Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about Amharic:How many episodes does Amharic have?The podcast currently has 221 episodes available.
December 30, 2022ስብከት ሃያ አንዴ የእግዚአብሔር መንግስት እሴቶች“እንግዲህ። ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ … ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።” ይህ ምዕራፍ ስለ ስጋት ምን ማድረግ እንዳለብን ይናገራል፣ ነገር ግን የምዕራፉ ዋና አስተምህሮ ቅድሚያ ልንሰጣቸው ስለሚገባ ነገሮች የሚያስተምር ነው፡፡ እኛ ስንጨነቅ፣ ለምን ዓይነት ነገር ዋጋ እንደምንሰጥና ለእኛ የሚጠነቀቀውን እግዚአብሔርን ምን ያህል እንደምንታመን እያሳየን ነው፡፡ እግዚአብሔርን በሕይወታችን ውስጥ ቅድሚያ ከሰጠነው፣ ሌሎች ነገሮች በልባችን ውስጥ ትክክለኛውን ሥፍራ ይይዛሉ፡፡...more32minPlay
December 30, 2022ስብከት ሃያ መንፈሳዊ እሴቶችትክክለኛ ባህርይ በውስጣቸው ያለ ደቀ መዛሙርት የሚኖሩት በትክክለኛ እሴቶች ነው፡፡ እነርሱ ቅድሚያ የሚሰጡት ነገር የተመሠረተው በዘላለማዊነት ላይ ነው እንጂ በምድራዊ ነገሮች ላይ አይደለም፡፡ ለዚህም ነው ደቀ መዛሙርት በምድር ላይ እንደ ጨውና እንደ ብርሃን ተፅዕኖን የሚያደርጉት፡፡ እንደ ኢየሱስ፣ ባለን ጊዜ በምናደርጋቸው ነገሮች የእኛ እሴቶች ምን እንደ ሆኑ ያስታውቁናል፣ ምን እንደምናስብ፣ ምን ዓይነት ስጋትና ምኞት እንዳለን፣ እና ምን ወይም ማንን እንደምናገለግል፣ ምክንያቱም እግዚአብሔርንና ገንዘብን ማገልገል አንችልም፡፡...more34minPlay
December 30, 2022ስብከት አስራ ዘጠኝ ምህረት ማዴረግና መጾምደቀ መዛሙርት እና ፆም - ልክ እንደ መስጠትና ፀሎት፣ ፆም መፆም ያለበት በቀጥታ ወደ እግዚአብሔር ነው እንጂ የሌሎችን ትኩረት ለመሳብ መሆን የለበትም፡፡ ልክ እንደሌሎቹ ተግባራት እግዚአብሔር እርሱ የሚመለከተውን ነገር ይሸልማል፣ ያም የልባችን ፍላጎቶች ነው፡፡ መስጠት ለእግዚአብሔር ያለንን መሰጠት የምናሳይበትን እድል እንደሚሰጠን ሁሉ፣ ፆምም በሕይወታችን ውስጥ ከሥጋዊ ጉዳዮች ይልቅ ለመንፈሳዊ ነገሮች ምን ያህል ዋጋ እንደምንሰጥ የምንለካበትን እድል ይሰጠናል፡፡ ፆም የእኛ ፀሎት ምን ያህል ከልብ እንደሆነ ያሳያል፡፡...more39minPlay
December 30, 2022ስብከት አስራ ስምንት መንፇሳዊ የፀልት ትምህርት እና የዯቀመዝሙር የፀልት ባህሪይኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን የፀሎት አርዓያ የሆነ ፀሎትን አስተማረ፣ ይህ ፀሎት በተለምዶ “የጌታ ፀሎት” ይባላል፣ ነገር ግን ይህ ፀሎት መባል የነበረበት “የደቀ መዛሙርት ፀሎት” ነው፡፡ ኢየሱስ ስለ ፀሎት ያስተማረን ፀሎት መፀለይ ያለበት ከሰዎች ዘንድ ትኩረትን ለማግኘት ሳይሆን ወደ እግዚአብሔር ነው፡፡ ይህ አርዓያ የሆነ ፀሎት በውስጡ የእግዚአብሔርን ፈቃድ መጠየቅ፣ ይህም የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያስቀድም ፀሎትን ይዟል፡፡ እንደዚሁም የግል ጥያቄዎችን፣ የደቀ መዛሙርቱን የግል ጥያቄዎችን የያዘ ፀሎት ነው፡፡ የእኛን ፈቃድ እንደ እርሱ ፈቃድ እንዲሆን ስናደርግ እግዚአብሔር የእኛን የግል ጥያቄዎችን ይመልሳል፡፡...more30minPlay
December 30, 2022ስብከት አስራ ሰባት የመስጠት መንፇሳዊ ስርዓትበማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 6 ላይ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን የተወሰኑ መንፈሳዊ ሥነ ስርዓቶችንና እሴቶችን እንዲከተሏቸው ሲያሳስባቸው እንመለከታለን፡፡ የእርሱ መፍትሄ አካል ለመሆን ለሚፈልጉ ሰዎች ኢየሱስ ያስተማረው የመጀመሪያው መንፈሳዊ ሥነ ስርዓት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መጋቢነት -- እኛ ያለንና እኛ ራሳችን የእግዚአብሔር ስለሆንን እኛ የእርሱ ንብረት አስተዳዳሪዎች ነን፡፡ እግዚአብሔር በግልና በፍላጎት በምስጢር የሚሰጡ ሰዎችን በግልጽ ይሸልማል፡፡ ይህ ማለት መጋቢነት ከሰዎች ትኩረትን ለማግኘት የምናደርገው አገልግሎት ሳይሆን ለእግዚአብሔር ስንል የምናደርገው አገልግሎት ነው፡፡...more29minPlay
