የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የዓለም ዜና፣ ነሐሴ 22፣ 2016
    -የኢትዮጵያ መንግሥትን በነፍጥ የሚወጉ ኃይላት በሐገሪቱ ብሔራዊ የምክክር ሒደት እንዲካፈሉ ለተደረገላቸዉ ጥሪ መልስ አለመስጠታቸዉን የምክክር ኮሚሽን አስታወቀ።ለታጣቂዎቹ ኃይላት ጥሪዉ የተደረገበትን መንገድና ጥሪዉ ሥለመድረስ አለመድረሱ ግን የኮሚሽኑ ባለሥልጣናት አልጠቀሱም።-----ግብፅ ለሶማሊያ የጦር መሳሪያ ማስታጠቅ ጀመረች።መሳሪያ የጫኑ ሁለት የግብፅ የጦር አዉሮፕላኖች ትናንት ሞቃዲሾ ማረፋቸዉን ዲፕላቶች አስታዉቀዋል።ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር ወደብ ለመኮናተር ከተስማማች ወዲሕ የሞቃዲሾና የካይሮ ፍቅር ፀጥንቷል
    11 min
  • የነሐሴ 21 ቀን 2016 ዓ/ም የዓለም ዜና
    ዓርስተ ዜና
    --የእስራኤል ልዩ ኃይል እጅግ በጣም ውስብስብ ባለው ልዩ ዘመቻ ደቡባዊ ጋዛ ውስጥ ከሚገኝ የሃማስ ዋሻ ውስጥ አንድ ታጋች ማስለቀቁን ዛሬ አስታወቀ። የ52 ዓመቱ ታጋች ከ10 ወራት በፊት ነበር በሃማስ ከደቡባዊ እስራኤል በሃማስ ታጣቂዎች ታግቶ የተወሰደው ።
    --በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ሰሞኑን በተከታታይ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ 23 ሰዎች ሞቱ። በአደጋዉ ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪ 2700 ያክል ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸዉ ተፈናቅለዋል።
    --የሱዳን ፈኖ ደራሽ ኃይል በዳርፉር ግዛት በስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ላይ በፈጸሙት የከባድ መሳሪያ ጥቃት በትንሹ 20 ሰዎች ተገደሉ።
    11 min
  • DW Amharic ነሐሴ 20 ቀን 2016 የዓለም ዜና
    DW Amharic--በስለት ሦስት ሰዎች የተገደሉባትን ዞሊንገን የጀርመን ምዕራባዊ ከተማን ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ እና ታዋቂ የሃገሪቱ ፖለቲከኞች ለህዝብ አጋርነታቸዉን በማሳየት ከተማዋን ጎበኙ። IS የተባለዉ ጽንፈኛ ቡድን ሃላፊነት በወሰደበት በዚህ ጥቃት ሦስት ጀርመናዉያን ተገድለዋል፤ ስምንት ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።
    --በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ በደረሰ ናዳ ህይወታቸው ካለፈ 10 ሰዎች መካከል እስካሁን የስድስቱን አስከሬን ማግኘት እንዳልተቻለ ተገለፀ። በሌላ በኩል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፤ ደቡብ አሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ፤ በኦሞ ወንዝና በቱርካና ሀይቅ ሙላት በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተፈናቀሉ።
    12 min
  • DW Amharic የነሐሴ 18 ቀን 2016 የዓለም ዜና
    በእስራኤል የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን መንግሥት በሚደግፉ እና በሚቃወሙ ሁለት ቡድኖች መካከል በተፈጠረው ግጭት ሁለት ኤርትራውያን መገደላቸውን ፖሊስ አስታወቀ። በምዕራብ ጀርመን በምትገኘው ዞሊንገን ከተማ ሦስት ሰዎች ከተገደሉበት እና ሌሎች ስምንት ከቆሰሉበት ጥቃት ጋር ግንኙነት ሳይኖረው አይቀርም የተባለ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ። የኤርትራ የቀድሞ የፋይናንስ ሚኒስትር ብርሃነ ኣብርሀ በእስር ላይ ሳሉ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። በጋዛ በትንሹ 50 ፍልስጤማውያን በእስራኤል ጥቃት መገደላቸውን የጋዛ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
    9 min
  • የሐሙስ ነሀሴ 16 ቀን 2016 ዓ/ም የዓለም ዜና
    DW Amharic- ህወሃት የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደርን በአዳዲስ ተሿሚዎች ለመቀየር ውይይት እንደሚጀምር ማስታወቁ- ሶማሊያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሀገሪቱ የሚያደርገውን በረራ እንደምታግድ መግለጿ- በአማራ ክልል ሁለት ዞኖች የመሬት መንሸራተት በሰብልና በመኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት ማድረሱ- የኬንያ ፖሊስ ከ40 በላይ ሴቶችን በመግደል ከዕስር ያመለጠ አንድ ተጠርጣሪን ለጠቆመ የገንዘብ ወሮታ እንደሚከፍል ማስታወቁ-ታሊባን የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ልዩ ዘጋቢን ወደ አፍጋኒስታን እንዳይገቡ ማገዱ
    11 min
  • የረቡዕ ነሐሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የነሐሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    በኮንሶ ዞን ዋና ከተማ ሰገን የገቡት ታጣቂዎች ከተማዋን ተቆጣጠሩ፤የፖሊስ አባላትና ሰላማዊ ሰዎችንም ገደሉ።
    የ7 ዓመትዋን ሄቨን አዎትን አስገድዶ በመድፈርና አንቆም በመግደል ጥፋተኛ የተባለው ጌትነት ባዬ ላይ ፍርድ ቤት ያስተላለፈውን የ25 ዓመት የእሥር ፍርድ በመቃወም በበይነ መረብ ፊርማቸውን ያኖሩ ሰዎች ቁጥር ዛሬ ከ240 ሺህ በላይ መድረሱ ተገልጿል።
    ኬንያ ውስጥ በርካታ ሰዎችን በተከታታይ በመግደል ተጠርጥሮ የታሰረው ኬንያዊና 12ኤርትራውያን እስረኞች ናይሮቢ ከሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ እንዲያመልጡ በመርዳት የተከሰሱ አምስት የኬንያ ፖሊሶች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ።
    12 min
  • DW Amharic የነሐሴ 13 ቀን 2016 የዓለም ዜና
    በምርጫ ቦርድ እውቅና የተነፈገው የህወሓት 14ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ደብረፅዮን ገብረሚካኤልን ሊቀ-መንበር አድርጎ መረጠ። አቶ አማኑኤል አሰፋ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳን በመተካት ምክትል ሊቀ-መንበር ሆነው ተመርጠዋል። የኬንያ መንግሥት ተቃውሞ በቀሰቀሰው የፋይናንስ ደምብ ውስጥ ተካተው ከነበሩ ቀረጦች የተወሰኑትን ሥራ ላይ በማዋል 1.2 ቢሊዮን ዶላር የመሰብሰብ ዕቅድ እንዳለው የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣን አስታወቁ። የተባበሩት መንግሥታት ተቀባይነት ከሌለው ደረጃ ደርሷል ያለውን የርዳታ ሠራተኞች ግድያ አወገዘ። ብዙ የርዳታ ሠራተኞች ከተገደሉባቸው አስር ሀገራት አንዷ ኢትዮጵያ ናት።
    10 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…