የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የረቡዕ የግንቦት 21 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የዓለም ዜና
    አማራ ክልል ውጊያ መኪያሄዱ፤ ትግራይ ክልል የምግብ ርዳታ የሚሹ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች መቸገራቸው፤ ደቡብ አፍሪቃ ብሔራዊ ምርጫ መከናወኑ፤ የየመን ሁቲ አማጺያን ስድስት መርከቦች ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን ማሳወቃቸው፤ ኢራን ለየመን ሁቲዎች የጦር መሣሪያ ድጋፍ እንደምታደርግ ለመጀመሪያ ጊዜ ማረጋገጧ፤ ኒጀር የሚገኘው የጀርመን የአየር መጓጓዣ ጣቢያ አገልግሎት መስጠቱ ይቀጥላል መባሉ፤ ደቡብ አፍሪቃ ብሔራዊ ምርጫ መካሄዱ እንዲሁም ኒጀር የሚገኘው የጀርመን የአየር መጓጓዣ ጣቢያ አገልግሎት መስጠቱ ይሰኛል ።
    10 min
  • የግንቦት 20፥2016 የዓለም ዜና
    -ኢትዮጵያ ዉስጥ በኦሮሚያና አማራ ክልሎች የሚደረሱ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች አሁን አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ።።የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል በበኩሉ መንግስት የደነገገዉን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲያነሳ ጠይቋል።-ደቡብ አፍሪቃ ዉስጥ «ልዩ መራጮች» የተባሉ የሐገሪቱ ዜጎች ዛሬ ለሁለተኛ ቀን ድምፅ ሲሰጡ ዉለዋል።
    -ስጳኝ፣ አየርላንድና ኖርዌ ዛሬ ለፍልስጤም በይፍ የመንግስትነት ዕዉቅና ሰጡ።እስራኤል ርምጃዉን አጥብቃ ተቃዉማዋለች።
    11 min
  • የግንቦት 19 ቀን 2016 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    እስራኤል ትናንት ምሽት ራፋ ላይ ባካሄደችው የአየር ጥቃት ቢያንስ 35 ፍልስጤማውያን መገደላቸው ተሰማ። ጥቃቱ የተፈጸመው በጦርነቱ የተፈናቀሉ ወገኖች በተጠለሉበት ስፍራ መሆኑ ትኩረት ስቧል።
    በእስራኤል እና ግብጽ አዋሳኝ ድንበር አካባቢ የተኩስ ልውውጥ አንድ የግብጽ ድንበር ጠባቂ ወታደር ተገደለ። ሁለቱም ሃገራት ጉዳዩን እየመረመሩ መሆኑን አስታውቀዋል።
    ባለፈው ሳምንት ዓርብ በተከሰተ የመሬት መደርመስ ከሁለት ሺህ በላይ ሕዝብ ከእነሕይወቱ ሳይቀበሩ እንዳለቀረ የፓፓዋ ኒው ጊኒ መንግሥት አመለከተ።
    የጀርመን ፍርድ ቤት ለሩሲያ በመሰለል በተጠረጠረ ወታደራዊ መኮንን ላይ የሦስት ዓመት ከመንፈቅ እስራት ፈረደ።
    11 min
  • የዓለም ዜና፤ ግንቦት 16 ቀን 2016 ዓ.ም አርብ
    DW Amharic --ባለፈው መስከረም ሽቱትጋርት ጀርመን ከተማ በተካሄደ የኤርትራውያን ድግስ ላይ ከተነሳው ብጥብጥ ጋር ተሳታፊ ነው የተባለ አንድ የ28 ዓመት ወጣት ሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወር እስራት ተፈረደበት። --ዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት (ICJ) እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ደቡባዊ ክፍል በምትገኘዉ ራፋህ ከተማ የምታካሂደዉን ወታደራዊ ጥቃት “በአስቸኳይ እንድታቆም ጠየቀ። --ኤል ኒኞየአየር ለዉጥ በዚህ ዓመት በምሥራቅ አፍሪቃ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በገደለው የጎርፍ መጥለቅለቅ ላይ "ምንም ዓይነት ተጽዕኖ" እንደሌለው አንድ የሳይንስ ሊቃውንት ቡድን ዛሬ ይፋ ባደረገዉ ጥናት አስታወቀ።
    12 min
  • የግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም የዓለም ዜና
    DW Amharic እስራኤል በደቡብ ጋዛ በምትገኘው የራፋሕ ከተማ እያካሄደችው ባለው ጥቃት 35 ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የጋዛ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ። -በጀርመን በሕዝብ በተመረጡ ፖለቲከኞች ላይ እየደረሰ ያለው የአመጽ ጥቃት እንዳሳሰባቸው የጀርመን ፕረዚዳንት ገለጹ። ፕረዚደንቱ ይህን የገለጹት ጀርመን የምትተዳደርበትን መሰረታዊ ሕግ የጸደቀበትን 75ኛ ዓመት ዛሬ በበርሊን ከተማ በተከበረበት መድረክ ነው።-ሩስያ ያለብንን የአየር መቃወምያ እጥረት እንደበጎ ዕድል በመውሰድ ጭካኔ የተሞላበት ጥቃት እየፈጸመችብን ነው ሲሉ የዩክሬይን ፕረዚደንት ቮሎደሚር ዘለንስኪ አስታወቁ።
    8 min
  • የግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም. ዐርዕስተ ዜና
    በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ላሊበላ ከተማና አካባቢዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና የፋኖ ታጣቂዎች ትናንት ሲዋጉ መዋላቸዉን የከተማይቱ ነዋሪዎች አስታወቁ።
    ከዓፋር ክልል ዘልቀው ገቡ የተባሉ ታጣቂዎች በትግራይ ክልል ራያ ዓዘቦ ወረዳ ሰኞ ሌሊት ለማክሰኞ አጥቢያ በከፈቱት ጥቃት በትንሹ ሰባት ሰዎች ገደሉ። ጥቃቱ የደረሰበት የራያ ዓዘቦ ወረዳ የጋራርሳ ነዋሪዎችና የአካባቢዉ ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት ከሟቾቹ አብዛኞቹ ሕፃናትና ልጆች ናቸዉ።
    ኖርዌይ አየርላንድና ስፔይን ለፍልስጤም እውቅና እንሰጣለን ማለታቸው የፍልስጤም መሪዎችን ሲያስደስት እስራኤልን ደግሞ አስቆጥቷል።
    11 min
  • የዓለም ዜና፤ ግንቦት 13 ቀን፣ 2016 ዓ.ም
    DW Amharic በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አንድ ስፔናዊን ጨምሮ አራት ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ። የስፔናዊዉ አስክሬን ወደ አዲስ አበባ መላኩ ነዉ የተነገረዉ።- የቀድሞ የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ በሚቀጥለው ሳምንት በሚካሄደው አጠቃላይ ምርጫ ለፓርላማ አባልነት እንዳይወዳደሩ በሀገሪቱ ህገ-መንግስታዊ ፍርድ ቤት ታገዱ።- በሰሜን ምዕራብ ኢራን ታብሪዝ ከተማ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢራናዉያን ዛሬ ወደ ጎዳና በመዉጣት ባለፈዉ እሁድ ምሽት በሄሊኮፕተር አደጋ ለሞቱት ለሃገሪቱ ፕሬዚዳንት እና ለሰባት አጃቢ ባለሥልጣናት የሐዘን ሽኝት አደረጉ። ሟቹ ፕሬዚዳንት ሃሙስ ምሽት በትዉልድ ከተማቸዉ የቀብር ስርዓታቸዉ ይፈፀማል።
    12 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…