Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ... more
FAQs about ዜና መጽሔት:How many episodes does ዜና መጽሔት have?The podcast currently has 1,995 episodes available.
February 13, 2024ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ኅብረት የሳሞአ ሥምምነት እንድትወጣ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠየቀየኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት የበላይ ጠባቂ አባቶች ህዳር 2016 ዓ. ም የተወሰኑ የአፍሪካ፣ የካሪቢያንና የፓሲፊክ ሀገራት የንግድና የኢኮኖሚ አሳሪ የአጋርነት ስምምነትን ከአውሮፓ ኅብረት ጋራ ``የሳሞአ ስምምነት`` መፈራረማቸውንና ኢትዮጵያ አንዷ ፈራሚ መሆኗን ጠቅሰው ኢትዮጵያ ራሷን ከስምምነቱ እንድታገል ጠይቀዋል።...more3minPlay
February 12, 2024የዓድዋ መታሰቢያ የአገር ግንባታ ፋይዳው - የሕዝብ አስተያየትአዲስ አበባ ውስጥ ግንባታው ተጠናቆ የተመረቀው ዓድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ለትውልድ አንድነት እና ለአገር ግንባታ የራሱ ሚና እንደሚኖረው ተነገረ፡፡ አስተያየታቸውን የሰጡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የሙዚየሙን ፋይዳ አጉልተው ያነሱት በርካቶች ናቸው፡፡ በተቃራኒው ግን ግንባታዉ ከሰላም እጦትና ከኢኮኖሚ አለመረጋጋት መቅደም የለበትም ያሉም ይገኛሉ፡፡...more4minPlay
February 12, 2024ዳግም የጀርመንን ምርጫ ያስተናገደችዉ በርሊን ከተማበርሊን ላይ በአንዳንድ አካባቢዎች በ 2021 ዓመት ተካሄዶ የነበረዉ ምርጫ በድጋሚ ተካሄደ። ወደ 500 ሺህ ግድም መራጮች የተሳተፉበት ይህ ምርጫ ዳግም የተካሄደዉ፤ በ 2021 ዓመት በተካሄደዉ ምርጫ አንዳንድ ድርጊቶች ሳይሟሉ በመቅረታቸዉ የተጓደለ ምርጫ ተካሄዷል...more5minPlay
February 12, 2024በማዕድን ቁፋሮ አፈር የተናደባቸዉ ከ20 በላይ ሰዎች እስካሁን አለመገኘታቸዉበአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ወገል ጤና ከተማ አቅራቢያ በባህላዊ ማዕድን ቁፋሮ ላይ የነበሩ ከ20 እስከ 30 የሚደርሱ ወጣቶች ባለፈው ሐሙስ ሌሊት ናዳ ተደርምሶ ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ በመግባታቸው የወጣቶቹ ህይወት ምን ላይ እንዳለ እንደማይታወቅ የአካባቢው ነዋሪዎች አመለከቱ፡፡ ወጣቶቹን በማሽን በታገዘ ቁፋሮ ማውጥት እንዳልተቻለም።...more4minPlay
February 09, 2024የየካቲት 1 ቀን 2016 የዜና መጽሔትየዜና መጽሄታችን 4 ርእሶች ይዟልሰሚ አጣን ያሉ የጃራ ተፈናቃዮች መንገድ ዘግተው የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸውን፤የቀይባሕር ዓፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት አምባገነን ያለውን የኤርትራ መንግስት በሕዝቡ ላይ የመከራ ቀንበሩን እያጠበቀ ነው ስለማለቱን፤የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአውሮጳ ሃገራት የሱዳን ስደተኞችን እንዲደግፉ ጥሪ ስለማድረጉ፤እንዲሁም የዶናልድ ትራምፕ የፍርድቤት ውሳኔና የሕግ ባለሙያ አስተያየት የሚሉ ናቸው።...more18minPlay
February 09, 2024በውጪ የሚኖሩ የቀይ ባሕር አፋር ወጣቶች ጥሪእንደ አቶ ያሲን፣ በአሁኑ ወቅት ኤርትራ ውስጥ ብዙ ግፍ እየደረሰበት እና እየተሰደደ ያለው ወጣቱ ክፍል ነው። «በአብዛኛው ወጣቱ ተሰዳጅ ነው። አሁን ብዙ ግፍ እየደረሰበት ያለው ሕዝብ ዋናው ተጠቂው አብዛኛው የቀይ ባሕር አፋር ወይም የኤርትራ ሕዝብ ወጣቱ ነው አብዛኛው። ይህ ክፍል ደግሞ ዛሬ በስደት ላይ ይገኛል።»...more4minPlay
February 07, 2024የጥር 29 ቀን 2016 የዜና መጽሔትየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ትናንት ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ ተከልክለው ወደ አሜሪካ እንዲመለሱ መደረጉን ቤተ ክርስትያኗ አአረጋገጠች። በኦሮሚያ ክልል ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን የገበያ እና የመጓጓዣ አድማ ከጠራ 10 ቀናት በኋላ የነቀምቴ ከተማ ነዋሪዎች ለተለያዩ ማኅበራዊ እና ኤኮኖሚያዊ ችግሮች መዳረጋቸውን ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። የሴኔጋል ፕሬዝደንት ማኪ ሳል በዚህ ወር መጨረሻ ሊካሔድ ቀነ ቀጠሮ ተቆርጦለት የነበረውን ምርጫ በማራዘማቸው በሀገሪቱ ተቃውሞ ተቀስቅሷል።...more20minPlay
FAQs about ዜና መጽሔት:How many episodes does ዜና መጽሔት have?The podcast currently has 1,995 episodes available.