Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ... more
FAQs about ዜና መጽሔት:How many episodes does ዜና መጽሔት have?The podcast currently has 1,995 episodes available.
April 08, 2024DW Amharic የመጋቢት 30 ቀን 2016 ዜና መጽሔትበአማራ ክልል ፍኖተ ሰላም ከተማ ገበያ መሀል ባለፈው ቅዳሜ በተከሰተ ፍንዳታ 32 ሰዎች መቁሰላቸውን የምዕራብ ጎጃም ዞን አስተዳዳሪ ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። በፍንዳታው ጉዳት የደረሰባቸው አብዛኞቹ ለገበያ ከገጠር ወደ ፍኖተ ሰላም ከተማ የተጓዙ እናቶች እንደሆኑ አቶ እድሜዓለም አንተነህ ገልጸዋል። በኦሮሚያ ክልል የበረታውን ግጭት እና የመንግሥት ጥሪ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ደጋፊዎች ሰልፍ እና የተቃዋሚዎችን ትችት እንዲሁም የሐዋሳ ሐይቅ የገጠመውን የብክለት ሥጋት የተመለከቱ ዘገባዎች በዜና መጽሔት ተካተዋል።...more16minPlay
April 05, 2024የመጋቢት 27 ቀን 2016 ዓም የዜና መጽሔትተከሳሽ የምክር ቤት አባላት ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረቡከደብረ ብርሀን ከተማ የተመለሱ የተፈናቀሉ ሰዎች ቅሬታሰላማዊ ሰልፍ የወጡ የመቐለ ዩኒቨርሰቲ ተማሪዎች በፖሊስ የሐይል እርምጃ ተበተኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለሕዳሴ ግድብ 19 ቢሊዮን ብር ማዋጣቱ ተጠባቂው የበልግ ወቅት የዝናብ ይዞታ...more20minPlay
April 04, 2024የመጋቢት 26፣2016 የዜና መፅሔት-የኢትዮጵያ መንግስት ጦር ኃይል በአማራ ክልል አድርሶታል ተብሎ የሚጠረጠረዉን የጦር ወንጀል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንዲያጣራ ሁዩማን ራይትስ ወች ጠየቀ።የመብት ተሟጋቹ ድርጅት እንደሚለዉ የመንግስት ወታደሮች አማራ ክልል መራዓዊ ከተማ ዉስጥ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች ገድለዋል።ሶማሊያ ዛሬ በሞቃዲሾ የኢትዮጵያን አምባሳደር አባርራለች።ግጭትና ጥቃት ያልተለየዉ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የ30 ዓመታት ጉዞን የሚያሳይ ያለውን የሦስት ቀናት አውደ ርዕይ ከትናንት ጀምሮ በማካሄድ ላይ ነው።...more25minPlay
April 03, 2024የመጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም. የዜና መጽሔትየኢትዮጵያ መንግሥትና የአይ ኤም ኤፍ የባለሙያዎች ድርድር መክሸፍየብልፅግናና የህወሓት መሪዎች ዉይይት፣ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች አስተያየት ሥለ የመኖሪያ ቤት ሕግ፣ነዳጅ እጥረት በአዲስ አበባ ያልተሰማው የደንጣ ዱባሞ ማኅበረሰብ ደምፅ...more22minPlay
April 02, 2024የመጋቢት 24፣2016 ዜና መፅሔት-የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመኖሪያ ቤት አከራይና ተከራዮችን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ያገለግላል ያለዉን አዲስ ሕግ አፀደቀ።ምክር ቤቱ «የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ» ያለዉ ሕግ በአከራይ፣ በተከራይና በመንግስት መካከል ግልፅነትና ተጠያቂነትን ለማስፈን ይረዳል ተብሏል።ዛሬ በመላው ኦሮሚያ ትላልቅ ከተሞች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. ወደ ስልጣን የመጡበት እና በስድስት ዓመታት የስልጣን ዘመናቸው አሳኩ የተባሉ ስራዎችን የሚያበረታታ የድጋፍ ሰልፍ ተደርጓል፡፡...more18minPlay
March 29, 2024ዜና መጽሔት፦ መጋቢት 20 ቀን 2016 ዓ.ም.በዜና መጽሔት ዝግጅታችን የትግራይና የአማራ ክልሎች ልዩነቶቻቸውን በውይይት እንዲፈቱ ነዋሪዎች ያቀረቡት ጥያቄየአማራ ክልል ግጭት የወደፊቱ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይትየሲቪክ ድርጅቶች ምክረ-ሀሳብ ለተመድ የዓለም አፉ ፍርድ ቤት በእስራኤል ላይ በድጋሚ ያስተላለፈው ትዕዛዝ በተሰኙት ርዕሶች ስር የተጠናቀሩ ዘገባዎች ይቀርባሉ።...more18minPlay
March 28, 2024የመጋቢት 19፣2016 ዜና መፅሔትበአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞን አዋሳኝ አካባቢ ለተከታታይ ሁለት ሳምንታት የቀጠለው ግጭት ባለፉት ሁለት ቀናት ጋብ ማለቱን የየዞኖቹ ነዋሪዎች አስታወቁ።የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሊቀ መንበር ረዳት ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራ መታሰራቸው ተገለፀ።ከጋምቤላ ከተማ ወደ ኑዌር ዞን ይንቀሳቀስ ነበር በተባለው ተሽከርካሪ ላይ በደረሰው ጥቃት የአምስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶይቼቨለ ተናግረዋል። ጥቃቱ የደረሰው ትናንት ረቡዕ መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም ኢታንግ ልዩ ወረዳ አካባቢ ነው።...more27minPlay
March 27, 2024የዜና መጽሔት፦ መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም.በዛሬው የዜና መጽሔት ከተካተቱት ዘገባዎች መካከል -የአደባባይ ኢፍጣርና ርዳታ በድሬዳዋ-አማኑኤል ሆስፒታል ያጋጠመው የቦታ እጥረት-አብዛኛዉ የኢትዮጵያዊ ደሐ ነዉ የሚለውን ጥናት-ድርቅ፣ረሃብ እና የምግብ ዋስት እጦት በኢትዮጵያ በሚሉት ርዕሶች ስር የተጠናቀሩ ዘገባዎች ይገኙበታል።...more19minPlay
FAQs about ዜና መጽሔት:How many episodes does ዜና መጽሔት have?The podcast currently has 1,995 episodes available.