Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ... more
FAQs about ዜና መጽሔት:How many episodes does ዜና መጽሔት have?The podcast currently has 1,995 episodes available.
March 26, 2024የመጋቢት 17፣2016 ዜና መፅሔት-በትግራይ ክልል ከሚገኘዉ ከኢሮብ ወረዳ 60 በመቶ የሚሆነዉ አካባቢ አሁንም በኤርትራ ወታደሮች ቁጥጥር እንደሚገኝ የወረዳዉ ነዋሪዎች አስታወቁ። በጋምቤላ ክልል ማንነታቸዉ በዉል ያልታወቁ ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት ሰላማዊ ሰዎችን ገደሉ።-የአዲስ አበባ መስተዳድር በከተማይቱ የተለያዩ አካባዎች የሚገኙ መንደሮችንና ቤቶችን በጥድፊያ ማፍረሱን ነዋሪዎችና ነጋዴዎች ተቃዋሙ።ቅሬታ አቅራቢዎቹ እንደሚሉት መስተዳድሩ አንዳድ አካባቢዎች የሚገኙ ቤቶቹን የሚያፈርሰዉ አንድም ያለምንም፣ ሁለትም ባጭር ጊዜ ማስጠንቀቂያ ነዉ።...more18minPlay
March 25, 2024ዜና መጽሔት፦መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም.የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኢሰመኮ ብሔራዊ ምርመራ ውጤትበመቀሌ በእስር ላይ የሚገኙ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ከእስራ እንዲፈቱ ያቀረቡት ጥሪ የሰዎች ደብዛቸው መጥፋትና የቤተሰብ ጭንቀትታግተው ወይም ተማርከው የነበሩ 271 የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ተወላጆች ተለቀው አርባ ምንጭ መግባታቸው ከሩስያው የሽብር ጥቃት በኋላ አውሮጳን ያሰጋው የሽብር ጥቃት የዛሬው ዜና መጽሔት የሚያስቃኘን ጉዳዮች ናቸው።...more23minPlay
March 22, 2024የዐርብ፤ መጋቢት 13 ቀን፣ 2016 ዓ.ም መጽሄተ-ዜናበዜና መጽሔት ዝግጅቱ፤ 1. በእሥር ላይ የሚገኙ የ14 ሰዎች አቤቱታ 2. አማካሪ' ምክር ቤት በትግራይ ሊቋቋም መሆኑ 3. ኢትዮጵያ ዉስጥ የሰላምና የእርቅ ውትወታዎች ለምን ውጤት አልባ ሆኑ?4. የኩፍኝ ወረርሽኝ መስፋፋት እና በኦሮምያ ክልል የቀጠፈው ሕይወት፤ እንዲሁም 5. ትኩረት የሳበው የአውሮጳ ህብረት የመሪዎች ጉባኤየተሰኙት ርዕሶች በስፋት እንቃኛለን።...more21minPlay
March 21, 2024የሐሙስ መጋቢት 12 ቀን፣ 2016 ዓ.ም. ዜና መጽሄት-ሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ ከተማና አካባቢዉ ባካባቢዉ ሚሊሺያና ከሌላ አካባቢ የመጡ በተባሉ ታጣቂዎች መካከል በተደረገ ዉጊያ በትንሽ ግምት 10 ሰዎች ተገደሉ ። ከአካባቢዉ ባለስልጣናትም ሆነ ከመንግስት እስካሁን በግልፅ የተነገረ ነገር የለም።ጋምቤላ ክልል ውስጥ በዜጎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች አሁንም መቀጠላቸውን የጋምቤላ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ ። በአማራ ክልል ያሉ አሽከርካሪዎች ለከፍተኛ የነዳጅ እጥረት በመጋለጣቸው ሥራቸውን ማከናወን እንዳልቻሉ ተናገሩ ። አሽከርካሪዎቹ ለቀናት ሰልፍ በመያዝ ከማደያዎች ነዳጅ ለመቅዳት የሚያደርጉት ጥረትም ውጤት እንደሌለው ገልጠዋል ።...more28minPlay
March 20, 2024የዜና መጽሔት፦መጋቢት 11 ቀን 2016 ዓ.ም.ዜና መፅሔቱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አላግባብ የወጣ ወይም የተዛወረዉ ገንዘብና ተማሪዎች፣የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የፌደራሉን መንግስት የሽግግር ፍትሕ መተቸቱንና ሌሎችም ርዕሶችን ይተነትና...more21minPlay
