ዜና መጽሔት

ዜና መጽሔት

Download on the App Store

ዜና መጽሔት episodes

  • የሚያዚያ 1 ቀን 2017 ዓመት የዜና መፅሔት
    በአዲስ አበባ ጎጃም መስመር በተደጋጋሚ መንገደኞች መታገታቸው መቀጠሉ፤ ትግራይ ክልል አዲስ የጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ተሾሞለታል፤ የክልሉ ነዋሪዎች ከአዲሱ አስተዳደር ምን ይጠብቃሉ? አስተያየታቸውን አሰባስበናል፤የግንባታ ዕቃዎች እጥረትና ዋጋ መናር እንዲሁም የመንገዶች መዘጋት ያስከተለው ችግር እንዲሁም በዩኔስኮ የተመዘገበው ዓመታዊው የሸዋል ኢድ በዓል አከባበርን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል የዜና መጽሔት።
    16 min
  • የዜና መጽሔት፤ መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም
    የዜና መፅሔት ጥንቅራችን፣ ጅቡቲ ለኢትዮጵያ ባለሐብቶች መጋበዟን የሚያወሳዉን ዘገባ ያስቀድማል። የኢትዮጵያ መንግስት ጦር አንድ ኦሮሞ ነፃ አዉጪ ሠራዊት ከፍተኛ አዛዥ ገደልኩ ማለቱን የሚቃኘዉን ዘገባ ተከትሎ፣ ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዉዝጥ 10 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸዉን የሚቃኘዉ ያሰልሳል።ላለፉት ሁለት ዓመታት የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝደንት ጄኔራል ታደሰ ወረደ የጊያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝደንት ሆነዉ መሾማቸዉን የሚዳስስ ዘገባም አለዉ።
    17 min
  • የመጋቢት 29 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    --በመንግሥት እና በፋኖ መካከል የሚካሄደዉ ጦርነት የአማራ ክልል ንግድን ማቀዛቀዙ
    --በዲራሼ ወረዳ በተቀሰቀሰ ግጭት በትንሹ 11 ሰዎች ተገደሉ
    --ወደ ትምህርህርት ገበታ ያልተመለሱት 1 ነጥብ 2 ሚልዮን የትግራይ ህፃናት እና ታዳጊዎች
    --የጅቡቲ የኢኮኖሚ እና የቱሪዝም ማዕከል የመሆን ጥረት
    18 min
  • የመጋቢት 26 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    አማራና አፍር ክልል አዋሳኝ ላይ የሚታየዉ ምክንያት የሌለዉ ፀብ፣
    በአስከፊ ኹኔታ እና ሥጋት ምያንማር ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን ጥሪ እና
    አጀንዳ ማሰባሰብ በአማራ ክልል ነገ ይጀመራል መባሉ ዜና መጽሔት ከሚያስቃኘን ጉዳዮች መካከል ይገኙበታል።
    17 min
  • የመጋቢት 24 ቀን 2017 ዜና መፅሔት
    በዕለቱ መጽሄተ ዜና አምስት ጉዳዮችን እናስተነትናለን ። የኢትዮጵያ ያለፉት ሰባት ዓመታት እንዴት ይታወሳል? የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አዲስ አወቃቀር ጉዳይ፤ የጋዜጠኞች፣ የሞያው እና የተቋማቱ ደኅንነት በኢትዮጵያ፤ በፈረንሳይ ብሔረተኛ ፓርቲና መሪዋ ማሪ ሌፐን ላይ የተላለፈ የፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲሁም የሱዳን ጦር «ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ትጥቅ እስኪፈታ እንፋለማለን» ሲል ስለመዛቱ የሚሉ ዘገባዎችም በተከታታይ ይቀርባሉ
    21 min
  • የመጋቢት 23 ቀን 2017 ዓም የዜና መጽሔት
    የዜና መፅሔት ጥንቅራችን፣ በሰሜን ኢትዮጵያዉ ጦርነት ግፍ ተዋለብን የሚሉ የትግራይ ተወላጆች የመሰረቱትን ክስ የሚያወሳዉን ዘገባ ያስቀድማል።የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ ማሻሻና የፕሪቶሪያዉ ሥምምነትን አተረጓጎም የሚያወሱት ዘገቦች ተከታትለዉ ተሰምተዉ የደቡብ ኢትዮጵያና የኦሮሚያ ባለሥልጣናትን ሥምምነት በሚያወሳዉ ያሳርጋል።
    18 min
  • የመጋቢት 19 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    -- በአማራ ክልል የሚታየዉ ቀዉስ በኤች አይ ቪ ህክምና አሰጣጥ ላይ ጫና ፈጠረ መባሉ
    -- የኦሮሚያ ወቅታዊ ፀጥታ፤ ተስፋና ተግዳሮቱ
    --የአዲስ አበባ ከተማ የምሽት ስራ ሰዓት መራዘም
    እንዲሁም
    -- በኢትዮጵያ የሚታየዉ የዋጋ ግሽበት መረጋጋት አሳይቷልል?
    16 min

About ዜና መጽሔት

From the publisher's feed

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ…