Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
July 29, 2024የሐምሌ 22 ቀን 2016 የዓለም ዜና* በሲዳማ ክልል በተከሰተ የመሬት መንሸራታት 11 ሰዎች ሞቱ* የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በውጭ ምንዛሪ ላይ ማሻሻያ አደረገ*የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ፀጥታ ምክር ቤት ውሳኔዎች አስተላለፈ*ፆታዊ ጥቃት እና የሰብዓዊ መብት ጥሰት በሱዳን*እስራኤል፤ በሂዝቦላህ ላይ ወታደራዊ ርምጃ ለመውሰድ ወሰነች* ፈረንሳይ፤ በኢንተርኔት አገልግሎት መስመሮች ላይ ጥቃት ተፈፀመ11 minPlay
July 25, 2024DW Amharic የዓለም ዜና፤ ሐምሌ 17 ቀን 2016 ዓ.ም--በየመን ባህር ዳርቻ 45 ስደተኞችን አሳፍራ ስትቀዝፍ የነበረች ጀልባ ሰምጣ አራት የተረፉ ሰዎች ብቻ መገኘታቸዉ ተነገረ።--በጎፋ ዞን የመሬት መንሸራተት አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 500 ሊደርስ እንደሚችል ተባለ።--ህወሓት ሊያደርገው ያቀደው 14ተኛ ጉባኤ በፓርቲው ቁጥጥር ኮምሽን ተቃውሞ ገጠመዉ። ህወሓት በ50 ዓመት ታሪኩ አጋጥሞት በማያውቅ ፈተና ውስጥ መሆኑም ተመልክቷል። --የኤርትራ መንግሥት የአቪየሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ ከአዲስ አበባ ወደ አስመራ በረራ እንዳያደርግ ባገደበት ውሳኔ ላይ ለመነጋገር እና ለመመካከር ሙከራ እያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ።9 minPlay
July 22, 2024የሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም. የዓለም ዜናየሰኞ ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በደረሰ የመሪት ናዳ የ30 ሰዎች ሕይወት አለፈ። በአደጋው የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከዚህም ሊጨምር ይችላል የሚል ሥጋት አለ።በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሃድያ ዞን የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከሦስት መቶ በላይ ሠራተኞች ካለፈው አርብ አንስቶ የሥራ ማቆም አድማ ላይ ናቸው። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከጎርጎሮሳዊው 2024ቱ የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ ትናንት ራሳቸውን ማግለላቸውን ካሳወቁ በኋላ ዴሞክራቶች ባይደን በምርጫው እንዲወዳደሩ ለመረጧቸው ለምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሀሪስ ድጋፋቸውን እየገለጹ ነው።11 minPlay
July 20, 2024የሐምሌ 13 ቀን 2016 የዓለም ዜናህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እንደ አዲስ ፓርቲ ለመመዝገብ ጥያቄ እንዳላቀረበ ቃል አቀባዩ አቶ አማኑኤል አሰፋ ተናገሩ። በአማራ ክልል የሚገኙ ሱዳናውያን ስደተኞችን ወደ ሌላ መጠለያ በማዘዋወር አውላላ እና ኩመር ጣቢያዎች በሒደት ሊዘጉ ነው። የኬንያ ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ የመንግሥታቸውን ካቢኔ አስራ አንድ አባላት ይፋ አደረጉ። ናይጄሪያ “በርካታ እና ተደጋጋሚ ጥፋቶች” ፈጽሟል ያለችውን የፌስቡክ እና የዋትስአፕ ባለቤት ሜታ ኩባንያ 220 ሚሊዮን ዶላር ቀጣች። የእስራኤል ኃይሎች ዛሬ ቅዳሜ በጋዛ ሠርጥ የተለያዩ አካባቢዎች በፈጸሟቸው ድብደባዎች ቢያንስ 30 ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የጤና ባለሥልጣናት አስታወቁ።9 minPlay