የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • DW Amharic የዓለም ዜና፤ ነሐሴ 2 ቀን 2016 ዓ.ም.ሃሙስ
    --የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን “የፕሬዚዳንቱ የሕይወት ዘመን ሽልማት” ተበረከተለት፡፡
    --በኢትዮጵያዋ ሶማሌ ክልል በዋቢ ሸቤሌ ወንዝ እስከ ገደፉ ሞልቶ በተከሰተ ጎርፍ ወደ ሦስት ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ከመኖርያ ቀዬያቸው መፈናቀላቸውን የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ።
    --የተለያዩ የኤርትራ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በሥልጣን ላይ ያለውን አምባገነን ያሉትን መንግሥት ለመታገል የጋራ ጥምረት መመስረታቸውን አስታወቁ።
    --ኬንያ የወጣቶች ተቃውሞ ዛሬ በመዲናዋ ናይሮቢ በርካታ ወጣቶች በተሳተፉበት ዳግም መቀስቀሱ ተነገረ።
    12 min
  • የረቡዕ ነሐሴ 1 ቀን 2016 ዓ.ም.የዓለም ዜና
    የነሐሴ 1 ቀን 2016 ዓ.ም.አርዕስተ ዜና
    በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ከሚኖሩበት መጠለያ ጣቢያዎች ወጥተው በመንገድ ዳር ከሚኖሩ የሱዳን ተፈናቃዮች መካከል አንዳንዶቹ ባለፈው ቅዳሜ ጥቃት እንደተፈፀመባቸው ተናገሩ።
    እስራኤል፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ብሪታንያ ፣ጀርመን የአውሮጳ ኅብረትና ሌሎች በአሸባሪነት የፈረጁት ታጣቂ ቡድን ሐማስ ያህያ ሲንዋርን የቡድኑ ከፍተኛ መሪ አድርጎ መረጠ።
    ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሜዳሊያ ሊያሸንፉ እንደሚችሉ የተገመተበት የወንዶች የሦስት ሺህ ሜትር መሰናክል የፍጻሜ ውድድር ዛሬ ምሽት 4:40 ይደረጋል። በውድድሩ የክብረ ወሰን ባለቤቱ ለሜቻ ግርማ ሳሙኤል ፍሬው እና ጌትነት ይሳተፋሉ።
    12 min
  • የሐምሌ 30 ቀን 2016 የዓለም ዜና
    *በመካከለኛው ምስራቅ ያየለው የጦርነት ስጋት
    *ኢትዮጵያ፦ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የፍትህ ጥያቄ
    *75 የፖሊስ አባላትን ገድለዋል የተባሉ ተፈረደባቸው
    *አቶ ታዬ ደንደዓ ከተመሰረተባቸው ሶስት ክሶች በሁለቱ ነጻ ተባሉ
    *ሱዳን፤ የስደተኞች መጠለያ ከአየር ጥቃት ደረሰ
    *ሩሲያ ወታደሮች ከዮክሬይን ጋር ወደሚያዋስናት ድንበር ላከች
    11 min
  • የዓለም ዜና፤ ሐምሌ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ሰኞ
    -የባንግላዴሽ የጠ/ሚ ሼክ ሃሲና በህዝባዊ ትግል ከስልጣን ለቀቁ። የ 76 ዓመትዋ ሃሲና፤ ምናልባትም ወደ ህንድ ሳይሰደዱ አልቀረም። -በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ በመሬት ናዳ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ በአደጋዉ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ሳይጨምር አይቀርም።-የደቡብ አፍሪቃ ፖሊስ ጆሃንስበርግ ዉስጥ ታፍነዉ ተይዘዉ የነበሩ 90 ኢትዮጵያዉያን ስደተኞችን ነፃ አስለቀቀ። ፍልሰተኞቹን ያፈኑት ሁለት የሰዎች አዘዋዋሪ ተጠርጣሪዎች ተይዘዋል።-ማሊ ከዩክሬይን ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋረጠች። የማሊ ዩክሪን አማፅያኑ ባደረሱት ጥቃት እጇ አለት በሚል ነዉ። ዩክሬይን የማሊ እርምጃን ኮንናዋለች።
    11 min
  • የአርብ ሐምሌ 26 ቀን 2016 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የአርብ ሐምሌ 26 ቀን 2016 ዓም አርዕስተ ዜና
    ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ በአማራ ክልል ከመንግሥት ጋር ከሚዋጉ አንዳንድ ቡድኖች ጋር ውይይት መጀመሩን ለመጀመሪያ ጊዜ መናገራቸው በክልሉ ነዋሪዎች አስተያየት እየተሰጠበት ነው። አንዳንድ የክልሉ ነዋሪዎች ሃሳቡን የተቀደሰ ሲሉ ፣ሌሎች ደግሞ ጥርጣሬ ገብቷቸዋል።
    በግጭት በተመሰቃቀለው በዳርፉር በሚገኘው ዘምዘም መጠለያ ኮሌራና ሌሎች መሰል በሽታዎች እንዳይሰፋፉ አስግቷል።
    ረቡዕ ቴህራን ውስጥ በአየር ጥቃት የተገደሉት የሃማስ ከፍተኛ መሪ የኢስማኤል ሀኔይ አስከሬን ሽኝትና ስርዓተ-ቀብር በስደት ይኖሩበት በነበረው በዶሀ በከፍተኛ የጸጥታ ጥበቃ ዛሬ ተፈጸመ።
    11 min
  • የሐምሌ 25 ቀን 2016 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    በአዲስ አበባ ከተማና ኦሮሚያ ክልል የብር አቅም መዳከምን ተከትሎ በሸቀጦች ላይ ዋጋ ጭማሪ ያደረጉ በርካታ የንግድ ድርጅቶች መዘጋታቸው ተገለጸ።
    በጸጥታ ችግር ምክንያት ለፈተና በሄዱበት ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ለሁለት ሳምንታት ያህል መቆየት የተገደዱት ከ400 በላይ ተማሪዎች ትናንት ማምሻውን ወደ ቤተሰቦቻቸው መመለሳቸው ተሰማ።
    የናይጀሪያ ፖሊስ በሀገሪቱ የተባባሰውን የዋጋ ንረትና የአስተዳደር ችግር በመቃወም አደባባይ ከወጡ ሰልፈኞች ጋር ፍጥጫ ገጥሟል።
    ትናንት ለተገደሉት የሃማሱ መሪ በኢራን ብሔራዊ የአስክሬን ሽኝት ሥረዓት ተከናወነ። አዲሱ የኢራን ፕሬዝደንት መንግሥታቸው ለሃማስ የሚያደርገው ድጋፍ ይጨምራል ብለዋል።
    11 min
  • የሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ/ም የዓለም ዜና
    DW Amharic
    -በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የሟቾችን አስክሬን የማፈላለጉ ሥራ ማብቃቱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት አስታወቀ ፡፡-የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የህወሃት አመራሮችን ኮነነ። ጊዚያዊ አስተዳደሩ የህዝባዊ ወያነ ሀርነት ትግራይ /ህወሓት/ አመራሮችን የኮነነው፤ በሙስና እና በተደራጀ የማዕድን የመሬት ዘረፋ ፣ በመሳሪያ ንግድ እና በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ነው።-የሱዳን ወታደራዊ መሪ ጄኔራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን የግድያ ሙከራ ተፈጸመባቸው።-የሃማስ መሪ እስማኤል ሃኒዬህ ኢራን ውስጥ ከጠባቂያቸው ጋር ተገደሉ።
    12 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…