የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የመስከረም 16 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
    DW Amharic-የዛሬው የዓለም ዜና በኢትዮጵያ የጋዜጠኞች እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እስር እና ወከባ እየጨመረ መጥቷል መባሉ፤በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ መከበሩ፤የሱዳን ጦር በዋና ከተማይቱ ካርቱም የመድፍ እና የአየር ድብደባ መጀመሩ ፤ደቡብ አፍሪቃ በፀረ አፓርታይድ ትግሉ ወቅት በስደት ሆነው ህይወታቸውን ያጡ ዜጎቿን አስከሬን ወደ ሀገር መመለሷ፤የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የተኩስ አቁም ስምምነት ሀሳብን ውድቅ ማድረጋቸው እና ሩሲያ የምዕራቡን ዓለም ለመገዳደር አዲስ የኒዩክሌር ጦር መሳሪያ አጠቃቀም ሰነድ ማውጣቷን ያስቃኛል።
    11 min
  • የመስከረም 15፣2017 የዓለም ዜና
    ደቡብ ኢትዮጵያና ጋምቤላ ክልሎች በደረሱ የመኪና አደጋዎች 35 ሰዎች ሞቱ።ናይሮቢ-የኬንያ እናቶች ጥሪ፣ የአምንስቲ ጥያቄ።አቡጃ-በኢትዮጵያ በኩል ያለፈ አደንዛዥ ዕፅ ሌጎስ ላይ ተያዘ።ቫቲካን-የእስራኤል-ሒዝቡላሕ ዉጊያና የርዕሠ ጳጳሱ ተማፅዕኖ።ኒዮርክ-የዓለም መሪዎች ጥሪና የእስራኤል ሊባኖስ ዉጊያ
    12 min
  • የዓለም ዜና፤ መስከረም 13 ቀን 2017 ዓ.ም ሰኞ
    --ሶማሊያ ከግብፅ ከፍተኛ መጠን ያለዉ የጦር መሳሪያን ለሁለተኛ ጊዜ ተረከበች። ግብፅ ዜጎችዋ በቶሎ ከሶማሌላንድ እንዲወጡም ጠይቃለች።--ፓኪስታን ዉስጥ የኢትዮጵያንና የሩስያ ዲፕሎማቶችን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት ልዑኮች ከጥቃት መትረፋቸዉ ተመለከተ።--ሱዳን ባለፈው ነሐሴ ወር ብቻ በኮሌራ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 388 ከፍ ማለቱ ተነገረ። በወረርሽኙ ወደ 13,000 ሰዎች ተይዘዋል።--እስራኤል በሊባኖስ እያካሄደች ያለዉ ጥቃት 'አደገኛ መዘዝ' ያስከትላል ስትል ኢራን አስጠነቀቀች። በእስራኤል እና በሂዝቦላ ሚሊሻ መካከል እየጠነከረ የመጣው ዉጥረት ፤ በመካከለኛው ምስራቅ የሚታየዉን ቀዉስ እንዳያሰፋ ስጋት አሳድሯል።
    12 min
  • የመስከረም 10፣2017 የዓለም ዜና
    -የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በቅርቡ ያደረገዉ ጉባኤ፣ ዉሳኔዎቹና የባንክ ሒሳቡ በፍርድ ቤት ታገደ።-የእስራኤልና የሊባኖስ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን የሒዝቦላሕ ዉጊያ ዛሬ አይሎ ዉሏል።ሒዝቡላሕ ሰሜን እስራኤልን በሚሳዬል፣ እስራኤል ባንፃሩ የሊባኖስ ርዕሰ ከተማ ቤይሩትን በጦር ጄቶች ደብድበዋል።-የአዉሮጳ ሕብረት ለዩክሬን 35 ቢሊዮን ዩሮ ብድር ሰጠ።
    10 min
  • የመስከረም 8 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    በደቡብ ምዕራብ ዳርፉር ውስጥ የሱዳን ጦር ባካሄደው የአየር ጥቃት ከ40 በላይ ሰዎች መገደላቸው ተነገረ። ዩናይትድ ስቴትስ የሱዳን ተቀናቃኝ ኃይሎች በአስቸኳይ ለውይይትም እንዲቀመጡ ጠይቃለች።
    የዩናይትድ ስቴትስ ሰው አልባ አውሮፕላን የመን አቅራቢያ መከስከሱን ፔንታገን አረጋገጠ። የየመን ሁቲ ሚሊሺያዎች ባለፉት ቀናት በርካታ አውሮፕላኖችን መትተው መጣላቸውን አስታውቀው ነበር።
    ሊባኖስ ውስጥ በድምፅና መልእክት መቀበያ መሣሪያ ፍንዳታ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ማሻቀቡ እየተነገረ ነው።
    ማዕከላዊ አውሮጳን ከሁለት አስርት ዓመታት ወዲህ ያጥለቀለቀው አስከፊ የጎርፍ አደጋ ከሮማንያ እስከ ፖላንድ ከባድ ውድመት አስከትሏል።
    10 min
  • የዓለም ዜና፤ መስከረም 7 ቀን፤ 2017 ዓ.ም ሰኞ
    DW Amharic የካይሮ መንግሥት ህወሓት እና ኤርትራን ማደራደር እንደሚፈልግ ተመለከተ። ግብፅና ኤርትራ ትስስራቸዉን ለማጠናከር ወታደራዊ ትብብር እና የመረጃ ልውውጥ ስምምነት ሊፈፅሙ እንደሚችል የግብፅ የዜና ምንጮች ዘገቡ። በጎንደር ከተማ ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ በፋኖና በመንግስት ወታደሮች መካከል ውጊያ ሲካሄድ መዋሉን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ በኢትዮጵያና በሶማሊያ መካከል ቱርክ አንካራ ላይ ሊደረግ የታቀደው ሦስተኛ ዙር ዉይይት ለሌላ ጊዜ መተላለፉን የሶማልያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ተናገሩ። ደቡብ ሱዳን በጎረቤቷ ሱዳን በኩል ወደ ውጭ ሃገር የነዳጅ ምርትን ለመላክ እና እንደገና ለማስጀመር እየሰራች መሆኑ ተነገረ።
    11 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…