የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • .የሰኔ 10 ቀን 2016 ዓ.ም የዓለም ዜና
    DW Amharic
    --ዓመታዊዉ የዶቼ ቬለ የመገናኛ ብዙኀን መድረክ "መፍትሄዎችን መጋራት" በሚል መሪ ቃል ዛሬ ሰኔ 10 ቀን 2016 ዓ/ም ተጀመረ።በጀርመኗ ቦን ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ መድረክ፤የዶቼ ቬለ ዋና ዳይሬክተር ፒተር ሊንቡርግ እና የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አናሊና ቤርቦክ በመድረኩ ንግግር አድርገዋል።
    --የኢትዮጵያ ህዝብ አብዮታዊ ፓርቲ/ ኢሕአፓ/ ፕሬዝዳንት የሆኑትን፤ ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራን ጨምሮ ዘጠኝ ሰዎች በገንዘብ ዋስትና ከእሥር እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት ወሰነ።
    --የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ የጦር ካቢኔ በመተናቸውን መበተናቸውን የእስራኤል ባለስልጣናት ገለፁ።
    11 min
  • DW Amharic የሰኔ 09 ቀን ቀን 2016 የዓለም ዜና
    የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ወደ ምትገኘው ነቀምቴ በሣምንት ሦስት ቀናት በረራ መጀመሩን አስታወቀ። የእስራኤል ጦር በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ የሰብአዊ ርዳታ አቅርቦትን ለማሳደግ በየዕለቱ ለሰዓታት ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንደሚገታ አስታወቀ። በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል እየተካሔደ የሚገኘውን ጦርነት ለማብቃት ያለመ ማንኛውም የሰላም ሥምምነት መሠረት የዩክሬን የግዛት አንድነት ሊሆን እንደሚገባ ሰማኒያ ሀገሮች ጥሪ አቀረቡ። በአውሮፓ ዋንጫ የምድብ አራት የመጀመሪያ ጨዋታ ኔዘርላንድስ ፖላንድን 2 ለ 1 አሸነፈች።
    8 min
  • የዓርብ ሰኔ 7 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የዓለም ዜና
    አርዕስተ ዜና፦ ሽንሌ፥ ኢሰመኮ በአፋር እና ሶማሌ አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭት ማገርሸቱ አሳስቦኛል አለ፤ የሩስያ ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን ከዩክሬን ጋ ለመደራደር ሀገራቸው በቁጥጥሯ ስር ካዋለቻቸው ግዛቶች የዩክሬን ጦር ሙሉ ለሙሉ መውጣትን እንደ ቅድመ ሁኔታ አስቀመጡ፤ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) ዋና ጸሐፊ ዬንስ ስቶልተንበርግ በዩክሬን ፍትሐዊ እና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ሩስያ የመስፋፋት ፍላጎቷን ልትገታ ይገባል አሉ፤ የአውሮጳ ሃገራት እግር ኳስ ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ ዛሬ ማታ ሙይንሽን ውስጥ የዘንድሮ አዘጋጇ ጀርመን ስኮትላንድን ትገጥማለች
    11 min
  • የዓለም ዜና፤ ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓ.ም ሐሙስ
    DW Amharic
    --በኢንዱስትሪ የበለጸጉት የቡድን ሰባት አባል ሐገራት የመሪዎች ጉባዔ ዛሬ በጣልያን ጀመረ። የሃገራቱ የጉባዔ ዋንኛ ርዕስ ዩክሬንን በጦር መሳሪያና በገንዘብ ድጋፍ ማጠናከር ነዉ። በጋዛ እየተካሄደ ያለዉ ጦርነት፤ ከቻይና ጋር ውጥረት የበዛበት የንግድ ግንኙነትና የፍልሰት ጉዳይ ጉባኤዉ ይመክርባቸዋል።
    --ገጣሚ በላይ በቀለ ወያ በገንዘብ ዋስ ከእሥር ተለቀቀ። ገጣሚዉ ወጣት ባሕር ዳር ከተማ ማረሚያ ቤት ለ 11 ወራት ታሥሮ ቆይቷል።
    --በየመን የባሕር ዳርቻ በደረሰ የጀልባ አደጋ ቢያንስ 49 ሰዎች መሞታቸዉ ተሰማ። በጀልባዉ ላይ፤ 115 ሶማልያዉያን እና 145 ኢትዮጵያዉያን ተሳፍረዉ ነበር።
    12 min
  • የሰኔ 5፣2016 የዓለም ዜና
    -ኢትዮጵያ ዉስጥ «ሑከትና ብጥብጥ በመፍጠርና ሕገመንግሥታዊ ሥርዓትን በመናድ» ተጠርጥረዋል የተባሉ 9 እስረኞች ዛሬ አዲስ አበባ ያስቻለዉ የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ቀረቡ።ተጠርጣሪዎቹ አዋሽ አርባ ከሚገኘዉ እስር ቤት በቅርቡ አዲስ አበባ ወደሚገኘዉ ፖሊስ ጣቢያ እስር ቤት የተዛወሩ ናቸዉ።-ለዘንድሮዉ ሐጂ ከ1.5 ሚሊዮን የሚበልጡ ምዕመናን ከሙስሊሞቹ ቅድስት ከተማ መካ ገቡ።-ጋዛን የሚያወድመዉን ዉጊያና ወታደራዊ ዘመቻ ለማስቆም ዩናይትድ ስቴትስና የአረብ ተከታዮችዋ የሚያደርጉት ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ዛሬም ለዉጤት አልበቃም።
    11 min
  • የማክሰኞ፤ ሰኔ 4 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የዓለም ዜና
    *«በወንጀል የተገኘ ንብረትን ሕጋዊ ማስመሰልና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር» የተባለ ረቂቅ አዋጅ ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ ።
    *የስምንተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዋና ከተማ አዲስ አበባን ጨምሮ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በዛሬው ዕለት መሰጠት ተጀመረ ። *260 ግድም ስደተኞችን ያሳፈረች ጀልባ የየመን የባሕር ጠረፍ አቅራቢያ የአደን ባሕረ ሰላጤ ውስጥ ሰጥማ ቢያንስ 49 ሰዎች መሞታቸው ተገለ ። ጀልባዋ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ስደተኞችን አሳፍራ ከሶማሊያ የባሕር ጠረፍ 320 ኪሎ ሜትሮች ቀዝፋ እንደነበር አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል ።
    11 min
  • የሰኔ 3 ቀን 2016 ዓ/ም የዓለም ዜና
    DW Amharic ለአራት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የአውሮጳ ህብረት ፓርላማ ምርጫ የመሃል ቀኙ የአውሮጳ ህዝቦች ፓርቲ የተሻለ ወንበር በማግኘት ተጠናቀቀ። የህብረቱ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርዙላ ፎን ዴር ላየን ፓርቲ ኢፒፒ ከ720 የፓርላማ መቀመጫዎች 189ኙን በማሸነፍ ፕሬዚዳንቷ በኃላፊነታቸው መቀጠል የሚያስችላቸውን መደላድል ፈጥሮላቸዋል ተብሏል። ምርጫው የአርንጓዴ እና ሊበራል ፓርቲዎች በርካታ መቀመጫዎችን ሲያጡ የቀኝ እና ግራ አክራሪዎች ግን ከምንጊዜውም ይልቅ ተጠናክረው የመጡበት እንደነበር የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገባ ያመለክታል። «ምርጫውን አሸንፈናል» ሲሉ የተደመጡት የህብረቱ ፕሬዚዳን
    11 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…