Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
May 21, 2025የግንቦት 13 ቀን 2017 ዜና መፅሔትየኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትናንት የተወያየበት፣ የውጭ ዜጎችን የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት የሚያደርገው ረቂቅ ሕግ ላይ አዎንታም፣ አሉታዊም አስተያየቶች እየተሰጡ ነው።መቐለ የሚገኙ ፍርድቤቶች የስራ ማቆም አድማ፣ ዛሬም ቀጥሏል። በወሊሶ ከተማና አከባቢው ኤሌክትሪክ እና ውሃ ከተቋረጠ ሦስት ሳምንት ሊሆን ነው። እነዚህና የኢትዮ አሜሪካ ንግድ ምክር ቤት የፖሊሲ አስተያየትና የዕውቅና ሽልማት የዛሬው ዜና መጽሔት የሚመለከታቸው ጉዳዮች ናቸው19 minPlay
May 19, 2025የግንቦት 11 ቀን 2017 ዓ.ም የዜና መጽሔትየቀጠለው የሐኪሞች ሥራ ማቆም አድማ፣ ህወሓት በመንግሥት ላይ ያቀረበዉ ወቀሳ ፣የጤና አገልግሎት ፈላጊዎች ቅሬታ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል፣ የአማራ ክልል የጤና ባለሙያዎች ስራችንን እየሰራን ትግላችንን እንቀጥላለን ማለታቸው ሶማሊላንድ ከሶማሊያ መነጠሏን ያወጀችበት 34ኛ ዓመት በዛሬው የዜና መጽሔት ትንታኔ የሚቀርብባቸው ጉዳዮች ናቸው19 minPlay
May 16, 2025የግንቦት 08 ቀን፣ 2017 ዓ.ም ዜና መጽሔትየዕለቱ መጽሄተ ዜና ትንታኔያችን በዋናነት የሚያተኩረው ኢትዮጵያ ውስጥ የጤና ባለሞያዎች ባነሷቸው ጥያቄዎች እና በመንግሥት ርምጃ ላይ ነው ። የቀጠለው የጤና ባለሙያዎች ጥያቄና የጤና ሚኒስቴር ምላሽ፤ ግቢ ልቀቁ የተባሉት ኢንተርን ሀኪሞች እና ሬዚደንቶች የተሰኙ ዘገባዎች እንዲሁም ሳምንታዊዎቹ አንድ ለአንድ እና ከወጣቶች ዓለም በጤና ባለሞያዎች ጥያቄ ላይ ያጠነጥናሉ ። በሕወሓት እና በፌዴራል መንግስት መካከል ስላለው ፍጥጫ የሚያወሳ ዘገባ፤ እና ስለ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የመካከለኛው ምሥራቅ ጉብኝት አንድምታም ቃለመጠይቅ አካተናል ።17 minPlay
May 15, 2025የግንቦት 7 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔት20 ዓመት የሞላው የ1997 ምርጫእንዴት ይታወሳል? በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት ችግር ምን ያህል ተፈትቷል? ህወሓት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከከፖለቲካ ፓርቲነት የተሰረዘበትን ውሳኔ መኮንነኑና ውሳኔው በህወሓትና በፌደራሉ መንግሥት ግንኙነት ላይ የሚያሳድረው ተጽእኖ እንዲሁም የኦሮሞ ፌደራሊስ ኮንግረስ አቤቱታ ዜና መጽሔት የሚያስቃኘን ጉዳዮች ናቸው።20 minPlay
May 14, 2025የረቡዕ ግንቦት 6 ቀን፣ 2017 ዓ.ም ዜና መጽሄትየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት)ን ከፖለቲካ ፓርቲነት መሠረዙን ዛሬ አስታውቋል። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን በተከሰተ ግጭት አንድ የፀጥታ አባልን ጨምሮ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን የአካባቢዎው ነዋሪዎች ተናግረዋል። እነዚህና የኮሪደር ልማትና የሸገር ከተማ ነዋሪዎች አቤቱታ እንዲሁም የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የዶናልድ ትራምፕ የመካከለኛው ምሥራቅ ጉብኝትና ከአረብ ሀገራት ጋር የፈጸሟቸው ውሎች ዜናውን በሚከተለው የዜና መጽሔት የሚተነተኑ ጉዳዮች ናቸው።24 minPlay
May 13, 2025የግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔትየዜና መፅሔት ጥንቅራችንየኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች የጠሩት የሥራ ማቆም አድማ የመደረግ-አለመደረጉን ተቃርኖ የሚቃኘዉን ዘገባ ያስቀድማል።ዜና መፅሔቱ ወደ ትግራይ የሚጓዙ የዉጪ ዜጎች እገዳ ተጣለባቸዉ መባሉ፣ ጋምቤላ ዉስጥ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች መገደላቸዉን የሚቃኙ ዘገቦችን አሰምቶን የአሜሪካዉ ፕሬዝደንት በሶስት የአረብ ሐገራት የሚያደርጉትን ጉብኝት የሚመለከት አጭር ቃለ መጠይቅ አለዉ።20 minPlay
May 12, 2025የዜና መጽሔት፤ ግንቦት 4 ቀን 2027 ሰኞበቀጠለው የህክምና ባለሞያዎች የደሞዝ ይጨመርልን የአደባባይ ጥያቄb፤ ደሴ ውስጥ የህክምና ባለሞያዎች ስለመታሰራቸው ፤ የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የህክምና ባለሞያዎችም የደሞዝ ይጨመርልን ጥያቄያቸውን ዛሬም ከስራ በፊት ማሰማታቸዉ እንዲሁም ህወሓት በምርጫ ቦርድ ላይ ያቀረበው ስሞታ የዜና መጽሔት ርዕሰ ጉዳያችን ነው።18 minPlay
May 09, 2025የግንቦት አንድ ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔትየዛሬው የዜና መጽሔት ዝግጅታችን፤ በከፋ ችግር ምያንማር ከነበሩ ኢትዮጵያውያን መካከል 82ቱ ዛሬ አዲስ አበባ መግባታቸው ፣ በኢትዮጵያ የህክምና ባለሞያዎች ተግዳሮት፣ ለአዲሱ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የመቐለ ልደታ ማርያም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መልካም ምኞት እና አዲስ ርዕሰ ሊቃነጳጳሳት የተሾመላት የካቶሊክ ቤተክርስትያን እና የዛሬ የቫቲካን ውሎ ላይ ያተኩራል።17 minPlay