ዜና መጽሔት

ዜና መጽሔት

Download on the App Store

ዜና መጽሔት episodes

  • የሚያዚያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    በዜና መጽሔት ዝግጅታችን ፣በምስራቅ ወለጋ ዜን ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 15 ሰዎች መገደላቸው ፤ የኢትዮጵያ ፖሊስ የአዲስ ስታንዳድርን «መረጃ ወይም ዳታ እወስዳለሁ» ማለቱ ፤ የዩናይትድ ስቴትስ የፌዴራል ፍርድ ቤት የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮን ጨምሮ ከስርጭት የወጡ የመገናኛ ብዙኃን ወደ ስራ እንዲመለሱ ያስተላለፈው ዉሳኔ እንዲሁም የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስን ህልፈት ተከትሎ የዓለም መሪዎች ያስተላለፏቸው መልዕክቶችን የተመለከቱ ዘገባዎች በዝርዝር የሚቀርቡ ርዕሰ ጉዳዮቻችን ናቸው ።
    21 min
  • የሚያዝያ 14 ቀን 2017 ዓ.ም የዜና መፅሔት
    በምዕራብ ኦሞ ዞን በተከሰተ የአባ ሰንጋ በሽታ ሳቢያ ሰባት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየበረታ የመጣው የወባ በሽታ ነዋሪዎችን ሥጋት ላይ ጥሏል፡፡ የውኃ እጥረት የጋምቤላ ነዋሪዎችን በመፈታተን ላይ ይገኛል። ከባሮ ወንዝ አጠገብ የምትገኘው ጋምቤላ የክልላዊ መንግሥት መቀመጫ ብትሆንም አንድ ጀሪካ ከወንዝ የተቀዳ ውኃ እስከ 20 ብር ይሸጥባታል። እነዚህ ዘገባዎች በዛሬው ዜና መጽሔት ይቀርባሉ። ሣ
    18 min
  • የሚያዚያ 10 2017 የዜና መፅሔት
    በዛሬዉ የዜና መፅሔት ጥንቅራችን በሰሙነ ሕማማት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የምትጠቀምባቸዉ ያሬዳዊ የዜማ ስልቶች በተለየ መልኩ አገልግሎት ይከወኖባቸዋል። አዲሱ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር በጦርነቱ ወቅት በትግራይ ለተፈፀመው ወንጀሎች ተጠያቂነት እንዲረጋግጥ እንዲሰራ ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች የተባለ የመብቶች ተሟጋች ድርጅት ጥሪ አቀረበ።
    9 min
  • የሚያዙያ 9 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    የዜና መፅሔት ጥንቅራችን፣ የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃሐን ደንብ ፖለቲከኞችን ለመሾም በሚፈቅድ መልኩ ዛሬ ዳግም መሻሻሉን የሚያወሳዉን ዘገባ ያስቀድማል።የፋሲካ በዓልን ከወላጅ-ወዳጆቻቸዉ ጋር ለማክበር ከየአካባቢዉ ወደ አማራ ክልል መጓዝ የፈለጉ አማኞች መጓዝ አልቻሉም። ምክንያት ግጭት ነዉ።ሁለተኛዉ ዘገባችን ይቃኘዋል።የአዲስ አበባ ፖሊስ የኢትዮጵያ ሕዝብን ባሕልና ወግ የሚጥስ ምስል በማሕበራዊ መገናና ዘዴዎች አሰራጭቷል ያለዉን ግለሰብ ማሰሩን የሚቃኝ ዘገባም አለን።የሱዳን ጦርነት፣ የለንደን ጉባኤተኞች ጥሪ ሌለኛዉ የዜና መፅሔት ርዕሳችን ነዉ።
    18 min
  • DW Amharic የሚያዝያ 8 ቀን 2017 የዜና መጽሔት
    የትግራይ ክልል መምህራን ደሞዝ እንዲከፈላቸው የክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በየነ፣ የድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ ከአራት መቶ ኪሎ ግራም በላይ አደንዛዥ እፅ አስወገደ፣ በውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያውያን ድርጅቶች የትብብር መድረክ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ንዋየ ቅዱሳትና መጻህፍት የአዕምሯዊ ንብረት ባለቤትነት
    18 min
  • DW Amharic የሚያዝያ 07 ቀን 2017 የዜና መጽሔት
    የኢትዮጵያ መንግሥት የኢኮኖሚ ዕድገት ዕቅድና የባለሙያ አስተያየት፣ ኢትዮ-ኤይድ፤ የኢትዮጵያ ለአደጋ ስጋት ምላሽ፣ በአዲስ አበባ ቅሬታ ያስነሳው “የመስጂድ አጥር መፍረስ” ፣ የፍልስጤምና ያውሮጳ ህብረት ባለሥልጣናት ውይይት
    19 min
  • የሚያዚያ 6 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    በዛሬው ዜና መጽሔት ዝግጅት
    በአማራ ክልል የተከሰተ የነዳጅ እጥረት
    የህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ፓርቲያቸው ከኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት ጋር በተፈራረመው ግጭት የማቆም ሥምምነት ላይ የአፍሪካ ኅብረት አሸማጋዮች በአፋጣኝ ተሰብስበው እንዲወያዩ ጥሪ ማቅረባቸው
    በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እየጨመረ የመጣው የኤች አይ ቪ ተህዋሲ ሥርጭት
    በአማራ ክልል በኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶ በተፈጸመ ሥርቆት ደሴን ጨምሮ በተወሰኑ አካባቢዎች ኤሌክትሪክ መቋረጡ።
    ህወሓት ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች በሰላማዊ ትግል እንዲጸኑ እና ሌሎች አማራጮች እንዳይከተሉ ጥሪ ማስተላለፉ ላይ ያተኮሩ ዘገባዎች ይቀርባሉ።
    18 min
  • የሚያዝያ 3 ቀን 2017 ዓ,ም የዜና መጽሔት
    በአማራ ክልል የሚደረገዉ ግጭት በጤና ባለሙያዎች ስራ ላይ ያደረሰዉ ጫና
    የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄ
    በጦርነት ከቤት ንብረታቸዉ ተፈናቅለዉ ከነበሩ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች የተወሰኑት ወደየቀያቸዉ ቢመለሱም
    አሁንም ከሥጋትና ችግር አለመላቀቃቸዉን የሚያወሳዉን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዘገባ
    14 min

About ዜና መጽሔት

From the publisher's feed

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ…