የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • DW Amharic የነሐሴ 9 ቀን 2016 የዓለም ዜና
    የጋምቤላ ምክር ቤት ዓለሚቱ ኡሞድን በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት የክልል ፕሬዝደንት አድርጎ ሾመ። ከኢትዮ- ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር 32 የጭነት ሎኮሞቲቮች 17ቱ አይሰሩም ተባለ። በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ የግብረ-ሠናይ ሠራተኛ ማንነቱ ባልታወቀ ወንጀለኛ ቡድን ተገደሉ። የ15 ዓመቱ ሔመን በቀለ የታይም መጽሔት የዓመቱ ምርጥ ታዳጊ ተብሎ ተመረጠ። የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት የአድሬ የድንበር መሸጋገሪያን ለሦስት ወራት ሊከፍት ነው። በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የጦጣ ፈንጣጣ 548 ሰዎች መግደሉ ተገለጸ። በጋዛ ተኩስ ለማስቆም የታቀደው የዶሐ ድርድር ያለ ሐማስ ተሳትፎ ተጀመረ።
    9 min
  • DW Amharic የነሐሴ 8 ቀን 2016 የዓለም ዜና
    ሶማሌላንድ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያን የምታሸማግለው ቱርክ ገለልተኛ አይደለችም ስትል ከሰሰች። የሶማሌላንድ ክስ የተደመጠው በአንካራ ለሁለተኛ ጊዜ የተካሔደው የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ውይይት ያለ ውጤት ከተበተነ በኋላ ነው። የሱዳንን ጦርነት ለማብቃት ያለመ ድርድር የብሔራዊው ጦር አዛዥ ጄነራል አብደል ፋታኅ አል-ቡርኻን በሌሉበት ተጀመረ። ግብጽ እና ሶማሊያ የወታደራዊ ትብብር ፕሮቶኮል ሥምምነት ተፈራረሙ። በጋዛ ውጊያ የገጠሙ ኃይሎች ተኩስ እንዲያቆሙ ለማድረግ ያቀደ ድርድር በቃጣር ሊካሔድ ነው። ጀርመን የኖርድ ስትሪም የጋዝ ማስተላለፊያን በማፈንዳት የጠረጠረችውን ግለሰብ ለመያዝ የእስር ማዘዣ አወጣች።
    10 min
  • የነሐሴ 6 ቀን 2016 የዓለም ዜና
    የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት የህወሓት “የሕግ ሰውነት፤ አግባብ ባለው ሕግ እና በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሠራር መሠረት ብቻ እልባት ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ” እንደሆነ አስታወቀ። የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሀገሮቻቸው መካከል የተቀሰቀሰውን ውጥረት ለማብቃት በቱርክ አሸማጋይነት በአንካራ ተገናኙ። በዩጋንዳ በደረሰ የቆሻሻ መደርመስ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 23 ደረሰ። በጋዛ በአስቸኳይ ተኩስ እንዲቆም ጀርመን፣ ፈረንሳይ እና ዩናይትድ ኪንግደም ጥሪ አቀረቡ። ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ወደ ሩሲያ ግዛት የገቡ የዩክሬን ወታደሮችን የሀገራቸው ጦር እንዲያባርር ትዕዛዝ ሰጡ
    11 min
  • የአርብ ነሐሴ 3 ቀን 2016 ዓ/ም የዓለም ዜና
    በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ግንደወይን ከተማ በደረሰ የመኪና አደጋ ወንዝ ውስጥ የሰጠሙ ሰዎች አስከሬን የማፈላለግ ስራ መቀጠሉ ተገለፀ።
    አቶ ጌታቸው ረዳ፤ ህወሓት አካሂዳለሁ ካለው ጠቅላላ ድርጅታዊ ጉባኤ ራሳቸውን ማግለላቸውን አስታወቁ።
    ሊባኖስ ውስጥ ያለው ሁኔታ የሚባባስ ከሆነ በተለይ ችግር ያለበት አካባቢ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ለማውጣት ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ።
    የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሾፍቱ ከተማ አከባቢ ግዙፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ሊያስገነባ መሆኑን አስታወቀ፡፡
    የሱዳን መንግሥት ከአሜሪካ ጋር ለመመካከር የልዑካን ቡድኑን ወደ ጅዳ እንደሚልክ ገለፀ።
    10 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…