣ድርጅቶችንና የታዋቂ ግለሰቦችን ያለፈ፣ያሁንና የወደፊት ምግባሮችን እያነሳ በባለሙያዎች አስተያየት የተደገፈ ትንታኔ ይቀር... more
FAQs about ማሕደረ ዜና:How many episodes does ማሕደረ ዜና have?The podcast currently has 339 episodes available.
March 16, 2026ማሕደረ ዜና ፣ የእስራኤል-ዩናይትድ ስቴትስና የኢራን የዉጊያ ሥልትና መልስ የለሽ ጥያቄዎችየቀድሞዉ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት መንግሥት ኃይለማርያም የናደዉ ዕዝ በ1987 (እጎአ መሆኑን አይዘንጉ) ግድም አፍአበት ላይ የገጠመዉን ሽንፈት ጠላት «አካቢዉን ከበቦ ሲያበቃ የዕዙን ጭንቅላት በጠበጠዉ» ዓይነት ብለዉ ባጭሩ ገልፀዉት ነበር።የእስራኤልና የዩናይትድ ስቴትስ ጦር የካቲት 28 ጧት የኢራንን የፖለቲካ፣ የጦርና የስለላ እናትን ቆርጦ ቢጥልም ፋርሶች እንደታሰበዉ «ያልተበጠበጡበት» ሁለተኛዉ ምክንያት የጠላታቸዉን የዉጊያ ሥልት ብዙ አጥንተዉ በቅርብ አመታት ኢራቅ፣ አፍቃኒስታንና ሊቢያ ላይ ከሆነዉ ተምረዉ የነኬይን ዘመናይ ሥልት በነ አፄ ምኒልክ ጥንታዊ ሥልት ለመመከት በመዘጋጀታቸዉ ነዉ።...more15minPlay
March 09, 2026ማሕደረ ዜና፣ የእስራኤል-ዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ጦርነት ያስከተለዉ ምሥቅልቅልእስራኤልና ዩናይትድ ስቴትስ ኢራንን መደብደብ የጀመሩት ቴሕራን ላይ የኢራን መሪዎችን፣ ሚናብ ዉስጥ ሕፃናት ሴት ተማሪዎችን በመግደል ነዉ።መሪዎቹን ከነሚስት ልጆቻቸዉ መግደል ለቴል አቪቭ ዋሽግተን መሪዎች ራሳቸዉ ደጋግመዉ እንዳሉት ጀግንነት ነዉ።የሚናብ-ኢራን ሴት ተማሪ-አስተማሪዎችን መግደል ግን ለዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራም የቴሕራኖች ሥራ እንጂ በዓለም ተወዳዳሪ የማይገኝለት ጦራቸዉ ስሕተት ዓይደለም።...more16minPlay
March 02, 2026ማሕደረ ዜና፣ የኻምኔይ መገደል፣ የኔታናያሁ የዕድሜ ልክ ምኞትና የትራምፕ ፉከራሳዳም ሁሴይ፣ ኦስማ ቢን ላደን፣ ሙዓመር ቃዛፊ፣ ዑስማኢል ሐንያሕ፣ ሐሰን ነስረላሕ ሌሎችም ሲገደሉ ዓለም ከአምባገነኖች፣ከጨቋኞች እና ካሸባሪዎች መላቀቋን የቴል አቪቭ-ዋሽግተን-ለንደን-ብራስልስ መሪዎች ለዓለም አዉጀዉ ነበር።ዓለም ግን ዘንድሮም ሰላም አታዉቅም።አምና ጥር ለሁለተኛ ጊዜ የዩናይትድ ስቴትስን የፕሬዝደትነት ሥልጣን የያዙት ዶናልድ ትራምፕ የሰላም ፕሬዝደንት መሆናቸዉን ሲደሰኩሩ የልዕለ ኃያሊቱ ሐገር መሪዎች የጦርነትን አትራፊነት ብቻ ሳይሆን አስከፊነትቱን የተረዱ መስለዉ ነበር...more16minPlay
