የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የዓለም ዜና፤ ሐምሌ 12 ቀን 2016 አርብ
    --መቀመጫዉን ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ያደረገዉ፤ የሳይበር ደህንነት ኩባንያ ባካሄደዉ የተሳሳተ የይዘት ማሻሻያ በመላው ዓለም ከፍተኛ መስተጓጎል አስከተለ። የአዉሮፕላን በረራዎች፤ የንግድ ተቋማት እና ሌሎች ስራዎች ለሰዓታት ተስተጓጎለዉ ነበር። --የኬንያ ፍርድ ቤት ፖሊስ በዋና ከተማዋ ናይሮቢ እና አካባቢዋ ላይ ፀረ-መንግስት ተቃውሞዎችን ለማገድ የወሰነዉን እርምጃ፤ ፍርድ ቤት አገደ።--የቀድሞ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ፤ በእጩነት መመረጣቸዉን በሙሉ ፍላጎት ተቀበሉ። በሌላ በኩል የቀድሞዉ ባራክ ኦባማ እና ናንሲ ፔሎሲ፤ ጆ ባይደን ለዳግም ምርጫ ለመወዳደር በቂ አቅም የላቸዉም ሲሉ ጥርጣሪያቸዉን ገልፀዋል።
    10 min
  • የሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓም አርዕስተ ዜና
    -«መንግስት የዜጎችን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ሕጋዊ ግዴታውን ሊወጣ ይገባል!» ሲል ኢሰመጉ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳሰበ ።«በዜጎች ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎች፣ እገታና አፍኖ መሰወር በሀገራችን በአሳሳቢ ደረጃ እየተስፋፋ ያለ ጉዳይ» ነው ያለው ኢሰመጉ ለመፍትኄው ግን የሚመለከታቸው አካላት ዳተኛ መሆናቸውን ጠቁሟል ።
    -ሳዑዲ አረብያ ዛሬ በአደንዛዥ እጽ ዝውውር የተወነጀሉ ሁለት ሰዎችን በሞት መቅጣትዋን የሀገሪቱ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
    የአውሮጳ ኅብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር ኢርዙላ ፎን ዴር ላየን ዛሬ ለሁተኛ የሥልጣን ዘመን ተመረጡ።
    10 min
  • የዓለም ዜና፤ የሐምሌ 9 ቀን 2016 ማክሰኞ
    የዓለም ዜና፤ የሐምሌ 9 ቀን 2016 ሰኞ
    አርዕስተ ዜና
    --የዩናይትድ ስቴትሱ ሪፐብሊካን ፓርቲ ዶናልድ ትራምፕን ለፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዲፎካከሩ በይፋ መረጠ። ትራምፕ በበኩላቸዉ የአንድ ወቅት ተቃዋሚያቸውን ተጣማሪያቸው አድርገው መረጠዋል።
    --በኬንያ ዛሬ ፕሬዝዳንት ሩቶ ስልጣን እንዲለቁ የሚጠይቁ ተቃዋሚ ሰልፈኞችን ዳግም ፖሊስ በአስለቃሽ ጢስ በተነ።
    --በሩዋንዳዉ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ፤ ፖል ካጋሜ በከፍተኛ ድምጽ ማሸነፋቸውን የሃገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ይፋ ባደረገዉ የቅድመ ቆጠራ ዉጤት አስታወቀ።
    --የሃንጋሪ ጠ/ሚ ቪክቶር ኦርባን የሚያደርጓቸውን አወዛጋቢ ጉዞዎች ተከትሎ የአዉሮጳ ህብረት ምክር ቤት እገዳ አስተላለፈ።
    10 min
  • የሰኞ ሐምሌ 8 ቀን 2016 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የሰኞ ሐምሌ 8 ቀን 2016 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    -በአማራ ክልል ለአንድ ዓመት ያህል ተቋርጦ የቆየው የኢንተርኔት ሞይል ዳታ ትናንት በአንዳንድ ከተሞች አገልግሎት መስጠት መቀጠሉን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ የአንዳንድ ከተሞች ነዋሪዎች አገልግሎቱ በተመረጡ ስልኮች ብቻ ነው የሚሰራው ብለዋል።
    -የኬንያ ፖሊስ በተደጋጋሚ ሰዎችን ሲገድል የነበረና ድርጊቱንም አምኗል ያለውን አ,ረመኔ ማሰሩን አስታወቀ።
    /አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ዳኛ ባለፈው ቅዳሜ ከግድያ ሙከራ የተረፉት የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዚህ ቀደም ምሥጥራዊ የመንግሥት ሰነዶች በመያዝ የተመሰረተባቸውን ክስ ውድቅ አደረጉ።
    11 min
  • የሐምሌ 7 ቀን 2016 የዓለም ዜና
    በዶናልድ ትራምፕ ላይ ተኩስ የከፈተው ተጠርጣሪ ተሽከርካሪ ውስጥ ፈንጂዎች መገኘታቸውን የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ። ከግድያ ሙከራ ያመለጡት ትራምፕ አሜሪካውያን በጋራ እንዲቆሙ ጥሪ ሲያቀርቡ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በተፎካካሪያቸው ላይ የተሞከረውን ግድያ አውግዘዋል። እስራኤል በማዕከላዊ ጋዛ በሚገኝ ትምህርት ቤት ላይ ዛሬ እሁድ በፈጸመችው ጥቃት በርካታ ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የጋዛ የጤና ሚኒስቴር ባለሥልጣናት አስታወቁ። በጀርመን ባደን ቩተንበርግ ግዛት በምትገኘው ላውትሊንገን ከተማ አንድ ግለሰብ ሁለት ሰዎች ገድሎ ራሱን አጠፋ።
    7 min
  • የሐምሌ 5 ቀን 2016 ዓ.ም የዓለም ዜና
    ኻርቱም፤ የሱዳን ፖሊስ የውጪ ዜጎች ከኻርቱም እንዲወጡ ማዘዙ
    ናይሮቢ፤ የኬንያ ፖሊስ አዛዥ ሥራቸውን ለቀቁ
    ናይሮቢ፤ የኬንያ ወጣቶች ተቃውሟቸውን ሊቀጥሉ እንደሚችሉ ማስጠንቀቃቸው
    ጄኔቫ፤ የሱዳን ተቀናቃኝ ኃይላት ለውይይት ጄኔቫ
    ሞስኮ፤ ሩሲያ በኔቶ ጉባኤ የባይደንን ስህተት ዓለም ልብ ይበልልኝ ማለቷ
    ካታማንዱ፤ ኔፓል ውስጥ የደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ
    10 min
  • የሐምሌ 3 ቀን 2016 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የሐምሌ 3 ቀን 2016 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    ሱዳን የሚገኙ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያና የኤርትራ ስደተኞች የከፋ አደጋ ላይ ናቸው ሲል ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ሂዩመን ራይትስ ዋች አሳሰበ። ከመካከላቸው ገዳሪፍ ያሉ ከ40 ሺህ በላይ የኢትዮጵያ ስደተኞች ይገኙበታል ።
    ከግንቦት አንስቶ በከፍተኛ ባለሥልጣናት ደረጃ በደቡብ ሱዳን መንግስትና በተቃዋሚዎች ተወካዮች መካከል በኬንያ ሲካሄድ የቆየው የሰላም ንግግር ሊጠናቀቅ ሲል ተሰናከለ።
    የኔቶ አባል ሀገራት መሪዎች ጉባኤ ላይ ዩናይትድ ስቴትስና ሌሎች የኔቶ አባል ሀገራት ለዩክሬን የአየር መከላከያ ስርዓት ለመለገስ ቃል ገቡ።
    11 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…