Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ... more
FAQs about ዜና መጽሔት:How many episodes does ዜና መጽሔት have?The podcast currently has 1,996 episodes available.
February 07, 2024የጥር 29 ቀን 2016 የዜና መጽሔትየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ትናንት ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ ተከልክለው ወደ አሜሪካ እንዲመለሱ መደረጉን ቤተ ክርስትያኗ አአረጋገጠች። በኦሮሚያ ክልል ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን የገበያ እና የመጓጓዣ አድማ ከጠራ 10 ቀናት በኋላ የነቀምቴ ከተማ ነዋሪዎች ለተለያዩ ማኅበራዊ እና ኤኮኖሚያዊ ችግሮች መዳረጋቸውን ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። የሴኔጋል ፕሬዝደንት ማኪ ሳል በዚህ ወር መጨረሻ ሊካሔድ ቀነ ቀጠሮ ተቆርጦለት የነበረውን ምርጫ በማራዘማቸው በሀገሪቱ ተቃውሞ ተቀስቅሷል።...more20minPlay
February 06, 2024በጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራርያ የተሰጡ የሕህዝብ አስተያየቶችጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ለሰጡት ምላሽ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ምን አስተያየት አላቸዉ? 350 የምክር ቤቱ አባላት ተገኝተዋል በተባለበት የዛሬው የምክር ቤቱ መደበኛ ጉባኤ ላይ 16 አባላት ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን አብዛኞቹ ጥያቄዎች የኢትዮጵያን ሰላምና ፀጥታ የተመለከቱ ናቸው።...more4minPlay
February 06, 2024ሰሞኑን በአማራ ክልል የተካሄዱ ህዝባዊ ዉይይቶች ላይ የተሰጡ አስተያየቶችበአማራ ክልል የተፈጠረውን የሰላም መደፍረስ በዘላቂነት ለመፍታትና አሉ በተባሉ ችግሮች ዙሪያ የፌደራልና የሁሉም ክልሎች ከፍተኛ ኃላፊዎች ሰሞኑን በአማራ ክልል 15 ያህል ከተሞች ህዝባዊ ውይይት አድርገዋል፡፡ ነዋሪዎች ውይይቱን በአወንታዊ ሲመለከቱት ሌሎች ደግሞ ውይይቶቹ ማዘናጊያና ሲሉ ተችተዋል፡፡...more4minPlay
February 06, 2024ድርቅ በአፋር ክልል ያስከተለው አደጋበቅርቡ የተከሰተው ድርቅ እንዲሁም የሰሜኑ ጦርነት ጥሎት ባለፈው አደጋ ምክንያት 40 በመቶ የክልሉ ሕዝብ አስቸኳይ የምግብና የውኃ አቅርቦት ፈላጊ እንዲሆን ማድረጉ ተገለፀ። የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት እስከ ስድስት መቶ ሺህ ያህሉ የክልሉ ሕዝብ በድርቅ ምክንያት ለችግር መዳረጉን አስታውቋል።...more4minPlay
February 06, 2024ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሰጡት ማብራርያመንግሥት ኢትዮጵያ ውስጥ ታጥቀው ከመንግሥት ጋር ከሚዋጉት ኃይሎች ጋር ለመነጋገር እና ለመወያየት ፍላጎት እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ሸኔም ሆነ በአማራ ክልል ያሉ ታጣቂ ኃይሎች" መሳሪያቸውን አስቀምጠው በሰላም ውይይት እንዲያደርጉ አሁንም መንግሥት ፍላጎት አለው" ብለዋል።...more5minPlay
February 05, 2024በተራዘመው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስተያየትበአማራ ክልል ለተጨማሪ አራት ወራት የተራዘመው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ የውስጥ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ የሚፈቱበት ሁኔታ አለመመቻቸቱን እንደሚያሳይ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ተናገሩ። የድንጋጌው መራዘም የሕዝቡን ችግር እንደማይቀርፍ ሌሎች ያነጋገርናቸው የፖለቲካ ድርጅቶች መሪዎችም ይናገራሉ።...more5minPlay
February 05, 2024እየተባባሰ የመጣው የመንገድ ላይ ጥቃትለወትሮው አንጻራዊ ደህንነት ይስተዋልባቸው የነበሩት ከአዲስ አበባ ሀዋሳ ፣ ወልቂጤና ቡታጅራ መንገዶች አሁን ላይ አሽከርካሪዎች በሥጋት ፤ መንገደኞች በፀሎት የሚጓዙባቸው መስመሮች ሆነዋል ነው የሚባለው ፡፡...more4minPlay
February 03, 2024በአማራ ክልል የተራዘመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና አንድምታውአማራ ክልል የተፈጠረውን የሰላም መደፍረስ ተከትሎ የተወካዮች ምክር ቤት ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ ም ለስድስት ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳ ጊዜ አዋጅ አፅድቋል፡፡ ምክር ቤቱ የጊዜውን መጠናቀቅ ተከትሎ ትናትን ባደረገው ልዩ ስብሰባ አዋጁ ለሌላ 4 ወራት እንዲራዘም ዉሳኔ አስተላልፏል፡፡...more5minPlay
FAQs about ዜና መጽሔት:How many episodes does ዜና መጽሔት have?The podcast currently has 1,996 episodes available.