February 23, 2026ማሕደረ ዜና፣ የዩክሬን ጦርነት አራተኛ ዓመት፣ መቆሚያ አለዉ ይሆን?ዩክሬንን የሚደግፉት የምዕራባዉያን መንግሥታትና ተቋማት እንደሚሉት የሩሲያ ዕቅድ ኪቪን ባጭር ጊዜ ምናልባትም በሶስት ቀናት ዉስጥ ተቆጣጥሮ ዜለንስኪና ተባባሪዎቻቸዉን አንቆ ወደ ሞስኮ ለመዉሰድ ነበር።ፑቲን ግን ዘመቻዉ ልዩ፣ ዩክሬንን በኃይል የመግዛት ዕቅድም እንደሌላቸዉ አስታዉቀዉ ነበር።የጦርነቱ ዕቅድ ምዕራባዉያኑ እንደገመቱትም ሆነ ፑቲን እንዳሉት እስካሁን አሸናፊና ተሸናፊ አልተለየም።...more14minPlay
February 16, 2026ማሕደረ ዜና፣62ኛዉ የሙኒክ የፀጥታ ጉባኤ፣የአዉሮጳ አሜሪካኖች ልዩነት መድረክየጀርመኑ መራሔ መንግሥት የአሜሪካ ወዳጆቻችን በቀጥታ እንዲረዱት በማለት ለጉባኤተኞች በእንግሊዘኛ ጭምር ያደረጉት ንግግር አዉሮጶች በትራምፕ አስዳደር እርምጃና መርሕ ከመስጋት አልፈዉ መናደድ፣ መቆጣታቸዉን የሚያስረዳ ነዉ።የፈረንሳይና የሌሎች የአዉሮጳ መንግሥታት መሪዎችና ተወካዮችም የፕሬዝደንት ትራምፕ አስተዳደርን በተደጋጋሚ ተችተዋል።አዉሮጳ የራስዋን የመከላከያ ኃይል ማጠናከር እንደሚገባት አሳስበዋልም።...more14minPlay
February 09, 2026ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮ-ኤርትራ ጠብ፣ የአፍሪቃ ቀንድ የሰላም ሥጋትሮሞች፣ቱርኮች፣ፖርቱጋሎች፣ አረቦች፣ አዉሮጶች፣ሐበሾች፣ ግብፆች፣ ሶቭየት ሕብረቶች፣ ኩባዎች፣ አሜሪካኖች በየዘመናቸዉ ዘምተዉ ገድለዉ ሞተዉበታል።የዚያን ምድር ሕዝብ ደም አፋሰዉበታል።በቅርቡ ደግሞ የመካከለኛዉ ምሥራቅና የእስያ ኃያል ቱጃር መንግሥታት እየተራኮቱበት ነዉ።የአፍሪቃ ቀንድ።የጎቲንገን ዩኒቨርስቲ ባልደረባ ዶክተር ማርኩስ ፊርግል ሆነ እንደሚሉት የአፍሪቃ ቀንድ የአዲስ ቅርምትና ማዕከል ሆኗል።...more14minPlay
February 02, 2026ማሕደረ ዜና፣ የዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ፍጥጫ ዲፕሎማሲ ወይስ ዉጊያባለፉት ጥቂት አመታት የዩናይትድ ስቴትስና የእስራኤል መሪዎች በወሰዱት እርምጃ የዓለም የዲፕሎማሲ ማዕከልነቱ የተሽመደመደዉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዲፕሎማቶችም የዋሽግተንና የቴሕራን መሪዎች ጦርነት ከመግጠም እንዲታቀቡ አደራ ብለዋል።በለንደን ስኩል ኦፍ ኤኮኖሚክስ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ፕሮፌሰር ፋዉዝ ጀርጀስ እንደሚሉት የዲፖሎማሲ ጥረት እየከሰመ፣ የጦርነቱ አይቀሬነት እየደመቀ ነዉ።...more14minPlay
