Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ... more
FAQs about ዜና መጽሔት:How many episodes does ዜና መጽሔት have?The podcast currently has 1,841 episodes available.
May 27, 2024የግንቦት 19 ቀን 2016 ዓ.ም. የዜና መጽሔትበደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ከሚገኘው የቡልቂ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ግንባታ ጋር በተያያዘ ከ15 ሚሊየን ብር በላይ በመመዝበር የተጠረጠሩ ባለሞያዎች እየተያዙ ነው፣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፤ የክልሎች ምክክር ምዕራፍን ከፊታችን ረቡዕ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በአዲስ አበባ እንደሚጀምር ዛሬ አስታውቋል። አፍሪቃ ኅብረት ቅጽር ግቢ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለማጭበርበር በመሞከር ተጠርጥረው የታሰሩት ቀሲስ በላይ መኮንን ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።...more14minPlay
May 22, 2024የግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም የዜና መጽሔትበታሪካዊቱ ላሊበላ ከተማ ዙሪያ በመንግሥትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ለሰዓታት የዘለቀ ውጊያ መካሄዱ፤ በትግራይና አፋር ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ የሰባት ሲቪሎች መገደል፤ የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን በነፍጥ ለሚፋለሙ ኃይላት ያቀረበው ጥሪ የት ደረሰ? በኦሮሚያ ክልል የቀጠለው ግጭት በሲቪል ዜጎች ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ፤ እንዲሁም በአሜሪካ የሚገኙ የኢትዮጵያ ሲቪክ ድርጅቶች የጻፉትን ደብዳቤ...more21minPlay
May 21, 2024የዜና መጽሔት፤ ግንቦት 13 ቀን፣ 2016 ዓ.ምDW Amharic የዉህዳን እና ሕዳጣን ማሕበረሰቦች መብት፤ የአቶ ታዬ ደንደዓ የክስ መቃወሚያ ውድቅ መሆን፤ በማጎ ብሄራዊ ፓርክ የስጳኝ ዜጋን ጨምሮ 4 ሰዎች ተገደሉ፤ እንዲሁም የአለማቀፍ ወንጀሎች መዳኛ ፍርድ ቤት በእስራኤልና ሀማስ መሪዎች ላይ ያቀረበው ክስ ጭብጥ የተሰኙ ርዕሶች ተጠናቅረዉበታል...more21minPlay
May 20, 2024DW Amharic የግንቦት 12 ቀን 2016 የዜና መጽሔትከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአፍሪካ ኅብረት አካውንት 6 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ለማጭበርበር ሞክረዋል በሚል በቁጥጥር ሥር ከዋሉ ተጠርጣሪዎች መካከል አራቱ አሁንም በፖሊስ ጣቢያ እንዲቆዩ ፍርድ ቤት አዘዘ። የወላይታ ዞን የሠራተኞቹን ደሞዝ ከሚቀጥለው ዓመት ተበድሮ ለመክፈል መገደዱ ተገለጸ። የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የጦር መሳርያ ዝውውርን ለመቆጣጠር እየጣረ መሆኑን አስታወቀ። በኦሮሚያ ክልል በምትገኘው ኪረሙ ከተማ 50 ሺሕ ተፈናቃዮች ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን የምሥራቅ ወለጋ ዞን ገለጸ። የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ለእስራኤልና ፍልስጤም የሁለት መንግሥት መፍትሔ ለማስገኘት እየሰሩ መሆናቸውን አስታወቁ...more21minPlay
May 17, 2024የግንቦት 9፣2016 ዜና መፅሔት-በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሥለ ኢትዮጵያ ፖለቲካዊና የሰብአዊ መብት ይዞታ የሰጡትን አስተያየት ኢትዮጵያ አጥብቃ ተቃወመችዉ።የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ባወጣዉ መግለጫ የአምባሳደሩን አስተያየት «ሐሰት« ና «ተቀባይነት» የሌለዉ በማለት አጣጥሎታል።-በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዎላይታ ዞን ደሞዝ ያልተከፈላቸዉ የመንግስት ሠራተኞች ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ያደረጉት ሰልፍ በፖሊስ ኃይል ተበተነ።-በቀጣዮቹ ሁለት ወራት 75 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎች ወደ ሰላማዊ ሕይወታቸው ለመመለስ እቅድ መያዙ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የተሃድሶ ኮምሽን አስታወቀ...more21minPlay
May 16, 2024የሐሙስ ግንቦት 8 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የዜና መጽሄትየዜና መጽሔ ዘገባዎቹ፦ለኢትዮጵያው ግጭት መፍትሄ የአሜሪካ ጥሪ፦ የአምባሳደሩ ንግግር፤ ለባሕላዊ ዳኝነት ትኩረት የሰጠው የፍትሕ ተቋማት ሽግግር ፤ የሲቪል ድርጅቶች ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አጀንዳዎችን አስገቡ፤ የኢትዮጵያ ኢንደስትሪ ዞኖች እጣፈንታ እና የፖሊሲ ለውጥ እንዲሁም እስራኤል በራፋሕ ላይ የከፈተችው ጦርነት ይሰኛሉ ።...more27minPlay
May 15, 2024የግንቦት 7 ቀን 2016 ዓ.ም. የዜና መጽሔትየአሜሪካን የአፍሪቃ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛን፣ የኦሮምያን የፖለቲካና ፀጥታ ችግር ለመፍታት ሁሉን አቀፍ ድርድር እንዲደረግ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ጠይቀዋቸዋል። በአማራ ክልል የሰላም እጦት ሰበብ በተለያዩ አካባቢዎች ትምሕርት ቤቶች በመዘጋታቸው ሴት ተማሪዎች እንዲያገቡ እየተገደዱ መሆኑን ነዋሪዎች ለዶቼቬለ ተናግረዋል።በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሶዶ ዙሪያ ወረዳ የመንግሥት ሠራተኞች ደሞዝ እንዲከፋላቸው በአደባባይ ሰልፍ ጠይቀዋል። እነዚህና የካናዳ መንግሥት እርዳታ ለቀድሞ ተዋጊዎች እንዲሁም በጎ ፈቃደኛዋ ሲስተት ካሕሳ ሓጎስ መሸለማቸውን የሚያስቃኙ ዘገባዎች ተካተዋል።...more21minPlay
May 14, 2024የማክሰኞ፤ ግንቦት 6 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የዜና መጽሄትየፖለቲከኛ በቴ ዑርጌሳን ግድያ የምርመራ ሂደት ምን ተግዳሮት ገጥሞት ይሆን?--ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ተማጋጋቢዎቹ ጎረቤት ሀገራት--በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ በተከሰተ ግጭት የሰው ህይወት ማለፉ እንዲሁም --የአዉሮጳ ህብረት 2024 ምርጫ ዛሬ ከያዝናቸዉ ለማስደ,ጥ ከያዝናቸዉ ዘገባዎቻችን መካከል ጥቂቶቹ ናቸዉ...more17minPlay
FAQs about ዜና መጽሔት:How many episodes does ዜና መጽሔት have?The podcast currently has 1,841 episodes available.