
Sign up to save your podcasts
Or


አብዛኞቻቸን ስለ ሞት ለመናገር እምብዛም ፈቃደኛነቱ የለንም።
ጉዳዩን አንስቶ ለመነጋገር ፈቃደኛ ባለመሆን ሳቢያም፤ የቁርጡ ቀን ደርሶ ለህልፈተ ሕይወት መዳረግ ሲገጥም፤ ሁነቶች ከድጡ ወደ ማጡ ያመራሉ።
ከቤተሰብዎ ጋር ስለ ወርስ፣ የቀብር ሥነ ሥር ዓትና ሌሎችም የሚሹትን ነገሮች ቀደም ብሎ መነጋገሩ በጣም ጠቃሚ ነው።
Feature by Audrey Bourget and Ildiko Dauda
ዶ/ር ጸጋዬ ደግነህ፤ የአፍሪካ ጁ-ጂትሱ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚደንትና የዓለም አቀፍ ጁ-ጂትሱ ፌዴሬሽን የሥነ ምግባር ኮሚቴ ምክትል ፕሬዚደንት፤ ያሬድ ንጉሤ፤ የ2017 ሮክሎው ጁ-ጂትሱ ተወዳዳሪና የአፍሪካ ጁ-ጂትሱ ሻምፒዮን፤ ስለ 2017ቱ ሮክሎው ጁ-ጂትሱ ውድድር ውጤት፤ እንዲሁም በኢትዮጵያና በአፍሪካ የስፖርቱን ዕድገትና ሂደት አስመልክተው ይናገራሉ።
ያሬድ ንጉሤ፣ ቀደም ሲልም በኦስትሪያ፣ ኬንያ፣ ጀርመንና ብራሰልስ ዓለም አቀፍ የጁዶና ጁ-ጂትሱ ውድድሮች ተካፍሏል።
ፕሮፌሰር ተከስተ ነጋሽ፤ እቴጌ ጣይቱ በፖለቲካ፣ ዲፕሎማሲና ወታደራዊ አመራር ብቃታቸው ለኢትዮጵያ ስላበረከቱት አስተዋጽኦዎች ይናገራሉ። ይናገራሉ። ፕሮፌሰር ተከስተ፤ “Woven into the Tapestry: How Five Women Shaped Ethiopian History” መጽሐፍ ደራሲ ናቸው።
ከዚህ ዓለም በሞት በሚለዩበት ወቅት የሰውነትዎን አካላት በመለገስ የ10 ሰዎችን ሕይወት እንደሚታደጉ ያውቃሉ?
በሺህዎች የሚቆጠሩ አውስትራሊያውያን ለአካላት ወይም ለደም ማጣራት ወረፋ ይዘው በሚገኙበት በአሁኑ ወቅት፤ የሰውነት አካል ለጋሽ የመሆኑ ጉዳይ ከመቼው በላቀ መልኩ በጣሙን አሥፈላጊ የሆነበት ጊዜ ነው።
Feature by Audrey Bourget
ፕሮፌሰር ተከስተ ነጋሽ፤ የንግሥተ ሳባ (ንግሥት ማክዳ) ታሪክ፤ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ማንነት በመቅረጹ ረገድና ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት መጎልበት ስላበረከታቸው አስተዋጽኦዎች ይናገራሉ። ይናገራሉ። ፕሮፌሰር ተከስተ፤ “Woven into the Tapestry: How Five Women Shaped Ethiopian History” መጽሐፍ ደራሲ ናቸው።
አቶ የሺዋስ አሰፋ፤ የሰማያዊ ፓርቲ ፕሬዚደንት፣ በቅርቡ በኢፌዴሪ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸድቆ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተመራውን የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ላይ ያለውን ልዩ ጥቅም ረቂቅ አዋጅ አስመልክተው ይናገራሉ።
ጋዜጠኛ ኤልያስ አማረ፤ የአሥመራ ከተማ ጁላይ 8, 2017 በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስ ባሕል ድርጅት (UNESCO) በዓለም ቅርስ ከተማነት መመዝገብን አስመልክተው ይናገራሉ።
ዶ/ር ጫኔ ከበደ፤ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ፕሬዚደንት፣ በቅርቡ በኢፌዴሪ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸድቆ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተመራውን የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ላይ ያለውን ልዩ ጥቅም ረቂቅ አዋጅ አስመልክተው ይናገራሉ።
አቶ መሐመድ ሐሰን፤ የቀድሞው የኢፌዴሪ መንግሥት ዲፕሎማት፣ ደራሲ፣ የአፍሪካ ቀንድና የመካከለኛው ምሥራቅ ጉዳዮች ተንታኝ፤ ስለ ኢትዮ-ኤርትራ ግንኙነቶችና የአካባቢውን የሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች አስመልክተው ይናገራሉ።
ፋሲካ አያሌው የአውስትራሊያው ቻናል 9 ቴሌቪዥን እያካሄደ ባለው The Voice የድምጻውያን ውድድር ለመጨረሻ ማጣሪያ ከደርሱት አንዷና ብቸኛዋ ኢትዮጵያዊት-ፊሊፒኖሳዊት-አውስትራሊያዊት ናት።
ወላጆችዋ ዶ/ር ደሳለኝ አያሌውና ወ/ሮ ሱዛን አያሌው፤ ስለ ፋሲካ የሙዚቃና የትምህርት መንታ መንገድ ጉዞ አንስተው ዝንቅ ስጋትና ደስታቸውን ያወጋሉ።
ድምፃዊት ፋሲካም ለአውስትራሊያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ምሥጋናዋን አቅርባለች።The Voice የመጨረሻ ማጣሪያ ውድድር የሚካሄደው እሑድ ጁላይ 2, 2017 ነው።
From the publisher's feed
Ranked by our users in the last 21 days

10 Listeners

9 Listeners

111,856 Listeners

0 Listeners

1 Listeners

0 Listeners

0 Listeners

3 Listeners

0 Listeners

1 Listeners

0 Listeners

0 Listeners

0 Listeners

0 Listeners

0 Listeners

0 Listeners

0 Listeners

0 Listeners

0 Listeners

0 Listeners

0 Listeners