Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about ስፖርት | Deutsche Welle:How many episodes does ስፖርት | Deutsche Welle have?The podcast currently has 509 episodes available.
February 20, 2023የካቲት 13 ቀን፣ 2015 ዓ.ም የስፖርት ዘገባየአደይ አበባ ብሔራዊ ስታዲየም ግንባታ መጓተት በሚሊዮን የሚቆጠር የብር ብክነትን አስከትሏል። ከንድፍ አንስቶ በግንባታ ሒደቱ ከ11 ዓመታት በላይ ያስቆጠረው የስታዲየም ግንባታ ጉዳይ በቢሊዮን የሚቆጠር ተጨማሪ የሀገሪቱ ሀብትን አደጋ ላይ ጥሏል። ነገ እና ረቡዕ የሻምፖዮንስ ሊግ ወሳኝ ግጥሚያዎች ይኖራሉ። ሪያል ማድሪድ ከሊቨርፑል ጋር ተፋጧል።...more12minPlay
January 23, 2023የጥር 15 ቀን፣ 2015 ዓ.ም የስፖርት ዘገባበእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ፦ እጅግ ውብ ፉክክር በታየበት ግጥሚያ አርሰናል ማንቸስተር ዩናይትድን ድል በማድረግ ዘንድሮ ዋንጫውን ለማንሳት የቆረጠ መሆኑን ዐሳይቷል። ኧርሊንግ ኦላንድ በዘንድሮ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ለማንቸስተር ሲቲ አራተኛ ሔትትሪኩን ሠርቷል። በጀርመን ቡንደስሊጋ ቬርደር ብሬመን በኮሎኝ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቷል።...more10minPlay
January 09, 2023የጥር 1 ቀን፣ 2015 ዓ.ም የስፖርት ዘገባዘንድሮ አልጀሪያ በምታስተናግደው የአፍሪቃ ሃገራት ሻምፒዮን (CHAN) ግጥሚያ ተፎካካሪ የሚሆነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን በምድብ «ሀ» ከሞዛምቢክ፤ አልጀሪያ እና ሊቢያ ጋር ከቀናት በኋላ ይጋጠማል። በስፔን አገር አቋራጭ የ10 ሺህ ሜትር የሩጫ ፉክክር ኢትዮጵያዊው አትሌት ሰሎሞን ባረጋ አሸናፊ ሆኗል።...more11minPlay
January 02, 2023የታኅሣሥ 24 ቀን፣ 2015 ዓ.ም የስፖርት ዘገባኤድሰን አራንቴስ ዶ ናሲሜንቶ የኳስ ንጉሡ ፔሌ ስንብት ዛሬ እየተካሄደ ነው። ከዓለማችን ድንቅ ተጨዋቾች አንዱ የሆነው ፖርቹጋላዊ አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለሳዑዲ ዓረቢያው አል ናስር መፈረሙ ቡድኑን በማኅበራዊ መገናኛ አውታር እጅግ ዝነኛ አድርጎታል። አትሌቲክስ እና ሌሎች የስፖርት መረጃዎንም አካተናል።...more10minPlay
FAQs about ስፖርት | Deutsche Welle:How many episodes does ስፖርት | Deutsche Welle have?The podcast currently has 509 episodes available.