December 30, 2022ስብከት አስራ ስዴስት ከላልች የተሻሇ ምን መሌካም ስራ አሊችሁን?ኢየሱስን ከተከተልን እና የእርሱ ባህርያት ካለን፣ ተለውጠን የዓለም ብርሃንና የምድር ጨው መሆን እንችላለን፡፡ ይህ ማለት እኛ ሌሎች ሰዎች እንደሚኖሩት ዓይነት ኑሮ አንኖርም ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ በልባችን ስለሚኖር እንደ ኢየሱስ እንሆናለን፡፡ ዓለም ከምታውቀው በላይ ፍቅር ይኖረናል፣ ዓለም ከምትረዳው በላይ የሆነ ፀጋና ምህረትን እናሳያለን፡፡ ይህንን በማድረግ በሰማይ እንደ አለው አባታችን እንሆናለን፡፡...more34minPlay
December 30, 2022ስብከት አስራ አምስት እግዚአብሔርን መምሰሌኢየሱስ “ጠላቶቻችሁን ውደዱ፣ ለሚያሳድዱአችሁ ጸልዩ” አለ፡፡ ከኢየሱስ ትምህርቶች ይህን ጥቅስ ለመተርጎምም ሆነ ለመተግበር እጅግ አስቸጋሪ ናቸው፡፡ እነዚህ ቃላት የሚያስተምሩት ትምህርት አለም ሰምታው የማታውቀውን ከፍተኛ ሥነ ምግባር ነው፡፡ ባለንጀራችንን እንዲሁም ጠላቶቻችንን መውደድ በእግዚአብሔር መሥፈርት የማይቻል ነው፣ ነገር ግን ይህንን ኢየሱስ በውስጣቸው ያለ እውነተኛ ደቀ መዛሙርት ይችላሉ፡፡ ኢየሱስ ይህንን ሃሳብ በደጉ ሳምራዊ ታሪክ ምሳሌነት አስተማረ፡፡...more31minPlay
December 30, 2022ስብከት አስራ አራት የእግዚአብሔር ሕግና የእናንተ ቃሌንግግራችሁ “አዎ ከሆነ አዎ” እንዲሁም “አይደለም ከሆነ አይደልም” ይሁን፡፡ በኢየሱስ የምድራዊ አገልግሎት ወቅት የነበሩ የኃይማኖት መሪዎች የሚፀኑ መኃላዎች እና የማይፀኑ መኃላዎች አሉ በማለት የመደቧቸው መኃላዎች ነበሩ፡፡ የእርሱ ደቀ መዛሙርት እንደ እግዚአብሔር ቃል የሚሆኑ ሰዎች እንዲሆኑና ቃላቸውን የሚያከብሩ እንዲሆኑ ኢየሱስ በአጽንዖት አስተማረ፡፡ “ዓይን ለአወጣ ዓይን፣ ጥርስ ለአወለቀ ጥርስ” የሚለው አባባል ፍትህን ለማግኘት ከባድ እርምጃ መወሰድ የለበትም ነገር ግን የተናደደ ወይም የተጎዳ ሰው መውሰድ ያለበት እርምጃ የተወሰነ መሆን አለበት፡፡...more28minPlay
December 30, 2022የአምሊካዊ ህግና ወንዴሞቻችንእኛ የምንኖረው ውድድር በበዛበት ዓለም ውስጥ ነው፡፡ እንዴት አድርገን ከእኛ “ተወዳዳሪዎች” ወይም ባላጋራዎች ጋር እንደምንኖር የኢየሱስ ትምህርት ግልጽ ያደርገዋል፡፡ የሚያስታርቁ ደቀ መዛሙርት ከጠላቶቻቸው ጋር ችግር ውስጥ መግባት የለባቸውም፡፡ ከተቃራኒ ፆታ ጋር ሊኖረን ስለሚገባ ግንኙነት ኢየሱስ አስተምሯል፡፡ በእርግጥ እንደ ጨውና እንደ ብርሃን መፍትሄ ለመሆን የወሲብ ፍላጎታችንን እንዴት መቆጣጠር እንዳለብን መማር አለብን፡፡ እግዚአብሔር ለጋብቻ ፍቺን በፍፁም እንዳላቀደ ኢየሱስ አስተማረ፡፡...more36minPlay
December 30, 2022ስብከት አስራሁሇት የአምሊካዊ ህግና ወንዴሞቻችንለአማኞች ጠንካራና በፍቅር የሆነ ግንኙነትን ማበልፀግና መጠበቅ ወሳኝ እንደሆነ ኢየሱስ አስተማረ፡፡ የኢየሱስ የምህረት ባህርይ ያላቸው ሰዎች በተግባር ማሳየት አለባቸው፣ ይህንን አለማድረግ የግል አምልኮአችንን ይጎዳል፡፡ ኢየሱስ “ወንድም” የሚለውን ሰው ማግለል የለብንም፡፡ እግዚአብሔርን የሚያስደስት ህብረት መመሥረት ከፈለግን ለወንድሞቻችና ለእህቶቻችን ያለን ቁጣና የጥላቻ መንፈስ መታረቅ አለበት፡፡...more21minPlay
FAQs about Amharic:How many episodes does Amharic have?The podcast currently has 221 episodes available.