ዜና መጽሔት

ዜና መጽሔት

Download on the App Store

ዜና መጽሔት episodes

  • በሺዎች የሚቆጠሩ ቤተ እስራኤላዊያን እስራኤል የገቡበት ዘመቻ ሰሎሞን ሲታወስ
    15 ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን አይሁዶች ወይም ቤተ እስራኤላዊያን በ36 ሰዓታት ውስጥ ከአዲስ አበባ እስራኤል የገቡበት ዘመቻ ሰሎሞን 34 ዓመት ሞልቶታል።ከቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በቀጥታ ቴላቪቭ በ35 የአውሮፕላን በረራዎች ወደ እስራኤል የገቡት ቤተ እስራኤላዊያን ዛሬ በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ላይ በጎ ድልድይ መሆናቸውም ተገልጿል።
    4 min
  • የግንቦት 22 ቀን 2017 የዜና መፅሔት
    የዜና መጽሔት ዝግጅታችን፤በአፋር ክልል ወደ ትግራይ ለሚሄዱ የጭነት መኪናዎች ኬላዎች ተዘግተዋል መባሉን፤ የመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ችግር ሊያካትት የሚችለውን የብሄራዊ ምክክር ኮሚሽን አጀንዳ ማሰባሰብያ ውይይትን፤እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ ቤተ እስራኤላዊያን እስራኤል የገቡበት ዘመቻ ሰሎሞንን ትውስታ፤የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል ።
    13 min
  • ለሶስት ቀናት የሚቆየው የብሄራዊ የውይይት ኮሚሽን አጀንዳ ማሰባሰቢያ ውይይት
    የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የትግራይ ክልል በአገራዊ ምክክር ሂደት ተሳታፊ እንዲሆን ኮሚሽኑ ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር እና ባለድርሻ አካላት ጥሪ አቀረበ፡፡ኮሚሽኑበኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ለሚገኙ ታጣቂ ኃይሎች እና እስካሁን በምክክር ሂደቱ መሳተፍ ላልጀመሩ የፖለቲካ ድርጅቶችም የተሳትፎ ጥሪ አቅርቧል፡፡
    4 min
  • የግንቦት 21 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    *የ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያ ላይ ላነሱት ወቀሳ ምላሽ ሰጠ
    *የኢትዮ-ኤርትራ ቀጣይ እጣፈንታ
    *በወሎ አካባቢዎች የተማሪዎች እና መምህራን ስደት በከፍተኛ መጠን ጨመረ ተባለ
    *የማኀበረ ግዩራን የሽልማት ሥነ ስርዓት
    18 min
  • የግንቦት 20 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    የግንቦት 20 በዓል በትግራይ ክልል ብቻ፤
    ስለ ግንቦት 20 የተሰጡ አስተያየቶች፤
    «ሰሚ አጣን» የሚሉት በሃድያ ዞን የሌሞ ወረዳ ነዋሪዎች፤
    የገራዶ ተፈናቃዮች «ለልማት በሚል» ዳግም መፈናቀላቸው
    የአውሮጳ ኅብረት የልማትና ትብብር ሚኒስትሮች ስብሰባና አጀንዳቸው
    20 min
  • የዜና መጽሔት፤ ግንቦት 19 ቀን 2017
    የዜና መፅሔት ጥንቅራችን የኤርትራ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ባለፈዉ ቅዳሜ ያደረጉት ንግግር የኦሮሞ ፖለቲከኞችን ማስቆጣቱን የሚቃኘዉን ዘገባ ያስቀድማል።የቀድሞዉ የትግራይ ጊዚያዊ ፕሬዝደንት ጌታቸዉ ረዳ የሚመሩት አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ለመመሥረት ፈቃድ ማግኘቱን የሚቃኘዉ ዘገባ ተከትሎ አማራ ክልል የወባና የኮሌራ በሽዎች ሰዎች መግደል-መያዛቸዉን የሚዳስሰዉ ያሰልሳል።
    14 min
  • የግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ጠንካራ ትችት የሰነዘሩት የኤርትራዉ ፕሬዚዳንት
    በዋግ ህምራ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደር በድርቅና በምግብ እጥረት እየተፈናቀሉ ያሉት አርሶደሮች ጉዳይ
    የሙርሌ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ሰዎች መገደላቸዉ፤ እንዲሁም
    የኤምፖክስ በሽታ ተዋሲ በኢትዮጵያ መገኘቱ ተረጋግጧል መባሉ
    17 min
  • የዐርብ ግንቦት 15፣ ቀን 2017 ዓ.ም ዜና መጽሄት
    የዜና መፅሔት ጥንቅራችን የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ከሐገሪቱ የጤና ሚንስቴር ጋር ለመደራደር መዘጋጀታቸዉን ከአድማ እስራቱ መቀጠል ጋር ያሰባጠረዉን ዘገባ ያስቀድማል።ዜና መፅሔቱ በኒ ሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጋብ ብሎ የነበረዉ የታጣቂዎች ጥቃት እንደገና ማገርሸቱን የሚያወሳዉን ዘገባ አስከትሎ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዉጪ ሸቀጥ ለሚያስገቡና ወደ ዉጪ ለሚጓዙ የሚፈቀደዉን የዉጪ ምንዛሪ መጠን መጨመሩን በሚቃኘዉ ዘገባ ያሳርጋል።
    14 min
  • የግንቦት 14 ቀን 2017 ዓ,ም የዜና መጽሔት
    ጤና ባለሞያዎች ጥያቄዎች ትኩረት እንዲሰጣቸውና ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኙ ኢሰመኮ ማሳሰቡ፤
    የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በሽሬ ቆይታቸው ስለተፈናቃዮች መናገራቸው፤
    የአውሮጳ ኅብረትና አፍሪቃ አገሮች የሚኒስትሮች ስብሰባ፤
    ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የደቡብ አፍሪቃ አቻቸውን ማሳጣታቸው
    18 min

About ዜና መጽሔት

From the publisher's feed

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ…