የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • DW Amharic የሰኔ 2 ቀን 2016 የዓለም ዜና
    በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጉዳት የደረሰበት በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ የሚገኘው አጼ ዮሐንስ አራተኛ ኤርፖርት ሥራ ጀመረ። በሶማሊያ ጋልጋዱድ ግዛት በተፎካካሪ ጎሳዎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት ቢያንስ 45 ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች 60 መቁሰላቸውን ባለሥልጣን ተናገሩ። እስራኤል አራት ታጋቾች ባስለቀቀችበት እና በስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ባካሔደችው ወታደራዊ ዘመቻ የተገደሉ ፍልስጤማውን ቁጥር ወደ 274 ማሻቀቡን የጋዛ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። አውሮፓውያን በአኅጉራዊው ምክር ቤት የሚወክሏቸውን ሕግ አውጪዎች ለመምረጥ ድምጽ ሲሰጡ ዋሉ። የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለሦስተኛ ተከታታይ የሥልጣን ዘመን ቃለ-መሐላ ፈጸሙ።
    11 min
  • የሰኔ 30፣ 2016 የዓለም ዜና
    -ሶማሊያ የሠፈረዉ የኢትዮጵያ ሠራዊት የወደፊት ተልዕኮን የሚመለከት መልዕክት ኢትዮጵያ በይፋ እንዳልደረሳት የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር አስታወቀ።ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር ያደረገችዉን ዉል ካልሰረዘች የኢትዮጵያ ጦር ከሶማሊያ እንደሚወጣ የሶማሊያ ሁለት ባለሥልጣናት ባለፈዉ ሰኞ አስታዉቀዉ ነበር።-የኢትዮጵያ የሚንስትሮች ምክር ቤት ለመጪዉ የበጀት ዓመት ወደ አንድ ትሪሊዮን ብር መደበ።በሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ወቅት የናትሴ ጀርመንን ድል ያደረጉት የተባባሪ ሐገራት ጦር ኖርማንዴይ ፈረንሳይ የገባበት 80ኛ ዓመት ታሰበ።
    12 min
  • የግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ ከታሰሩ ከ 80 በላይ ሰዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ። ዛሬ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ከቀረቡት ውስጥ ጋዜጠኞች፣ የቤተ ክርስትያን ሰዎች እና ፖለቲከኞች ይገኙበታል ተብሏል።
    የዘንድሮው የዶቼቬለ የንግግር ነጻነት ሽልማት ለሩስያዊቷ ዩልያ ናቫልናያና ሟቹ ባለቤታቸው አሌክሲ ናቫልኒ ለመሠረቱት በምህፃሩ FBK ለተባለው ፀረ ሙስና ድርጅታቸው ዛሬ ተሰጠ።
    አንድ «አማራጭ ለጀርመን» የተባለው የጀርመን ፓርቲ ፖለቲከኛ በደቡብ ምዕራብ ጀርመንዋ በማንሀይም ከተማ ትናንት ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ፓርቲያቸውና ፖሊስ አስታወቁ።
    11 min
  • የዓለም ዜና፤ ግንቦት 27 ቀን 2016 ዓ.ም ማክሰኞ
    DW Amharic
    --ኢትዮጵያ ከደቡብ ኮሪያ 1 ቢሊዮን ዶላር ለመበደር የሚያስችላት ዉል ተፈራረመች። ዛሬ በተጀመረዉ የደቡብ ኮሪያና የአፍሪቃ የመሪዎች ጉባኤ ላይ 30 መሪዎችን ጨምሮ የ48 የአፍሪቃ ሐገራት ባለሥልጣናት ተገኝተዋል።
    --ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የተፈራረመችዉን የወደብና ዕዉቅና የመስጠት የመግባቢያ ስምምነት ካልሰረዘች ሶማሊያ የሠፈሩ የኢትዮጵያ ወታደሮችን ከሀገሯ እንደምታስወጣ ሞቃዲሾ አስታወቀች።
    --በደቡባዊ ጀርመን ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ መድረሱን ተከትሎ፤ ከድንገተኛ ጎርፍ ከለላ ለማግኘት እና ቅድመ ጥንቃቄ ለማድረግ እንዲያስችል ወጪያቸዉን እንዲያሳድጉ ጥሪ ቀረበ።
    14 min
  • የአርብ ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም የዓለም ዜና
    አርዕስተ ዜና
    የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ካቢኔ ዛሬ ወደ ፓርላማ የመራው የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ማሻሻያ ህወሓት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሕጋዊ ሆኖ እንዲመዘገብ መንገድ የሚከፍት ነው።
    በደቡብ አፍሪቃው ምርጫ የድምጽ ቆጠራ ኤ ኤን ሲ ከ50 በመቶ በታች ድምጽ ማግኘቱ ከታወቀ በኋላ ሌሎች ፓርቲዎች ዛሬ የጥምረት ንግግር ለማካሄድ ዝግጅት መጀመራቸው ተሰማ ።
    የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቀረቡባቸው 34 ክሶች በሙሉ ጥፋተኛ በመባላቸው ላይ የተለያዩ መንግስታትና የፓርቲዎች መሪዎች አስተያየቶች እየተሰጡ ነው።
    12 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…