የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • DW Amharic የመስከረም 6 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    አዲሱ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ 16 የቀድሞ ከፍተኛ አመራሮች ከፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ማገዱ አስታወቀ። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ብልጽግና ፓርቲ አባላቱን ሲያሰለጥን እንዳለፈው ዓመት “ከመንግሥት ካዝና ገንዘብ አውጥቶ” እየከፈለ ነው ሲል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ወነጀለ።የኬንያ ዋና ኦዲተር ሀገሪቱ ከተለያዩ ወገኖች የተበደረችውን ዕዳ ኦዲት ማድረግ መጀመሩን የፋይናንስ ሚኒስትሩ ተናገሩ። በምዕራብ እና ማዕከላዊ አፍሪካ በጣለ ከባድ ዝናብ እና ባስከተለው ጎርፍ ምክንያት ከ500 በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን እንዳጡ የተመ አስታወቀ።
    10 min
  • የዓርብ መስከረም 3 ቀን 2016 ዓ/ም የዓለም ዜና
    DW Amharic-በኮሬ ዞን በእገታ ላይ የነበሩ አራት አርሶ አደሮች መገደላቸው፤በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን አንድ ድልድይ በመደርመሱ፤ ዞኑን ከአጎራባች አካባቢዎች ጋር የሚያገናኝ መንገድ አገልግሎት እንደማይሰጥ መገለፁ፤የሴኔጋሉ ፕሬዝዳንት የሀገራቸውን ፓርላማ መበተናቸው፤መካከለኛው አውሮፓ በመጭው ቅዳሜና እሁድ በሚጥለው ከባድ ዝናብ ለከፍተኛ የጎርፍ ይጋለጣል መባሉ፤የሰሜን ኮሪያው መሪ ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ የኒውክሌር ማብላያ እና የዩራኒየም ማበልፀጊያ ቦታዎችን መጎብኘታቸው፤ዶናልድ ትራምፕ ከተፎካካሪያቸው ካማላ ሀርስ ጋር ሌላ የምርጫ ክርክር እንደማያደርጉ ማስታወቃቸው የዛሬው የዓለም ዜና ያካተታቸው ርዕሰ ጉዳዮች ናቸው።
    11 min
  • የመስከረም 2 ቀን ፣ 2017 ዓ.ም.የዓለም ዜና
    የሐሙስ መስከረም 2 ቀን 2017 ዓም አርዕስተ ዜና
    የተባበሩት መንግሥታት የትምሕርት የሳይንስና የባህል ድርጅት በምህጻሩ ዩኔስኮ ዩኔስኮ የሱዳን ብሔራዊ ቤተ መዘክርን ጨምሮ በሌሎች የሱዳን ቤተ መዘክሮች እና የቅርስ ተቋማት ላይ ተፈጽመዋል የሚባሉ ዝርፊያዎችና ጉዳቶች በእጅጉ አሳስቦኛል አለ።
    ስዊድን ወደ ሀገራቸው በፈቃደኝነት ለሚመለሱ ስደተኞች እስከ 34 ሺህ ዶላር እንደምትከፍል አስታወቀች።
    በደቡብ ምዕራብ እስያን የመታው ያጊ የተባለው ወጀብ ያስከተለው ጎርፍ የገደለው ሰው ቁጥር ከ250 በለጠ።
    12 min
  • የጳጉሜን 4 ቀን 2016 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ጅማ ሆሮ ወረዳ ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መናድ የሦስት ሰዎች ሕይወት አለፈ። በንብረት ላይም ከፍተኛ ውድመት ደረሰ።
    በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ያለፉት ተማሪዎች ብዛት ከአምናው እንደሚሻል ተገለጸ። እንዲያም ሆኖ ከ1,363 ት/ቤቶች ምንም ተማሪዎች እንዳላለፉ የትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ አስታውቋል።
    ሰሜን ናይጀሪያ ውስጥ የነዳጅ ቦቴ ሰዎች ካሳፈረ ትልቅ መኪና ጋር ተጋጭቶ በተፈጠረ ፍንዳታ ቢያንስ 52 ሰዎች ሞቱ።
    ምዕራባዊ ሶርያ ውስጥ እስራኤል ባደረሰችው የአየር ጥቃት 16 ሰዎች ሲገደሉ፤ በርካቶች መጎዳታቸው ተነገረ። ኢራን ጥቃቱን አውግዛለች።
    11 min
  • የጳጉሜ 2 ቀን 2016 ዓ/ም የዓለም ዜና
    Dw Amharic-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማረቆ ልዩ ወረዳ ዛሬ እኩለ ቀን አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት ማለፉ፣በአማራ ክልል ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ አድርገዋል በተባሉ 7ሺህ የሚጠጉ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መውሰዱ፣ አርብ ዕለት በዌስት ባንክ የተገደለችው ቱርካዊ-አሜሪካዊት ወጣት ግድያ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ መጠየቁ፣ሩሲያ በአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ላይ ገደብ እንደምትጥል መግለጿ እንዲሁም የዶናልድ ትራምፕ ክስ የሀገሪቱ ምርጫ እስኪጠናቀቅ ድረስ ብይኑ እንዲዘገይ መወሰኑን የዛሬው የዓለም ዜና የያዛቸው ርዕሰ ጉዳዮች ናቸው።
    13 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…