የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • DW Amharic የሰኔ 22 ቀን 2016 የዓለም ዜና
    የኢትዮጵያ መንግሥት እና የፋኖ ታጣቂዎች የሚያደርጉትን “የርስ በርስ ጦርነት” አቁመው ድርድር እንዲጀምሩ በአማራ ክልል የተቋቋመ የሰላም ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ። “የርስ በርስ ጦርነቱን በድርድር ለመፍታት ፈቃደኛ ነኝ” ያለው የኢትዮጵያ መንግሥት “ብዙ አደረጃጀት እና መሪ” አላቸው ያላቸው የፋኖ ታጣቂዎች “ለመደራደር አንድ መሆን አለባቸው” በማለቱ ምክር ቤቱ መቋቋሙን ተገልጿል። • የግብረ-ሰናይ ድርጅቶች የሱዳን “ሰው ሰራሽ ረሐብ” ከተፈራው የከፋ ሊሆን እንደሚችል አስጠነቀቁ። በኬንያ ተቃውሞ ቢያንስ 30 ሰዎች መገደላቸውን ሒውማን ራይትስ ዎች አስታወቀ።
    8 min
  • የሰኔ 21 ቀን 2016 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ምሥራቅ ቦረና በሚል አዲስ ዞን ስር የሚተዳደረው ጎሮዶላ ወረዳ እየተጓተተ በሚከፈው ደሞዝ መቸገራቸውን ሠራተኞች አመለከቱ። ሠራተኞቹ እንደሚሉት ከሚያዚያ ወር ወዲህ ደሞዝ አላገኙም።
    የየመን ሁቲ አማጽያን ዛሬም በቀይ ባሕር ላይ ስትጓዝ በነበረች በመርከብ ላይ አምስት ሚሳኤል መተኮሳቸው ተነገረ። የብሪታንያ የባሕር ንግድ ኮርፖሬሽን ዛሬ እንደገለጸው በመርከቧ ላይ ጉዳት አልደረሰም።
    የአውሮጳ ሕብረት ሃገራት መሪዎች ለሕብረቱን ኮሚሽን ፕሬዝደንትነት ዑርዙላ ፎንደር ሌይንን ለሁለተኛ ጊዜ በይፋ ሰየሙ። ጉባኤው የኢስቶኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ካያ ካሌስንም ለሕብረቱን የውጭ ጉዳይ ኃላፊነት መርጧል።
    9 min
  • የሐሙስ ሰኔ 20 ቀን 2016 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የሐሙስ ሰኔ 20 ቀን 2016 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ህዝባቸው የተቃወመው የታክስ ጭማሪ ሕግ ላይ ፊርማቸውን እንደማያኖሩ ቢያሳውቁም ተቃዋሚዎች ዛሬም አደባባይ ወጥተው ነበር። በናይሮቢ የንግድ ማዕከል የተሰባሰቡ በርካታ ተቃዋሚዎችን ፖሊስ በፕላስቲክ ጥይቶችና በአስለቃሽ ጢስ በትኗል።
    በሱዳን 755 ሺህ ሰዎች ለረሀብ መጋለጣቸውን ዓለም አቀፍ አጥኚዎች ዛሬ ይፋ ያደረጉት አንድ ዘገባ አስጠነቀቀ። ረሀቡ የሚያሰጋው በ14 የሱዳን አካባቢዎች ነው።
    ከከሸፈው የትናንትናው የቦሊቭያ መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ በኋላ በርካታ ወታደራዊ መኮንንኖች መታሰራቸውን አንድ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣን ተናገሩ።
    10 min
  • የሰኔ 17 ቀን 2016 ዓም የዓለም ዜና
    የሰኔ 17 ቀን 2016 ዓም ዐርእስተ ዜና
    የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በእነ ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራ እና ሌሎች በሚገኙበት መዝገብ የተከሰሱ እንዲለቀቁ ወሰነ።
    የአውሮጳ ኅብረት በሱዳኑ ጦርነት ለተፈጸሙ የተለያዩ ወንጀሎች ተጠያቂ ባላቸው ስድስት ሱዳናውያን ላይ ዛሬ ማዕቀብ ጣለ። ስድስቱ ሱዳናውያን በሱዳን ውጊያ የሚያካሂዱት የመንግሥት ጦርና የፈጥኖ ደራሹ ኃይል አመራሮች መካከል ናቸው።
    በሄይቲ የተስፋፋውን የወሮበሎች አመጽ ለመከላከል በሀገሪቱ ይሰማራሉ ከተባሉት የየኬንያ ፖሊሶች የመጀመሪያዎች ወደዚያውሊሄዱ ነው ተባለ። ወደ ሄይቲ የሚጓዙት ነገ ነው።
    12 min
  • DW Amharic የሰኔ 16 ቀን 2016 የዓለም ዜና
    በቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ ሶማሌ፣ አፋር እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ለ6ኛው ሀገር አቀፍ የቀሪ እና የድጋሚ ምርጫ ነዋሪዎች ድምጽ ሲሰጡ ዋሉ። ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ መንግሥታቸው ተግባራዊ በሚያደርገው የግብር ጭማሪ ላይ በኬንያ ሀገር አቀፍ ተቃውሞ ካካሔዱ ወጣቶች ጋር ለመነጋገር ፈቃደኛ መሆናቸውን አስታወቁ። የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ዮቭ ጋላንት ከመስከረም 26 ቀን 2016 ጀምሮ በጋዛ ሲካሔድ በቆየው ውጊያ ላይ “ወሳኝ” ለተባለ ንግግር ወደ አሜሪካ አቀኑ። የኬንያ ኃይሎች ማክሰኞ በወሮበሎች ወደምትታመሰው ሔቲ እንደሚዘምቱ የሀገሪቱ መንግሥት እና የፖሊስ የመረጃ ምንጮች ተናገሩ። በሩሲያ እና ዩክሬን ጥቃቶች ሰዎች ተገደሉ
    9 min
  • የሰኔ 14፣ 2016 የዓለም ዜና
    -ለኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበዉ «ንብረት የማስመለስ ረቂቅ አዋጅ» ዉጪ በሚኖሩ ኢትዮጵያዉንና ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን ላይ ችግር የሚፈጥር ከሆነ ከአዋጁ አርቃቂዎች ጋር እንደሚነጋገርበት የዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር አስታወቀ።-ምዕራባዊ ሱዳን ዳርፉር ግዛት ዉስጥ ለረሐብ ለተጋለጠዉ ሕዝብ ተጨማሪ የምግብ ርዳታ ማከፋፈሉን የዓለም ምግብ ድርጅት አስታወቀ።-የእስራኤል ጦር ከደቡብ ጋዛን ከሰሜን ደቡባዊ ሊባኖስን መደብደቡን ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ።የሊባኖሱ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን ሒዝቡላሕም ሰሜናዊ እስራኤል በሚሳዬል መደብደቡን አስታዉቋል።
    12 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…