ዜና መጽሔት

ዜና መጽሔት

Download on the App Store

ዜና መጽሔት episodes

  • የግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    የዜና መጽሔት ዝግጅታችን
    የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት የአቶ ሽመልስ አብዲሳ የሰላም ጥሪ፣
    የአውሮፓ ህብረት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የሰጠው ሽልማት ፣
    ዓረና ትግራይ በክሉ ለሚታየው ሕገወጥ የመንግስት ባለስልጣናትን መወቀሱን፤
    እንዲሁም የቀድሞው አሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተከሰሱባቸው 34 ክሶች ጥፋተኛ መባላቸውን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል
    18 min
  • የረቡዕ የግንቦት 21 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የዜና መጽሄት
    በአማራ ክልል ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞንች በሚገኙ አንዳንድ አካባቢዎች ሰሞኑን በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ መደረጉን ነዋሪዎች አስታወቁ።ዉጊያዉ ዛሬም መቀጠሉን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።በትግራይ ክልል 4 ነጥብ 5 ሚልዮን ሕዝብ የምግብ እርዳታ እንደሚሻ የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮምሽን አስታወቀ።ከዕርዳታ ፈላጊው ለ3 ሚልዮን ዜጎች ዓለምአቀፍ ተቋማትና ሌሎች አጋዦች እርዳታ እየቀረበ ቢሆንም የተቀሩት 1 ነጥብ 5 ሚልዮን ግን አሁንም ያለ ምንም ድጋፍ ችግር ላይ መሆናቸው ተገልጿል።
    15 min
  • ዜና መጽሔት፤ ግንቦት 20 ቀን 2016 ዓ.ም ማክሰኞ
    DW Amharic በዚህ ዝግጅታችን
    የኢትዮጵያ መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን እንዲያነሳ መጠየቁ ፤
    በራያ አላማጣ አካባቢዎች እየተከሰተ ያለዉ አፈና መዋከብ፤
    የግንቦት 20 አዎንታዊ እና አሉታዊ ፍሬው ስታወስ፤
    የመንገድ መዘጋት በምዕራብና በምስራቅ ጎጃም ዞኖች እንዲሁም
    የአዉሮጳ ህብረት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በጋዛ ጉዳይ ላይ ስለመምከራቸዉ የተሰኙ ርዕሶችን እናስተነትናለን።
    21 min
  • የግንቦት 19 ቀን 2016 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ከሚገኘው የቡልቂ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ግንባታ ጋር በተያያዘ ከ15 ሚሊየን ብር በላይ በመመዝበር የተጠረጠሩ ባለሞያዎች እየተያዙ ነው፣
    የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፤ የክልሎች ምክክር ምዕራፍን ከፊታችን ረቡዕ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በአዲስ አበባ እንደሚጀምር ዛሬ አስታውቋል።
    አፍሪቃ ኅብረት ቅጽር ግቢ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለማጭበርበር በመሞከር ተጠርጥረው የታሰሩት ቀሲስ በላይ መኮንን ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
    14 min
  • የግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም የዜና መጽሔት
    በታሪካዊቱ ላሊበላ ከተማ ዙሪያ በመንግሥትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ለሰዓታት የዘለቀ ውጊያ መካሄዱ፤
    በትግራይና አፋር ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ የሰባት ሲቪሎች መገደል፤
    የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን በነፍጥ ለሚፋለሙ ኃይላት ያቀረበው ጥሪ የት ደረሰ?
    በኦሮሚያ ክልል የቀጠለው ግጭት በሲቪል ዜጎች ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ፤ እንዲሁም በአሜሪካ የሚገኙ የኢትዮጵያ ሲቪክ ድርጅቶች የጻፉትን ደብዳቤ
    21 min
  • የዜና መጽሔት፤ ግንቦት 13 ቀን፣ 2016 ዓ.ም
    DW Amharic የዉህዳን እና ሕዳጣን ማሕበረሰቦች መብት፤ የአቶ ታዬ ደንደዓ የክስ መቃወሚያ ውድቅ መሆን፤ በማጎ ብሄራዊ ፓርክ የስጳኝ ዜጋን ጨምሮ 4 ሰዎች ተገደሉ፤ እንዲሁም የአለማቀፍ ወንጀሎች መዳኛ ፍርድ ቤት በእስራኤልና ሀማስ መሪዎች ላይ ያቀረበው ክስ ጭብጥ የተሰኙ ርዕሶች ተጠናቅረዉበታል
    21 min
  • DW Amharic የግንቦት 12 ቀን 2016 የዜና መጽሔት
    ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአፍሪካ ኅብረት አካውንት 6 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ለማጭበርበር ሞክረዋል በሚል በቁጥጥር ሥር ከዋሉ ተጠርጣሪዎች መካከል አራቱ አሁንም በፖሊስ ጣቢያ እንዲቆዩ ፍርድ ቤት አዘዘ። የወላይታ ዞን የሠራተኞቹን ደሞዝ ከሚቀጥለው ዓመት ተበድሮ ለመክፈል መገደዱ ተገለጸ። የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የጦር መሳርያ ዝውውርን ለመቆጣጠር እየጣረ መሆኑን አስታወቀ። በኦሮሚያ ክልል በምትገኘው ኪረሙ ከተማ 50 ሺሕ ተፈናቃዮች ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን የምሥራቅ ወለጋ ዞን ገለጸ። የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ለእስራኤልና ፍልስጤም የሁለት መንግሥት መፍትሔ ለማስገኘት እየሰሩ መሆናቸውን አስታወቁ
    21 min

About ዜና መጽሔት

From the publisher's feed

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ…