Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about Amharic:How many episodes does Amharic have?The podcast currently has 221 episodes available.
December 30, 2022ስብከት አስራ አንዴ የእግዚአብሔር ህግና የሰዎች ህይወትብዙ ሰዎች ኢየሱስ ብሉይ ኪዳንን እየተፃረረ ነው ብለው ያስባሉ፣ ነገር ግን እርሱ ሲቃወም የነበረው የኃይማኖት መሪዎችን ትምህርት ነው፡፡ እርሱ ለደቀ መዛሙርቱ ሲናገር፡- “እኔ የማስተምራችሁ ሁሉ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የሚገኝ ነው፣ እኔ ግን የማስተምረው የእናንተ ኃይማኖት መሪዎች ከሚያስተምሩት የተለየ ነው፡፡” ኢየሱስ ስለ ሕጉ ፊደልና ስለ ሕጉ መንፈስ ልዩነት አስረዳ፡፡ እርሱ ሕጉ ውጫው ሳይሆን ውስጣዊ መሆን አለበት ብሎ አስተማረ፡፡...more27minPlay
December 30, 2022ስብከት አስር ጨው እና ብርሃንእውነተኛ ደቀ መዛሙርት መደበቅ የማይችሉት እውነት ኢየሱስ እነርሱን የባህል ለውጥ እንዲያመጡ እንደሚጠቀምባቸው ነው፡፡ የእርሱ ደቀ መዛሙርት በተራራ ላይ እንዳለች ከተማና በመቅረዝ ላይ እንዳለ ሻማ ናቸው፡፡ በጨለማ ለሚገኙ እጅግ በርካታ ሰዎች ብቸኛ ብርሃን ክርስቲያኖች ብቻ ናቸው፡፡ የእርሱ ደቀ መዛሙርት ጨው እና ብርሃን የመሆን ሚናቸውን ካልተወጡ ማንም ሊወጣው አይችልም፡፡ደቀ መዛሙርት ወደ አለም የተላኩት የእግዚአብሔርን መፍትሄ ሁሉም ሰው እንዲያንጸባርቁ ነው፡፡...more22minPlay
December 30, 2022ስብከት ዘጠኝ ባህሌ እና ባህሪይብፁዓን የኢየሱስ የተራራው ስብከት መሠረታዊ ሐሳቦች ናቸው፡፡ እነዚህ ብፁዓን ዓለምን የሚለውጡትን መልካም ባሕርያት የሚገልፁ ናቸው፡፡ ቀጥሎ ኢየሱስ የእርሱ ደቀ መዛሙርት የሚኖሩበትን ባህልና ሕብረተሰብ እንዲለውጡ ማብራሪያና የትግበራን ትምህርት ሰጥቷል፡፡ ደቀ መዛሙርት ክርስቶስን በሚመስል ባሕርይ የዓለምን ሕዝብ ሲያገለግሉ፣ እነርሱ ሥጋን ከመበስበስ እንደሚጠብቅ ጨው፣ የእነርሱ ተፅዕኖ ዓለምን ከመጥፋት ያድናል፣ እነርሱም ጠቃሚ የሆኑ ኢየሱስ የሚጠቀምባቸው አስፈላጊ ሰዎች ይሆናሉ፡፡...more23minPlay
December 30, 2022ስብከት ስምንት የተሰዯደ የሰሊም መሌክተኞች እና ተስፋዎች“ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፣ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና፡፡” የሚያስታርቁ ብፁዓን የሚለውን ተከትሎ ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው የሚለው መጠቀሱ ምክንያት አለው፡፡ እነዚያ የእርቅ አገልግሎት አገልጋዮች ብዙ ጊዜ መከራን ይቀበላሉ፣ ሕይወታቸውንም የሚያጡበት ጊዜ አለ፣ ምክንያቱም እነርሱ ራሳቸውን የኢየሱስ ወገን ስላደረጉ ነው፡፡ እውነተኛ ደቀ መዛሙርት፣ በኢየሱስ የሚኖሩ፣ “የብፁዓን” ባሕርይ ያላቸው፣ ሰዎች መሆን እንዳለባቸው እንዲሆኑ በመልካም ሥነ ምግባር ሰዎችን የሚሞግቱ ብዙ ጊዜ ለኢየሱስ መከራን ይቀበላሉ፡፡...more18minPlay
December 30, 2022ስብከት ሰባት የእርቅ አገሌግልትሰባተኛው ብፁዓን (የሚያስታርቁ ብፁዓን ናቸው፣ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና) የሚናገረው የእግዚአብሔር መፍትሄ ተልዕኮ አካል ለሆኑት ነው፡፡ የሰው ልጆች ከእግዚአብሔር ተለይተዋል፡፡ እና ከእግዚአብሔር ጋር ከታረቅን - ከእርሱ ጋር ያለን ግንኙነት ትክክለኛ ከሆነ - ሌሎችን ከእርሱ ጋር እንድናስታርቅ እግዚአብሔር ይጠቀምብናል፡፡ እንዲሁም እርሱ እኛ እንድንታረቅና ሌሎችም እንዲታረቁ ይረዳቸዋል፡፡...more22minPlay
December 30, 2022ስብከት ስዴስት የፍቅር ሌብ“የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፣ ይማራሉና፡፡ ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፣ እግዚአብሔርን ያዩታልና፡፡” “ምሕረት” ሚለው ቃል “ቅድመ ሁኔታ የሌለበት ፍቅር” ማለት ነው፡፡ የዚህ ዓይነት ፍቅር ደቀ መዛሙርቱ የእግዚአብሔርን ፍቅር ለሌሎች ማስተላለፍ የሚችሉ እንዲሆኑ የሚያስችላቸው ነው፡፡ እኛ የምሕረት ሰዎች ስንሆን የእኛ ፍላጎት ጥያቄ ላይ ይወድቃል ምክንያቱም ቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ፍቅርን ለመረዳት ከባድ ስለሆነ ነው፣ በተለይም የዚህን ዓይነት ፍቅር አይተው ለማያውቁ ሰዎች፡፡ እግዚአብሔር እኛን በወደደበት ፍቅር እኛም ሌሎችን ስንወድድ ፍላጎታችን ንፁህ ይሆናል፡፡...more23minPlay
December 30, 2022ስብከት አምስት የተሇየ ፅዴቅለጽድቅ መራብና መጠማት ትክክለኛን ነገር ለማወቅ በጥልቅ ፍላጎት መፈለግ ነው፡፡ እንዴት እንደምታደርጉና ምን እንደምታደርጉት ለእግዚአብሔር አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ እኛ የተጠራነው ትክክለኛውን ነገር እንድናደርግ ነው እንጂ ምቹ ነገሮችን እንድናደርግ አይደለም፡፡ ብፁዓን በሚለው ትምህርት ውስጥ ንድፍን እንመለከታለን፡፡ እነዚህ ብፁዓን በሚለው ትምህርቶች ውስጥ ሁሉም የቀረቡት ጥንድ ጥንድ ሆነው፡፡ እኛ የምናዝነው በመንፈስ ድሆች እየሆንን ነው፣ እኛ የዋሆች ስንሆን ለጽድቅ እንራባለን እንጠማለን፡፡ የተሰጠን ተስፋ ሙሉ በሙሉ እንደምንሞላ ነው፡፡...more24minPlay
December 30, 2022ስብከት አራት የማፅናናት አገሌግልት እና እረፍትደቀ መዛሙርቱ ማዘንና የዋህ ማለት ምን ማለት እንደሆነ መማር አለባቸው፡፡ አማኞች አንዳንድ ጊዜ የሃዘን ምልክትን ማሳየት ስህተት ነው ብለው ያስባሉ፡፡ የእኛን ሃዘን ትክክለኛውን ጥያቄ እንድንጠይቅ፣ መልስን ከእግዚአብሔር እንድንፈልግ፣ እና እግዚአብሔር ያዘጋጀውን በረከት እንድንቀበል ለመጠቀም እግዚአብሔር ይፈልጋል፡፡ በምድር ላይ ከኖሩ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ሙሴ ትሁት እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይመሰክራል፡፡ የዋህነት ማለት በአዛዥ ቁጥጥር ሥር መሆን ነው፡፡ የዋህ ደቀ መዝሙር በእግዚአብሔር አብ ቀንበር ሥር በስነሥርዓት የሚኖር ነው፡፡...more31minPlay
December 30, 2022ስብከት ሶስት እኔ አሌችሌም እርሱ ግን ይችሊሌኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ማስተማር የጀመረው በስምንት ባሕርያት ሲሆን እነርሱም “ብፁዓን” ተብለው የሚታወቁት ናቸው፡፡ ኢየሱስ እነዚህ ባሕርያት ላሉአቸው ደቀ መዛሙርት ሊባርካቸው ቃል ገባ፡፡ እነዚህ የተባረኩ ባሕሪያት የአመለካከት ግለ - ታሪክ ወይም አስተሳሰብ ሲሆኑ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርትን ባሕሪይ ላይ ተፅዕኖ የሚያመጡና የእርሱ መፍትሄ አካልና በምድር ላይ ለሚሰቃዩ ሰዎች የክርስቶስ መልስ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡ የእነዚህ ባሕሪያት የመጀመሪያው “በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፣ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና፡፡” የሚለው ነው፡፡...more24minPlay
December 30, 2022ስብከት አንዴ የተራራው ሊይ ስብከት አውዴበጣም አስፈላጊ በሆነው የተራራው ስብከት ኢየሱስ በገሊላ በሚገኝ ተራራ ላይ የእርሱ ደቀ መዛሙርት ነን የሚሉትን ሰዎች የሞገተበት፣ ደቀ መዛሙርቱን በእግዚአብሔር ፍቅርና በዓለም ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን በሚያሰቃይ ሕመም መካከል ስልታዊ በሆነ መንገድ ያስቀመጠበት ነው፡፡ እርሱ የራሱን ደቀ መዛሙርት ከእርሱ ጋር አብረው እንዲሰሩና የእርሱ ፍቅር አስተላላፊዎች እንዲሆኑ ሞገታቸው፡፡ እርሱ የተራራውን ስብከት ያጠናቀቀው አድማጮቹ ለእርሱ የተሰጡ እንዲሆኑና 12ቱን ሰዎች ሐዋርያት፣ ወይም “የተላኩ” ብሎ በመመደብ ሲሆን እነዚህ ሰዎች ለኢየሱስ ኖረው ለኢየሱስ የሞቱ ናቸው፡፡...more26minPlay
FAQs about Amharic:How many episodes does Amharic have?The podcast currently has 221 episodes available.