March 19, 2024የማክሰኞ መጋቢት 10 ቀን፣ 2016 ዓ.ም መጽሄተ ዜናባለፈዉ የካቲት ማብቂያ በታጣቂዎች ታግተዉ የነበሩ የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች ተገድለዉ አስከሬናቸዉ ተጥሎ መገኘቱን ቤተሰቦቻቸዉ አስታወቁ። በኢትዮጵያ የሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን እና የማኅበራዊ ሚዲያ ጋዜጠኞች ከዘገባቸው ጋር ተያይዞ ከተለያዩ አካላት የሚደርስባቸውን ጫና እስር እና እንግልት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው ።ከሰሞኑ አዲስ አበባ ውስጥ የሙቀት መጠን መጨመርን ተከትሎ አልትራ ቫዮለንት (ቆዳን የሚጎዳ ከፍተኛ የጸሓይ ጨረር) ሊያስከትል ይችላል የሚለው መረጃ የማኅበራዊ መገኛኛ ዘዴዎችን በእጅጉ አጨናንቆት ተስተውሏል ፡፡ በመጽሄተ ዜና ከተካተቱ ጉዳዮች ይገኙበታል ።...more21minPlay
March 18, 2024ዜና መጽሔት፤ መጋቢት 9 ቀን 216 ዓ.ም ሰኞየዜና መጽሔት ዝግጅት ፤-ኦነግ ለዓመታት የታሰሩት አባላቱ እንዲፈቱ ያቀረበው ጥያቄ እና የአብዲ ኢሌን መፈታት ማዉገዙ-በፋኖ መታገታቸው የተነገረው የደቡብ ክልል ነዋሪዎች ጉዳይ-በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ባንክ ስርዓት ላይ ሰሞኑን ያጋጠመው ችግርና የአገልግሎት መቋረጥእንዲሁም የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለአምስተኛ የስልጣን ዘመን ማሸነፋቸው ላይ ያተኮሩ ዘገባዎችን አካቷል።...more20minPlay
March 15, 2024የዜና መጽሔት፦ መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም.በምሽቱ የዜና መጽሔት ዝግጅታችን -.በሃይቅ የሚገኙ ተፈናቃዮች የእርዳታ ተማፅኖ ጥሪ -የፖለቲከኞች ከእስር መለቀቅና የእነዶ/ር ወንድወሰን የፍርድ ቤት ውሎ-ታስረዉ የነበሩ የቀድሞ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ክስ መቋረጥ -ረቂቅ ሕግ የተዘጋጀበት፤ የሃይማኖት እና የብሔራዊ በአላት ጉዳይ በኢትዮጵያ፤እንዲሁም የአንድ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አመራሮች እግድየተሰኙት ርዕሶች በስፋት እንቃኛለን።...more20minPlay
March 14, 2024የሐሙስ መጋቢት 5 ቀን፣ 2016 ዓ.ም ዜና መጽሄትየፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት ግምገማ ስብሰባ ፍጻሜ፣ ህወሓት ስለ ስብሰባው ያወጣው መግለጫ፣በቁጥጥር ስር የሚገኙት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የአቶ ክርስቲያን ታደለ ያለመከሰስ መብት መነሳት፣ በመምህራን ደሞዝ አለመከፈል ጉዳይ ላይ የተወያየው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ፣ ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ያቀረበው ጥሪ እንዲሁም የሴቶች የተሀድሶና የክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል የዓለም ዜናን የሚከተለው የዜና መጽሔት የሚያስቃኘን ጉዳዮች ናቸው።...more27minPlay
March 13, 2024የረቡዕ መጋቢት 4 ቀን፣ 2016 ዓ.ም. የዜና መጽሄትኮሌራ ዳግም በሀረሪ ክልል ሕይወት ማጥፋቱ፤የትግራይ ተወላጅ የመከላከያ አባላት እንዲፈቱ መጠየቁ፤ቄሌም ወለጋ በፀጥታ ችግር የሰዎች ሕይወት እየጠፋ ነው፤በኦሮሚያ ክልል «የአቡነ ጴጥሮስ መንበር መስርተናል» ያሉ ታሳሪዎች መፈታት፤ትግራይ ክልል የሚገኙ ተፈናቃዮች ሮሮ ይሰኛሉ ዘገባዎቹ ።...more20minPlay
FAQs about ዜና መጽሔት:How many episodes does ዜና መጽሔት have?The podcast currently has 1,995 episodes available.