የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የጳጉሜ 2 ቀን 2016 ዓ/ም የዓለም ዜና
    Dw Amharic-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማረቆ ልዩ ወረዳ ዛሬ እኩለ ቀን አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት ማለፉ፣በአማራ ክልል ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ አድርገዋል በተባሉ 7ሺህ የሚጠጉ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መውሰዱ፣ አርብ ዕለት በዌስት ባንክ የተገደለችው ቱርካዊ-አሜሪካዊት ወጣት ግድያ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ መጠየቁ፣ሩሲያ በአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ላይ ገደብ እንደምትጥል መግለጿ እንዲሁም የዶናልድ ትራምፕ ክስ የሀገሪቱ ምርጫ እስኪጠናቀቅ ድረስ ብይኑ እንዲዘገይ መወሰኑን የዛሬው የዓለም ዜና የያዛቸው ርዕሰ ጉዳዮች ናቸው።
    13 min
  • የዓርብ ጳጉሜ 1 ቀን 2016 ዓ/ም የዓለም ዜና
    DW Amharic - በእስር ላይ የነበሩ ሰባት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ከፍተኛ ባለስልጣናት ከእስር መለቀቃቸው- በኢትዮጵያ በመጭው አዲስ ዓመት ሰላም እንዲሰፍን፣ ፍትሕና ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ መጠየቁ -የሱዳን ጦር ከፋኖ ታጣቂዎች ሸሽተው ወደ ሱዳን የገቡ 77 የኢትዮጵያ ወታደሮችን ትጥቅ ማስፈታቱን--በኬንያ በአንድ አዳሪ ትምህርት ቤት ውስጥ በደረሰ የእሳት አደጋ 17 ተማሪዎች መሞታቸውን- በሱዳን እርስ በእርስ የሚዋጉት ሁለቱም ኃይሎች የጦር ወንጀል ሊባል የሚችል ጥቃት ፈጽመዋል መባላቸው -በደቡብ ሱዳን ከ700 ሺህ በላይ ሕዝብ በጎርፍ መጎዳቱን የተሰኙ ርዕሰ ጉዳዮችን የዛሬው የዓለም ዜና አካቷል።
    10 min
  • የነሐሴ 30 ቀን 2016 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ጋብ ብሎ የነበረው ውጊያ ማገርሸቱን ነዋሪዎች ለዶቼ ቬለ ተናገሩ። ለቀናት ተኩስ እንዳልነበረ የገለጹት እማኞች ዛሬ ከቀትር በኋላ ከ11 ሰዓት ጀምሮ በከተማዋ የተለያየ አካባቢ ተኩስ መከፈቱን አመልክተዋል።
    ቻይና በቀጣይ ሦስት ዓመታት ለአፍሪቃ ሃገራት ከ50 ቢሊየን ዶላር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀቷን አስታወቀች።
    ከሱዳን ተፈናቅለው በኢትዮጵያ ተጠግተው ከነበሩ ስደተኞች 700 የሚሆኑት ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተነገረ።
    በጀመርኗ ሙኒክ ከተማ በዛሬው ዕለት ፖሊስ አንድ ተጠርጣሪን ተኩሶ መግደሉ ተነገረ።
    11 min
  • የነሐሴ 28፣2016 የዓለም ዜና
    -የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደና ከ-ኤርትራ የሚያደርገዉን በረራ አቋረጠ።የአየር መንገዱ የበላይ ኃላፊ እንዳሉት አየር መንገዳቸዉ በረራዉን ያቋረጠዉ ኤርትራ ባንክ የሚገኝ ገንዘቡ በመታገዱ ነዉ።የዉጪ ዲፕሎማቶች እንደሚሉት ግን አየር መንገዱ በረራዉን ያቋረጠዉ የአዲስ አበባና የአስመራ ግንኙነት ሲበዛ በመሻከሩ ነዉ።----የኢትዮጵያ መንግስት የሰዎችን መታገትና የሚደርስባቸዉን የመብት ጥሰት ለማስቆም ሁነኛ እርምጃ እንዲወስድ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በድጋሚ ጠየቀ።-60 ከመቶ የሚሆኑ የአፍሪቃ ወጣቶች ከየሐገራቸዉ መሰደድ እንደሚፈልጉ አንድ ጥናት አረጋገጠ።
    12 min
  • የነሐሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም የዓለም ዜና
    የፋኖ ታጣቂዎች ዛሬ የጠረፍ ከተማ የሆነችው መተማ ከተማን ተቆጣጥረው መዋላቸውን የከተማዋ ናዋሪዎች ለዶይቼ ቬሌ ገለጹ።
    የጀርመን ቀኝ ጽንፈኛ ፓርቲ በሁለት ፌደራል ግዛቶች በተካሄደው ምርጫ ያገኘው ስኬት በመራሄ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ አስተዳደር ላይ ጫና ማስከተሉ እየተነገረ ነው።
    ሩሲያ በዛሬው ዕለት የተጠናከረ የሚሳኤል ጥቃት በዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭና በሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች ላይ ከፈተች።
    በፓሪስ 2024 ፓራለምፒክ የሚሳተፉ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል እያስመዘገቡ ነው።
    11 min
  • የነሐሴ 25 ቀን 2016 ዓ.ም የዓለም ዜና
    *ኢትዮጵያ ፦ በአማራ ክልል ከፍተኛ ዝናብ ያስከተለው ጥፋት
    *ኬንያ፣ ከፍተኛ የኃይል መቆራረጥ ገጠማት
    *ቱኒዝያ፣ አደጋ ላይ የነበሩ 28 ስደተኞች ተረፉ
    *ጀርመን፤ ስድስት ሰዎች በስለት ተወግተው ቆሰሉ
    *እስራኤል፤ በጄኒን የሚካሄደው ከባድ ውጊያ ቀጥሏል
    *ኢትዮጵያ ፤ በዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና 2ኛ ደረጃ ላይ
    9 min
  • የነሐሴ 24 ቀን 2016 ዓ.ም የዓለም ዜና
    በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማረቆ ልዩ ወረዳ ማንነትን መሠረት ያደረገ ነው በተባለ ጥቃት አራት የአንድ ቤተሰብ አባላትን ጨምሮ ሰባት ሰዎች መገደላቸው ተሰማ።
    ኢትዮጵያ ሶማሊላንድ ውስጥ ለሚገኘው ቆንስላ ጽሕፈት ቤቷ አዲስ አምባሳደር ሾመች።
    የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የኢትዮጵያን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ ከ3,600 በላይ የሕግ ታራሚዎችን በይቅርታ መልቀቁን አስታወቀ። ከታሰሩ የኦነግ አባላት የተለቀቀ የለም።
    የቀድሞው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ፕሮፌሰር እንድርያስ እሸቴ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ትናንት ሐሙስ ነሐሴ 23 ቀን፣ 2016 ዓ.ም ማረፋቸውን ዩኒቨርስቲው አስታወቀ።
    10 min
  • የዓለም ዜና፤ ነሐሴ 23 ቀን፤ 2016 ዓ.ም ሐሙስ
    አርስተ ዜና፤
    --የአውሮጻ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሃላፊ ጆሴፍ ቦሬል በእስራኤል ሚኒስትሮች ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ሃሳብ ለማቅረብ እየሰሩ እንደሆነ ተመለከተ።
    --በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጢ ዞን ጎርፍ ከ6ሺህ በላይ ነዋሪዎችን አፈናቀለ። የጎርፍ አደጋው መንሥኤ በአካባቢው ከተገነባ የመስኖ ግድብ ነዉ ተብሏል። በሌላ በኩል በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ በናዳ ለተጎዱ እርዳታ እየተጠበቀ ነዉ። --ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት «ሂውማን ራይትስ ዋች» በሱዳን ከ16 ወራት በላይ በዘለቀዉ የእርስ በእርስ ግጭት፤ ሁለቱንም ተፋላሚ ወገኖች ፤ የጦርነት ወንጀል ፈፅመዋል ሲል ከሰሰ።
    11 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…