Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
ኢትዮጵያን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ከተለያዩ እንግዶች እና በተለያዩት የዓለም ሀገሮች ከሚገኙት ወኪሎቻችን ጋ የምናካሂደውን እና በየሣምንቱ እሁድ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከአሥር ደቂቃ ላይ የሚተላለፈውን የውይይት ዝግጅት ያዳምጡ።... more
FAQs about እንወያይ | Deutsche Welle:How many episodes does እንወያይ | Deutsche Welle have?The podcast currently has 488 episodes available.
April 12, 2020ዉይይት፤ኮሮናን እንዴት እንከላከል ከሌሎችስ ምን ልምድን እንዉሰድ?«የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተኅዋሲዉን ስርጭት ለመቀነስ ይህን ያህል ሚና ይጫወታል ብለን መዘርዘር ባንችልም፤ አደጋዉን ለመቀነስ ሚና እንዳለዉ እሙን ነዉ። በኤች አይቪ ላይ የሰራነዉ ስህተት የኮሮና ላይ ልንደግም አይገባም። የፖለቲካ ልዩነት የሚነሳበት ጊዜ አይደለም። ሁሉም በጥምረት በጋራ የሚሰራበት ጊዜ ነዉ» ተወያዮች ያነስዋቸዉ ነጥቦች ናቸዉ።...more32minPlay
March 29, 2020ውይይት፤ ኮሮናን የመከላከል እርምጃዎች በኢትዮጵያየኮሮና ወረርሽኝ ባለጸጋ ድሀ፣ ጉልበተኛ ደካማ፣ ሊቅ መሀይም ሳይል በዓለማችን በአስደንጋጭ ሁኔታ በፍጥነት መሰራጨቱንና የሰዎችን ሕይወት ማጥፋቱን ቀጥሏል። የኢትዮጵያ ዝግጅት እና የበሽታው ሥርጭት የዛሬው እንወያይ የሚያተኩርባቸው ጉዳዮች ናቸው።...more31minPlay
March 23, 2020የኮሮና ወረርሽኝን ለመግታት ኢትዮጵያ ምን ማድረግ ይገባታል?የኢትዮጵያን የጤና አገልግሎት በቅርበት የሚያውቁ የሕክምና እና የማኅበረሰብ ጤና ባለሙያዎች ጣልያን፤ ቻይና እና ኢራንን የመሳሰሉ አገሮች ያመሰው የኮሮና ወረርሽኝ 110 ሚሊዮን ገደማ ዜጎች ባሏት አገር ቢስፋፋ የሚፈጠረው ቀውስ አስግቷቸዋል። 15 ሺሕ ገደማ ሰዎችን ለገደለው የኮሮና ወረርሽኝ ኢትዮጵያ እንዴት መዘጋጀት ይገባታል?...more32minPlay
February 10, 2020ዉይይት፤ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በኢትዮጵያ ለምን?በኢትዮጵያ የፖለቲካ ለዉጥ እስኪደረግ ድረስ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ሕግና ስርዓትን በማወክ ሰዎችን በማንገላታት የግል መገናኛ ዘዴዎችን በማፈን፤ የመናገር ነፃነትን በመገደብ ይወቀስ የነበረዉ መንግሥት ነበር። አሁን ደግሞ የተለያዩ የፖለቲካ፤ የጎሳ፤ የሃይማኖት ቡድናት ወይም ግለሰቦች ናቸዉ።...more34minPlay
February 02, 2020የክረምቱ ምርጫ፦ ሥጋት እና ፈተናለውይይት በቀረበው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ምርጫ ከተካሔደ ኢትዮጵያውያን ከስድስት ወራት ከአስራ አምስት ቀናት ገደማ በኋላ ተወካዮቻቸውን መርጠው መንግሥት ለመመሥረት ድምጽ ይሰጣሉ። ከዝናባው ክረምት ባሻገር የተካረረው የፖለቲካ ኃይሎች ቅራኔ ከእምነት እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የዘለቀው የጸጥታ ቀውስ ነፃና ፍትኃዊ ምርጫ ለማካሔድ ያስችላሉ?...more31minPlay
February 02, 2020ውይይት፦ ምርጫ በክረምትበሺሕዎች የሚቆጠሩ የምርጫ አስፈፃሚዎች መልምሎ፤ አሰልጥኖ አሰማርቶ በክረምት ምርጫ ማካሔድ ምን ያክል ይሳካል? ለፖለቲካ ፓርቲዎች እና ምርጫውን ለሚከታተሉ የሲቪክ ማኅበራትስ ምን ፈተና ይዞ ይመጣል? የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጸጥታ እና መረጋጋት በእርግጥ ምርጫ ለማካሔድ ያስችላል?...more31minPlay
FAQs about እንወያይ | Deutsche Welle:How many episodes does እንወያይ | Deutsche Welle have?The podcast currently has 488 episodes available.