
Sign up to save your podcasts
Or


ክፍል 3፡ የባህል ሚና ለሰላም, ሰብዓዊ መብት እና ዲሞክራሲ ግንባታ
በዚህ ክፍል የባህል ተመራማሪ ከሆኑ ዶ/ር ጥላሁን በጅቷል ጋር ኪነ-ጥበብ፣ባህል እና ፈጠራ በሰላም ግንባታ፣ሕብረተሰብ ላይ ተሃድሶ በመፍጠር እንዲሁም በብሔራዊ ኢትዮጵያዊ ማንነት ላይ ምን አይነት ሚና እንደሚጫወቱ እንዳስሳለን፡፡
ከባህላዊ ትሩፋቶች እስከ ዘመናዊ ኪነ-ጥበብ ድረስ ያሉትን ሁኔታዎች እንዲሁም በባህል፣በግጭት መፍታት እና በሰብዓዊ መብት መካከል ያሉትን ጥልቅ ትስስሮች ዶ/ር ጥላሁን ይተነትናሉ፡፡ በተጨማሪም የበርካታ አመታት ጥናት ላይ ተመርኩዘው ዶ/ር ጥላሁን የሚከተሉት ላይ ምልከታቸውን ያጋራሉ፡፡
· ከበፊት የተወረሱ፣ጎልተው የሚታዩ እንዲሁም ብቅ ብቅ እያሉ የሚገኙ አዳዲስ ባህሎች ሚና · ባህል በምን መልኩ የማኅበራዊ ስምምነትን ያዳብራል · የኢትዮጵያን የፈጠራ ዘርፍ ምን ተግዳሮቶች ተጋርጠውበታል · ኪነ-ጥበብ ለምን የፖሊሲ ድጋፍ እና የኢኮኖሚ ኢንቨስትመንት ያስፈልገዋል
ይመልከቱ እንዲሁም አስተያየትዎን ያስፍሩ!
ሰብስክራይብ ያድርጉ፤ አዳዲስ ክፍሎች ሲወጡ እንዲደርስዎም የደወል ምልክቱን ይጫኑ!
ለበለጠ መረጃ ድረ-ገጻችንን https://cfcafrica.org ይጎብኙ፡፡
In this powerful episode, we sit down with Dr. Tilahun Bejitual—a cultural researcher—to explore how art, culture, and creativity can play a transformative role in peace building, social healing, and national identity in Ethiopia.
Drawing from years of research and fieldwork, he shares insight on:
• The role of residual, dominant, and emerging cultures • How culture can foster social harmony • The challenges facing Ethiopia's creative sector • Why the arts need policy support and economic investment
Watch, comment, and share your thoughts below.
Don't forget to subscribe and hit the notification bell to stay updated.
Discover more at https://cfcafrica.org.
#CfCAEthiopia #1PercentForCulture #SustainablePublicFunding
Culture as a Driver for Job Creation is the third episode in the CfCA Ethiopia Podcast series-a platform for rich and reflective conversations on culture and the cultural and creative industries (CCIs). Hosted by Teshome Wondimu and subtitled in English, this episode explores the vital link between culture and employment in Ethiopia. Can cultural heritage become a source of sustainable jobs and economic development?
Joining the discussion is Dr. Bayleyegn Tasew, a renowned cultural anthropologist with nearly four decades of experience studying Ethiopian culture, folklore, and society. Together, they unpack the potential of Ethiopia's cultural assets to drive job creation, stimulate local economies, and empower communities.
Discover more at https://cfcafrica.org.
የሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ ፖድካስት ሁለተኛው ክፍል 'የመንግስት ድጋፍ ለባህል' የሚል ሲሆን- በባህል እና የባህል እና ፈጠራ ኢንዱስትሪ ላይ የካበቱ እና ጥልቀት ያላቸው ውይይቶች የሚካሄዱበት መድረክ ነው፡፡
በተሾመ ወንድሙ ተዘጋጅቶ ከእንግሊዝኛ የግርጌ መግለጫ ጋር የሚቀርበው ይህ ክፍል በኢትዮጵያ እንዲሁም ከዛም ባሻገር ኪነ-ጥበብን ለመደገፍ የመንግስት ድጋፍ እንዴት እንደሚመደብ ይዳስሳል፡፡በባህል ላይ የመንግስት ኢንቨስትመንት ምን ይመስላል? ተስፋ ሰጪ የሆኑ አዳዲስ ክንውንኖች ምንድን ናቸው፤ክፍተቶችስ ያሉት እምን ጋ ነው? የሚሉትን ጥያቄዎች ይመለከታል፡፡
ይህንን ውይይት የሚቀላቀሉት ዶ/ር ይስማ ጽጌ ሲሆኑ ጥናታዊ ምርምር ስራዎችን የሚሰሩት ዶ/ር ይስማ በቅርብ ጊዜ የሰሩት ጥናት በባህል ዘርፉ ላይ የመንግስት የገንዘብ ድጋፍ ምን ይመስላል የሚለው ላይ የብርሃን ጮራን የሚፈነጥቅ ነው፡፡ አቶ ተሾመ እና ዶ/ር ይስማ በጋራ የዚህን ጥናት መረጃ በጥልቀት ይመለከታሉ፣ዘላቂ የገንዘብ ድጋፍ እንዳይኖር የሚያደርጉ እንቅፋቶች እንዲሁም የለውጥ መንገዶችም ላይ ይወያያሉ፡፡
ለበለጠ መረጃ https://cfcafrica.org
Public Funding for Culture is the second episode in the CfCA Ethiopia Podcast series—a platform for rich and reflective conversations on culture and the cultural and creative industries (CCIs).
Hosted by Teshome Wondimu and subtitled in English, this episode explores how public funds are allocated to support the arts in Ethiopia and beyond. What does government investment in culture look like? What are the promising developments—and where do the gaps remain?
Joining the conversation is Dr. Yisma Tsige, a researcher whose recent work shines a light on public financing within the cultural sector. Together, they delve into the data, discuss the barriers to sustainable funding, and highlight pathways for progress.
Tune in and explore more at https://cfcafrica.org
የባህል ምንነት እና ፋይዳው የሚለው የመጀመሪያ ክፍል የፖድካስት ዝግጅት የሲኤፍሲኤ ፖድካስት ተከታታይ ክፍሎችን መክፈቻ ዝግጅት ሲሆን ይህ ፖድካስት በባህል እና በባህላዊ እና ፈጠራ ኢንዱስትሪው ላይ ላተኮሩ የካበቱ እንዲሁም ጥልቅ ምልከታን የያዙ ውይይቶች የሚንጸባረቁበት መድረክ ነው፡፡
በዚህ በተሾመ ወንድሙ አቅራቢነት በሚቀርበው እና የእንግሊዝኛ የግርጌ መግለጫ ባለው የመክፈቻ ክፍል 'ባህል ምንድነው? ፋይዳውስ?ኅብረሰተብን በመቅረጽ ረገድ ምን ሚና ይጫወታል? እና በባህል ጥላ ስር የሚገኙት ዘርፎች ምንድናቸው?' የሚሉ መሰረታዊ ጥያቄዎችን በማንሳት መድረኩን እንከፍታለን፡፡
ዶ/ር ፍሬሕይወት ባዩ በምልከታቸው ባህል በእለት ተእለት ሕይወታችን እንዲሁም በማኅበረሰብ ላይ ያለውን ትርጉም እና አንድምታ በዝርዝር እንድመለከት በማድረግ ለውይይቱ ጥልቀት እና ትርጉም ይሰጡልናል፡፡
የበለጠ ለማወቅ የሚከተለውን ድረ-ገጽ ይጎብኙ https://cfcafrica.org
Defining Culture and Its Importance launches the CfCA Ethiopia Podcast series—a platform for rich and reflective conversations on culture and the cultural and creative industries (CCIs). In this opening episode, hosted by Teshome Wondimu, subtitled in English, we set the stage with fundamental questions: What is culture? Why does it matter? What role does it play in shaping society? and What domains fall under the umbrella of culture? Bringing depth and nuance to the conversation is Dr. Firehiwot Bayu, whose insights help us unpack the meaning and impact of culture in our everyday lives and communities.
Tune in and explore more at https://cfcafrica.org
From the publisher's feed