January 26, 2026ማሕደረ ዜና፣ አንድ ዓመት ከትራምፕ «አሜሪካ ትቅደም» መርሕ ጋርየምዕራብ አዉሮጳ መንግሥታት የእስራኤን አለመቃወማቸዉን ሲያስታዉቁ፣ ትራምፕ እስራኤልን ደግፈዉ ኢራንን ደበደቡ።ኢራንን የኑክሌር ተቋማት ሙሉ በሙሉ አወደምን አሉም።12 ቀናት ያስቆጠረዉ የእስራኤል-ዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ጦርነት በተለይ ኢራንና እስራኤል ዉስጥ የሰዉ ሕይወት ከማጥፋቱ በተጨማሪ ከፍተኛ የምጣኔ ሐብት ኪሳራ አስከትሏል።ዩናይትድ ስቴትስም ለ18 ሰዓታት ድብደባ ወደ 2 ቢሊዮን ዶላር አዉጥታለች።የ12ቀናቱ ድብደባማ ሆነ ትራምፕ ያወ,ጁት ድል የእስራኤል፣ የዩናይትድ ስቴትስና የኢራን መሪዎች ለተጨማሪ ጦርነት ከመዛዛት፣ በጦር ኃይል ከመፋጠጥ አለማዳኑ እንጂ እንቆቅልሹ።ፍጥጫዉ ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ።...more15minPlay
January 19, 2026ማሕደረ ዜና፤ ሶማሊያ፣ የአዲሱ የአፍሪቃ ቀንድ ቅርምት ማዕከልበማግሥቱ ቅዳሜ የሞቃዲሾ መንግሥትን የሚደግፉ ወይም የእስራኤልና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን እርምጃ ከሚቃወሙት መካከል የቱርክ፣ የሳዑዲ አረቢያ፣ የሱዳንና የጅቡቲ አምባሳደሮችና ፖለቲከኞች ላስ አኖድ ገቡ።የዲፕሎማቶቹና የፖለቲከኞቹ ጉብኝት አዲስ በተመረጡት የሰሜን ምሥራቅ ግዛት ፕሬዝደንት አብዲቃድር አሕመድ አዊ-ዓሊ (ፊርዲሕዬ) በዓለ-ሲመት ላይ ለመገኘት እንደሆነ ተነግሯል።ትክክለኛ መልዕክቱ ግን እስራኤል ከድፍን ዓለም ተሽቀዳድማ፣ የዓለም ሕግን ጥሳ፣ የሶማሊያን ሉዓላዊነት አፍርሳ፣ ለሶማሊላንድ ዕዉቅና መስጠቷን ከቃላት በላይ በድርጊት ለመቃወም ነዉ...more15minPlay
January 12, 2026ተቃውሞ የበረታባት ኢራን ለድርድርም ይሁን ለጦርነት ዝግጁ መሆኗን ገለጸችኢራን ዳግም በተጣለባት ማዕቀብ መገበያያ ገንዘቧ ሲላሽቅ በተፈጠረ ኢኮኖሚያዊ ጫና የተቀሰቀሰ ተቃውሞ ሦስተኛ ሣምንቱን አስቆጥሯል። እስካሁን ከ530 በላይ ተዋሚዎች እና የጸጥታ አስከባሪዎች መገደላቸውን አክቲቪስቶች ገልጸዋል። ኢራን ለተቃውሞዎች እንግዳ ባትሆንም ጂዖ ፖለቲካዊ ሁኔታዎች ፣ የአሜሪካ እና የእስራኤል መሪዎች የሰጧቸው አስተያየቶች የአሁኑን አሳሳቢ አድርገውታል።...more13minPlay
FAQs about ማሕደረ ዜና:How many episodes does ማሕደረ ዜና have?The podcast currently has 339 episodes available.