ዜና መጽሔት

ዜና መጽሔት

Download on the App Store

ዜና መጽሔት episodes

  • የግንቦት 9፣2016 ዜና መፅሔት
    -በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሥለ ኢትዮጵያ ፖለቲካዊና የሰብአዊ መብት ይዞታ የሰጡትን አስተያየት ኢትዮጵያ አጥብቃ ተቃወመችዉ።የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ባወጣዉ መግለጫ የአምባሳደሩን አስተያየት «ሐሰት« ና «ተቀባይነት» የሌለዉ በማለት አጣጥሎታል።-በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዎላይታ ዞን ደሞዝ ያልተከፈላቸዉ የመንግስት ሠራተኞች ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ያደረጉት ሰልፍ በፖሊስ ኃይል ተበተነ።-በቀጣዮቹ ሁለት ወራት 75 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎች ወደ ሰላማዊ ሕይወታቸው ለመመለስ እቅድ መያዙ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የተሃድሶ ኮምሽን አስታወቀ
    21 min
  • የሐሙስ ግንቦት 8 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የዜና መጽሄት
    የዜና መጽሔ ዘገባዎቹ፦ለኢትዮጵያው ግጭት መፍትሄ የአሜሪካ ጥሪ፦ የአምባሳደሩ ንግግር፤ ለባሕላዊ ዳኝነት ትኩረት የሰጠው የፍትሕ ተቋማት ሽግግር ፤ የሲቪል ድርጅቶች ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አጀንዳዎችን አስገቡ፤ የኢትዮጵያ ኢንደስትሪ ዞኖች እጣፈንታ እና የፖሊሲ ለውጥ እንዲሁም እስራኤል በራፋሕ ላይ የከፈተችው ጦርነት ይሰኛሉ ።
    27 min
  • የግንቦት 7 ቀን 2016 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    የአሜሪካን የአፍሪቃ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛን፣ የኦሮምያን የፖለቲካና ፀጥታ ችግር ለመፍታት ሁሉን አቀፍ ድርድር እንዲደረግ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ጠይቀዋቸዋል።
    በአማራ ክልል የሰላም እጦት ሰበብ በተለያዩ አካባቢዎች ትምሕርት ቤቶች በመዘጋታቸው ሴት ተማሪዎች እንዲያገቡ እየተገደዱ መሆኑን ነዋሪዎች ለዶቼቬለ ተናግረዋል።
    በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሶዶ ዙሪያ ወረዳ የመንግሥት ሠራተኞች ደሞዝ እንዲከፋላቸው በአደባባይ ሰልፍ ጠይቀዋል። እነዚህና የካናዳ መንግሥት እርዳታ ለቀድሞ ተዋጊዎች እንዲሁም በጎ ፈቃደኛዋ ሲስተት ካሕሳ ሓጎስ መሸለማቸውን የሚያስቃኙ ዘገባዎች ተካተዋል።
    21 min
  • የማክሰኞ፤ ግንቦት 6 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የዜና መጽሄት
    የፖለቲከኛ በቴ ዑርጌሳን ግድያ የምርመራ ሂደት ምን ተግዳሮት ገጥሞት ይሆን?
    --ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ተማጋጋቢዎቹ ጎረቤት ሀገራት
    --በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ በተከሰተ ግጭት የሰው ህይወት ማለፉ እንዲሁም
    --የአዉሮጳ ህብረት 2024 ምርጫ
    ዛሬ ከያዝናቸዉ ለማስደ,ጥ ከያዝናቸዉ ዘገባዎቻችን መካከል ጥቂቶቹ ናቸዉ
    17 min
  • DW Amharic - ዜና መጽሔት፤ የግንቦት 5 ቀን፣ 2016 ዓ.ም ሰኞ
    DW Amharic - ከባድ ዝናብ ድንኳናቸውን ያፈራረሰባቸው በደቡብ ወሎ የሚገኙ ተፈናቃዮች ፤
    በድሬደዋ የጎርፍ ጉዳትን ለመቀነስ ያለመው ፕሮጀክት፤
    በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ቦረና ዞን የተማሪዎች ጥያቄና ስጋት፤
    እንዲሁም ጅቡቲ ለዓለም አቀፍ ባለሀብቶች ያቀረበችውን የልማት ጥሪ የተሰኙ ዘገባዎች ተጠናቅረዉበታል።
    18 min
  • DW Amharic የሚያዝያ 30 ቀን 2016 ዜና መጽሔት
    ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በነቀምቴ ከተማ ከአራቱም የወለጋ ዞኖች ለተውጣጡ የማኅበረሰብ ክፍሎች “ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ምላሽ አግኝቷል፤ ለዚህ አንታገልም” ሲሉ ተናገሩ። በግጭት ምክንያት በአማራ ክልል ደም ባለመሰብሰቡ ሆስፒታሎች ሕሙማን ለማከም ችግር ገጥሟቸዋል። በትግራይ ክልል የሚገኘው እና በጦርነት ወቅት የተጎዳው የአል ነጃሺ መስጂድ መልሶ ለመገንባት ያቀደ መርሐ ግብር ይፋ ተደረገ። ኢትዮጵያ በፕሬስ ነጻነት ባለፈው ዓመት ከነበረችበት በአስራ አንድ ደረጃዎች ወደ ኋላ አሽቆለቆች። እስራኤል በራፋ የጀመረችው ወታደራዊ ዘመቻ እንዳሳዘናቸው የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ግንኙነት ኃላፊ ጆሴፕ ቦሬል ተናገሩ።
    21 min
  • የማክሰኞ ሚያዝያ 29 ቀን፣ 2016 ዓ.ም ዜና መፅሔት
    የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት)ኃይላት ከሱዳን ጦር ጋር ወግነው እየተዋጉ ነው በማለት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ያቀረበውን ክስ የትግራይ ክልል ዜያዊ አስተዳደር አስተባበለ። በአማራ ክልል የሰሜን ጎጃም ዞን መምህራን ደመወዝ ከተከፈላቸው ከ2 ወራት በላይ መሆኑን ዐስታወቁ።የቅድመ ክስ እሥርን ለመቆጣጠር እና ለማስቀረት እንዲሁም የፍትሐዊ እና ሰብአዊ መብት መርኾችን ያካተተ የወንጀል ፍትሕ ሥርዓት ለመገንባት፤ የፍትሕ አካላት እና ሌሎች ባለድርሻዎች ግዴታቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ።በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞን ዛሬ ጠዋት የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ነዋሪዎች ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል
    19 min

About ዜና መጽሔት

From the publisher's feed

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ…