ዜና መጽሔት

ዜና መጽሔት

Download on the App Store

ዜና መጽሔት episodes

  • የዜና መጽሔት፤ ኅዳር 16 ቀን፣ 2018 ዓ.ም
    የዜና መጽሄት እና ሳምንታዊ መሰናዶዎችን በቅደም ተከተል ያስደምጣል። የዜና መጽሔታችን በዛሬ ጥንቅሩ የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ገዚው ብልጽግናን ለመዋሃድ መወሰኑ እና ተቃዉሞ ፤ በአፋር ክልል ኤርታሌ በሺህ ዓመታት ውስጥ የተከሰተው የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ እና ያስከተለው መዘዝ፣ በሥራቸው የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ኢትዮጵያዉያን ባለሙያዎች መሸለማቸው፤ የተሰኙ ዘገባዎች ቀርበዉበታል።
    22 min
  • የኅዳር 15 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዜና መፅሄት
    የዛሬው የዜና መጽሔት ፤ ፤የኢትዮጵያ ሙስሊምን ከትምህርት እና ሀገራዊ ተሳትፎ በማራቅ ዘላቂ ልማት አይኖርም ሲል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ማስታወቁ ፤ቡለን ወረዳ ባለፈው ቅዳሜ ማለዳ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት በርካታ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸዉ ፤ እንዲሁም በአዉሮጳ ኅብረት ተቃዉሞ የገጠመዉ የአሜሪካ የ 28 ነጥብ የሰላም እቅድ ለዩክሬይን የተሰኙ ርዕሶችንበስፋት ያስቃኘናል።
    18 min
  • የኅዳር 12 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዜና መፅሄት
    በዛሬው የዜና መጽሔት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለመጀመሪያ ጊዜ የ520 ሚሊዮን ዶላር ስምንት ጨረታዎች ይፋ ማድረጉ፤ደቡብ አፍሪቃ የምታስተናግደው በአፍሪቃ የመጀመሪያው የቡድን ሀያ ጉባኤ፤ የዓለም ባንክ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸዉ ሃገራት ለጤና ጥበቃ የሚመድቡት ገንዘብ እጅግ ዝቅተኛ ነዉ ማለቱ እንዲሁም፤ ፓሪስ ላይ የተካሄደዉ የጀርመን ፈረንሳይ ትብብር ጉባኤየተሰኙ ርዕሶችን ያስቃኘናል።
    26 min
  • የሕዳር 11 ቀን 2018 የዜና መፅሔት
    በኢትዮጵያ የፀጥታ እና የፖለቲካ ጥያቄዎች መልስ ካላገኙ ቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ምርጫ ሊሆን አይችልም ሲሉ የኦፌኮ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ለዶቼቬለ ተናግረዋል። በደቡብ ወሎ ዞን ሐይቅ እና ዉጫሌ ከተሞች አቅራቢያ የተጠለሉ ተፈናቃዮች አቤቱታ አቅርበዋል። እናት ፓርቲ ፣ከተጣመርኩበት «ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት» ከተባለው ቅንጅት፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰርዞኛል ሲል ወቅሷል። እነዚህና የአውሮፓ ኅብረት አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ዛሬ ያካሄዱት ስብሰባ የዛሬው የዜና መጽሔት ዝግጅታችን የሚያተኩርባቸው ጉዳዮች ናቸው።
    25 min
  • የህዳር 10 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    የዕለቱ መጽሔታችን ሦስት ርዕሰ ጉዳዮችን በቅደም ተከተል ያስደምጣል። ከምርጫ በፊት ሰላም እንዲሰፍን ፣የታሰሩ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች እንዲፈቱ መጠየቁ፣ ዩናይትድ ስቴትስና ሳዑዲ አረቢያ በንግድ፣ በቴክኖሎጂ፣ በጦር መሳሪያ ሽያጭና በመከላከያ ያላቸዉን ትብብር ለማጠናከር መስማማታቸው፣ እንዲሁም የጄፌሪ ኤፕስታይን የወሲብ ቅሌት ሰነድ ይፋ እንዲሆን መወሰኑ እና አንድምታውን የተመለከቱ ዘገባዎች በዝርዝር የሚቀርቡ ርዕሰ ጉዳዮቻችን ናቸው ።
    18 min
  • የኅዳር 8 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክክር የገጠሙት ተግዳሮቶች “ፖለቲካዊ መፍትሔ ያስፈልጋቸዋል”መባሉ
    ቢያንስ አምስት ኢትዮጵያዊያን በአንድ ሳምንት ውስጥ ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ተገድለዋል
    የጋዜጠኛ እና ደራሲ ዜናነህ መኮንን 1ኛ ዓመት መታሰቢያ
    17 min
  • የሕዳር 5 ቀን 2018 የዜና መፅሔት
    የዓለም ዜናን በሚከተለው የዜና መጽሔት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጂንካ ከተማ መከሰቱ የተሰማው የ«ቫይራል ሄመሬጂክ ፊቨር» ጉዳይ ፣ በታንዛኒያ ምርጫ ከደረሰው ግጭት በኋላ ፖሊስ ስለወሰዳቸው ርምጃዎች የወጡ አዳዲስ መረጃዎች እንዲሁም በጀርመን የታሰበው ፈቃደኛነትን መሠረት ያደረገ ብሔራዊ ውትድርና የተሰኙት ርዕሶች ይተነተናሉ
    16 min
  • የሕዳር 4 ቀን 2018 ዓ.ም የዜና መፅሔት
    በዜና መፅሔቱ በጅንካ ከተማ የተከሰተው በሽታ፤ ፈረንሳይ የዛሬ 10 ዓመት የበርካቶችን ሕይወት የቀጠፉ የሽብር ጥቃቶች የተፈጸሙበትን ዕለት አስባ መዋሉዋ እንዲሁም የኢራንና የዓለም የአቶሚክ ተቆጣጣሪ ድርጅት ዉዝግብን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል።
    20 min
  • የህዳር 3 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    የዓለም ዜናን በሚከተለው የዜና መፅሔት ፣ ተቃውሚ ፓርቲዎች ከመጭው የኢትዮጵያ ምርጫ በፊት ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር መጠየቃቸውን ፣ ኢትዮጵያ COP32 እንድታስተናግድ መመረጧን ፣ የተባበሩት አረብ ኢመሬቶች በሌሎች ሀጋራት ያላትን ተፅዕኖ እንዲሁም የትራምፕ አስተዳደር አዳዲስ የስደተኞች ፖሊሲዎችና አንደምታቸውን የሚያስቃኙ አራት ዘገባዎች አሉን
    19 min

About ዜና መጽሔት

From the publisher's feed

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ…