Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ... more
FAQs about ዜና መጽሔት:How many episodes does ዜና መጽሔት have?The podcast currently has 1,841 episodes available.
May 13, 2024DW Amharic - ዜና መጽሔት፤ የግንቦት 5 ቀን፣ 2016 ዓ.ም ሰኞDW Amharic - ከባድ ዝናብ ድንኳናቸውን ያፈራረሰባቸው በደቡብ ወሎ የሚገኙ ተፈናቃዮች ፤ በድሬደዋ የጎርፍ ጉዳትን ለመቀነስ ያለመው ፕሮጀክት፤ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ቦረና ዞን የተማሪዎች ጥያቄና ስጋት፤እንዲሁም ጅቡቲ ለዓለም አቀፍ ባለሀብቶች ያቀረበችውን የልማት ጥሪ የተሰኙ ዘገባዎች ተጠናቅረዉበታል።...more18minPlay
May 08, 2024DW Amharic የሚያዝያ 30 ቀን 2016 ዜና መጽሔትጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በነቀምቴ ከተማ ከአራቱም የወለጋ ዞኖች ለተውጣጡ የማኅበረሰብ ክፍሎች “ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ምላሽ አግኝቷል፤ ለዚህ አንታገልም” ሲሉ ተናገሩ። በግጭት ምክንያት በአማራ ክልል ደም ባለመሰብሰቡ ሆስፒታሎች ሕሙማን ለማከም ችግር ገጥሟቸዋል። በትግራይ ክልል የሚገኘው እና በጦርነት ወቅት የተጎዳው የአል ነጃሺ መስጂድ መልሶ ለመገንባት ያቀደ መርሐ ግብር ይፋ ተደረገ። ኢትዮጵያ በፕሬስ ነጻነት ባለፈው ዓመት ከነበረችበት በአስራ አንድ ደረጃዎች ወደ ኋላ አሽቆለቆች። እስራኤል በራፋ የጀመረችው ወታደራዊ ዘመቻ እንዳሳዘናቸው የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ግንኙነት ኃላፊ ጆሴፕ ቦሬል ተናገሩ።...more21minPlay
May 07, 2024የማክሰኞ ሚያዝያ 29 ቀን፣ 2016 ዓ.ም ዜና መፅሔትየሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት)ኃይላት ከሱዳን ጦር ጋር ወግነው እየተዋጉ ነው በማለት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ያቀረበውን ክስ የትግራይ ክልል ዜያዊ አስተዳደር አስተባበለ። በአማራ ክልል የሰሜን ጎጃም ዞን መምህራን ደመወዝ ከተከፈላቸው ከ2 ወራት በላይ መሆኑን ዐስታወቁ።የቅድመ ክስ እሥርን ለመቆጣጠር እና ለማስቀረት እንዲሁም የፍትሐዊ እና ሰብአዊ መብት መርኾችን ያካተተ የወንጀል ፍትሕ ሥርዓት ለመገንባት፤ የፍትሕ አካላት እና ሌሎች ባለድርሻዎች ግዴታቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ።በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞን ዛሬ ጠዋት የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ነዋሪዎች ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል...more19minPlay
May 06, 2024DW Amharic የሚያዝያ 28 ቀን 2016 ዜና መጽሔትበነሐሴ 2014 የተመሠረተው የሲዳማ ፌድራሊስት ፓርቲ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እየተወዛገበ ነው። በትግራይ የሚገኙ አንድ ሚልዮን ገደማ የጦርነቱ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ለመመለስ ተስፋ አድርገዋል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንና አገልጋዮቿ ላይ የሚደረገው "ማሳደድና እስር በአስቸኳይ ይቁም" ሲል እናት ፓርቲ ባወጣው መግለጫ ጠየቀ።...more14minPlay
May 02, 2024የሐሙስ ሚያዚያ 24 ቀን፣ 2016 ዓ.ም. ዜና መጽሄትበዕለቱ መጽሄተ ዜና አምስት ጉዳዮችን እናስተነትናለን። ዘገባዎቹ፦ የቀሲስ በላይ መኮንን የችሎት ውሎ፤ ብርቱ ዝናም ተፈናቃዮችን ከድንኳናቸውም አፈናቀለ፤ የአውሮጳ ሕብረት ምክር ቤት ውሳኔ - የኢትዮጵያ ምላሽ፤ የነዳጅ እጥረት በኦሮሚያ ክልል እንዲሁም ስደተኞችን ለመግታት የአውሮጳ ኅብረት 1,07 ቢሊዮን ዶላር ለሊባኖስ ይሰኛሉ ።...more22minPlay
May 01, 2024የሚያዝያ 23 ቀን 2016 የዜና መፅሔትመንግስት በየጊዜው የሚካሄዱ ግድያዎችንና የዘፈቀደ እስር እንዲያቆም መጠየቁ፣የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕረዚደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ ጋዜጣዊ መግለጫ፣የሃይማኖት መሪዎችና የሃገር ሽማግሌዎች በግጭት አፈታት ላይ ሚናቸው እየቀጨጨ እንደመጣ መገለጹን፣በአማራ ክልል ድርቅና መፈናቀል የተረጂዎች ቁጥር እንዲያሻቅብ ማድረጉን...more16minPlay
FAQs about ዜና መጽሔት:How many episodes does ዜና መጽሔት have?The podcast currently has 1,841 episodes available.