ሙዚቃ የልጅነት ህልሙ ነዉ። በኦሮምኛ፣በአማርኛ ፣በሶማልኛ፤ በኮንሶኛ፣በቡርጅኛና በጌዴወ ቋንቋወች አቀንቅኗል። ብዙ ብሔርና ብሄረሰቦች ባሉበት አካባቢ ማደጌ ለዚህ ረድቶኛል ይላል።
ሙዚቃወቹ የቋንቋዉ ተናጋሪ ያልሆኑትን ሳይቀር ቀልብ የሚገዙ ናቸዉ።ፉላንዬ፣ጃልጅሎ፣ሹቤ ዳኢ መለዌ ከተወዳጅ ሙዚቃወቹ መካከል ጥቂቶቹ ናቸዉ።ቱባዉን የብሔር ብሄረሰቦች ባህል የሚያሳዩት የሙዚቃ ቪዲዮወቹም ለድምፃዊዉ መለያወቹ ናቸዉ።የዛሬዉ የመዝናኛ ዝግጅት እንግዳችን ድምጻዊ አቡሽ ዘለቀ።